Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በመተማ በኩል ሕገወጥ የዓሳ ንግድ መበራከቱ ተገለጸ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከተከዜና ከጣና በሕገወጥ መንገድ ተጠምዶ በመተማ በኩል እየወጣ ያለው የዓሳ ሀብት፣ በሕጋዊ መንገድ ለገበያ ከሚቀርበው በላይ መሆኑን የአማራ ክልል የእንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ የክልሉ መንግሥት የያዘውን ሳይጨምር በተያዘው ሩብ ዓመት ብቻ፣ ወደ 15 ቶን የሚጠጋ የዓሳ ምርት በሕገወጥ መንገድ ወደ ሱዳን እንደወጣ መረጃው እንደደረሳቸው ተናግረዋል፡፡

የአማራ ክልል ሰፊ የሆነ የዓሳ ሀብት ቢኖረውም አሁን ግን ሕገወጥ የዓሳ አቅራቢዎች ራሳቸውን በጦር መሣሪያ በማደራጀት ጭምር በሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣ የዓሳ አቅርቦት ሥራው ወደ ሕገወጥነት እያደላ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

አዋሽ ባንክ የጨረታ ማስታወቂያ

ሕገወጥ ነጋዴዎቹ ለዓሳ ማጥመጃነት የሚገለገሉበት መረብ ከየት እንደሚመጣ አለመታወቁ፣ አልፎ ተርፎም የማጥመዱ ሥራ የሚከናወነው በሌሊት መሆኑ የቁጥጥርና የክትትል ሥራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

‹‹በሌሊት የሚደረገው ዓሳ ማጥመድ ብቻም ሳይሆን ግብይይትም ነው ያሉት አቶ ደበበ›› ሕገወጥ እንቅስቃሴውን ለመግታት የፀጥታም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ቅንጅትና ርብርብ ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ መንግሥት እንስሳት ሀብት ልማት ኤጀንሲ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ ችግሩ ምን እንደሆነ፣ የትና ለምን የሚሉትን ጉዳዮች መለየቱን፣ ከዚህ በኋላ የጋራ ውይይቶች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማድረግ ለሁሉም የየድርሻውን ኃላፊነት በመስጠት፣ ችግሩን የመቅረፍ ሥራ እንደሚከናወን ተናግረዋል፡፡

ሕገወጥነት በሁሉም የግብይት ዓይነቶች እንዳለ፣ ወተትና ማርን ከባዕድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል ጭምር እየተከናወነ የሚገኝ ተግባር ቢሆንም፣ የሁሉም አካላት ቅንጅት እስካለ ድረስ የሚቀረፍ መሆኑን የኤጀንሲው ዋና ሥራ አስኪያጅ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የሚደረገውም የሰላምና ፀጥታ ማስከበር ሒደት በተጠናከረ ቁጥር ሕገወጥነቱን በጊዜ ሒደት ማድረቅ እንደሚቻልም አክለዋል፡፡

በኤልያስ ተገኝ

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች