Thursday, June 8, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ዓለማየሁ ገዳ(ፕርሮፌሰር)ና ብርሃኑ አበጋዝ(ፕሮፌሰር)ን ጨምሮ 16 የምጣኔ ሃብት ሙሁራን የተካተቱበት ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ተቛቛመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

አጠቃላይ የኢኮኖሚውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የሙሁራንንና የባለሙያዎችን ግብረ መልስ መቀበል ጠቃሚ መሆኑን በማመንና ገለልተኛ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤት ለማቋቋም፣ እጩ አባላትን በጥቆማና በሥራ ማመልከቻ ለመቀበል  ባለፈው ዓመት ታህሣሥ 21 ቀን 2012 ዓም ባወጣው ማስታወቂያ መሠረት  290 ምሁራንን ማግኘት መቻሉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።
በመሆኑም የቀረቡትን እጩ ምሁራን በሦሥት በመክፈል በተደረገ ማጣራት፣አለማየሁ ገዳ(ፕሮፌሰር)፣ ብርሃኑ አበጋዝ(ፕሮፌሰር)፣ጋቢሳ እጀታ(ፕሮፌሰር)ና መላኩ ደስታ(ፕሮፌሰር)ን ጨምሮ 16 ምሁራንን በመምረጥ ብሔራዊ የኢኮኖሚ ምክር ቤቱ ዛሬ ታህሣሥ 5 ቀን 2013 ዓም መቋቋሙን ጽሕፈት ቤቱ ይፋ አድርጓል።
ምክር ቤቱ ገለልተኛ ከሆኑ ምሁራንና ባለሙያዎች  ሀሳብ ከመቀበልና የፖሊሲ አካታችነትን ከመቀበል ባለፈፈ፣ ያልታዩ ጉዳዮችን ለማየት፣አገሪቷ ያለችበትን ውስብስብ የሆነ ድህነትንና ሌሎች ማህበራዊ ችግሮችን ለመረዳትና ውጤታማ የፖሊሲ አማራጮችን ለመመርመር እንደሚያስችል ጽሕፈት ቤቱ ገልጿል።

Bid

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች