Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ የባዶ እግር ትሩፋቶች ሲዘከሩ

ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ የባዶ እግር ትሩፋቶች ሲዘከሩ

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሊምፒክ ማራቶን ድሉ 60ኛ ዓመትን ጨምሮ ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ የተሳተፉ የአትሌቲክስ  ባለድሎችን “የባዶ እግር ትሩፋቶች” በሚል መሪ ቃል ተተኪዎች የሚፈሩባቸው የማዘውተሪያ ግንባታዎችን በማከናወን እያሰባቸው ይገኛል፡፡

ፌዴሬሽኑ ካለፈው ቅዳሜ ታኅሳስ 3 እስከ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ያዘጋጀው መርሐ ግብር ተተኪዎች የሚፈሩባቸው የአትሌቲክስ መሠረተ ልማቶች ላይ ትኩረት በማድረግ ፕሮግራሙን ለየት እንዲል አድርጓል፡፡ አትሌቲክሱን ጨምሮ በሌሎችም ስፖርቶች ለረዥም ጊዜ ይነሳ የነበረውን የሥልጠናና የማዘውተሪያ ቦታ ችግሮችን ያስወግዳል የሚለውን ታሳቢ ለማድረግ መርሐ ግብሩ ተዘጋጅቷል ብሏል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ኅዳር 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ጉርድ ሾላ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ አጠገብ 753 ካሬ ሜትር ባዶ ቦታ ላይ ለሚያስገነባው ባለ 12 ወለል ድብልቅ አገልግሎት የሚሆን ሕንጻ የመሠረት ድንጋይ ያስቀምጣል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን በለገጣፎ ለገዳዲ ባስገነባው ማዘውተሪያ ሥፍራ ምርቃት ላይ ቀደምቶቹ አትሌቶች የሚታሰቡበት አንድ አካል ይሆናል፡፡

ማዘውተሪያው ለአትሌቶች ልምምድ የሚሆን 1.6 ኪሎ ሜትር የአሸዋ ጥርጊያ ሜዳ፣ 400 ሜትር የአሸዋ ትራክ (መም)፣ የመታጠቢያና መጸዳጃ ቤቶች እንዲሁም የልብስ መቀየሪያና ማረፊያ ቦታዎችን ያካተተ ነው፡፡ ግንባታው ከ17 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉንም ገልጿል፡፡

ቀደምቶቹን በሚያስበው የሁለተኛው ቀን በጠዋቱ መርሐ ግብር፣ ለአትሌቲክሱ ፈር ቀዳጅ የሆኑት ሻምበል አበበ ቢቂላና ሻምበል ማሞ ወልዴ መካነ መቃብራቸው በሚገኝበት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ፌዴሬሽኑ ያስገነባው ሐውልት ይመረቃል፡፡ በዚሁ ዕለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመገኘት የሞስኮ ኦሊምፒክ የድርብ ድል ባለቤቱ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠርና ስመ ጥሩው አሠልጣኝ ወልደመስቀል ኮስትሬ (ዶ/ር) የሚያስታውስ የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎትና አበባ የማስቀመጥ መርሐ ግብር የሚከናወን ይሆናል፡፡

እንደ ፌዴሬሽኑ፣ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ የሻምበል አበበ ቢቂላ የሮም ኦሊምፒክ 60ኛ ዓመት የማራቶን ድል እና ከሜልቦርን (1956) እስከ ሪዮ ዴጄኔሮ (2016) ኦሊምፒክ በአትሌቲክሱ ተሳትፈው ኢትዮጵያን ያስጠሩ ጀግኖች በሸራተን አዲስ ይታወሳሉ፡፡ በፕሮግራሙ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣኖችና የአትሌቲክሱ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን የወከሉ አትሌቶችና በሕይወት የሌሉ ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት የሽልማትና የምሥጋና ሥርዓት ከመፈጸም ባለፈ በሦስቱ ቀደምቶች አበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴና ምሩፅ ይፍጠር ስም የተዘጋጀ የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት ይደረጋል፡፡

በመጨረሻም ሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በሚያከናውነው 24ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንትና የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ የዚሁ ፕሮግራም አንድ አካል መሆኑ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹በየቦታው ምርት እየገዙ የሚያከማቹ ከበርቴ ገበሬዎች ተፈጥረዋል››

አቶ ኡስማን ስሩር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር...

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...