Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለአወዛጋቢው የአፍሪካ ጤና አጠባበቅና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የመሠረት...

ለአወዛጋቢው የአፍሪካ ጤና አጠባበቅና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ) ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

ቀን:

በአሜሪካና በቻይና መንግሥታት እንዲሁም በሞሮኮና የኢትዮጵያ መንግሥታት መካከል ውዝግብ ፈጥሮ የቆየው፣ የአፍሪካ በሽታ አጠባበቅና መከላከል ማዕከል (ሲዲሲ)፣ በአዲስ አበባ በ100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንዲገነባ ሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ፡፡

የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽን እ.ኤ.አ. በ2012 ዓ.ም. የገነባችው ቻይና የአፍሪካ ሲዲሲን ለመገንባት እ.ኤ.አ. ጁን 2019 ከአፍሪካ ኅብረት የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኢልፋዲል መሐመድ ጋር ስምምነት ከተደረገ በኋላ፣ አሜሪካ ሥጋቷን ስትገልጽ ቆይታለች፡፡ እንደ ሞሮኮ ያሉ አገሮች ደግሞ ከኢትዮጵያ የተሻልን በመሆናችን ተቋሙ እኛ ዘንድ ቢገነባ የተሻለ አገልግሎትና ድጋፍ እንዲያገኝ ማድረግ እንችላለን ሲሉ ነበር፡፡

በተለይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የቻይና መንግሥትና የዓለም ጤና ድርጅትን ቫይረሱን ደብቀዋልለ በማለት በመውቀሳቸው፣ ለዓለም የጤና ድርጅት አገራቸው ታደርግ የነበረውን ድጋፍ ያቋረጠች ሲሆን፣ ይኼንን ተከትሎም በአሜሪካና በቻይና መካከል የሚደረገው የቃላት ጦርነት ተካርሮ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አዋሽ ባንክ የጨረታ ማስታወቂያ

ከዚህ በኋላ ቻይና የአፍሪካ ሲዲሲን ለመገንባት ዕቅድ እንዳላት፣ ከአፍሪካ አኅጉር ጋር ያላትን ስትራቴጂካዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ይረዳኛል ያለችውን ፕሮጀክት ለመገንባት በጀት መድባ ስትንቀሳቀስ ነበር፡፡

ይሁንና የአፍሪካ ኅብረት የመሰብሰቢያ አዳራሽና የኅብረቱን ኮምፒዩተሮች መጥለፍና መረጃዎችን ወደ ቻይና መላክ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎች ተጠምዳ እንደነበር፣ ይህም እ.ኤ.አ. በ2017 በመታወቁ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ እንደነበር በማውሳት፣ የአሜሪካ ቅሬታ ‹‹አሁንም ቢሆን ቻይና የአፍሪካ ሲዲሲ ማዕከልን ለመገንባት የምትሻው ለአፍሪካ አስባ ሳይሆን፣ የአፍሪካን ሲዲሲን በመሰለል፣ በአፍሪካ የሚገኙ በሽታዎችን ዘረመላዊ መረጃ በመሰብሰብ ለወደፊት የሚሆኑ መድኃኒቶችን ለማምረት የበላይነትን ለማግኘት በማለም የገባችበት ተግባር ነው፤›› በማለት ተችታለች፡፡

ስለዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገነባውን የሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ቻይና የምትገነባው ከሆነ፣ ለተቋሙ አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምታውቆም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዝተው ነበር፡፡ ስለዚህም የኢቦላን ወረርሽኝ መከሰት ተከትሎ እ.ኤ.አ. በ2017 የተመሠረተው የአፍሪካ ሲዲሲ መሥሪያ ቤት ግንባታ በቻይና እጅ እንዳይገባ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ፕሬዚዳንቱ ተናግረው ነበር፡፡

አሁን በቻይናው ሲሲኢሲሲ የግንባታ ተቋራጭ ኩባንያ የሚገነባውና ከአጠቃላዩ 9,000 ካሬ ሜትር መሬት ቅጥር ግቢ ውስጥ በ4,000 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፈው የዚህ ተቋም ዋና መሥሪያ ቤት የመሠረት ድንጋይ፣ የአፍሪካ ኅብረት የማኅበራዊ ጉዳዮች ኮሚሽነር አሚራ ኢልፋዲል መሐመድ፣ በአፍሪካ ኅብረት የቻይና አምባሳደር ሊዩ ዩሺ፣ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ተቀምጧል፡፡

የአፍሪካና የቻይና ወዳጅነትን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል የተባለለት ይኼ ፕሮጀክት በ25 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የማኅበራዊ ጉዳይ ኮሚሽነሯ አሚራ ኢልፋዲል ‹‹አፍሪካ እንተባበር ከሚላት ማንኛውም አካል ጋር ለመተባበርና አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ናት›› ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ከዋና መሥሪያ ቤቱ በተጨማሪ በአምስት የአፍሪካ አገሮች ቀጣናዊ ጣቢያዎች እንደሚኖሩት የተነገረው የአፍሪካ ሲዲሲ በኬንያ፣ በናይጄሪያ በዛምቢያ፣ በጋቦንና በግብፅ የተለያዩ ቀጣናዎችን የሚያስተባብሩ ቢሮዎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡

ይሁንና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ በመሆኗ እንዲህ ያለ ትልቅና ተጨማሪ አኅጉራዊ ቀጣና በአዲስ አበባ ሊገነባ አይገባውም የሚሉ እንደ ሞሮኮና

 ደቡብ አፍሪካ ያሉ ተፅዕኖ ፈጣሪ አገሮችን በመጫን ውሳኔውን ለማስቀየር ጥረቶች የተደረጉ ቢሆንም፣ የአፍሪካ ሲዲሲ ማቋቋሚያ ሕግ ላይ የተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት የሚገኝበት አገር እንደሚሆን መጠቀሱ ጥረቱ እንዳይሳካ ካደረጉ ምክንያቶች አንዱ ነው፡፡ ይሁንና የኅብረቱ የመሪዎች ጉባዔ ሌላ አገር ከመረጠ የዋና መሥሪያ ቤቱ መቀመጫ ሊለወጥ እንደሚችልም ተደንግጓል፡፡

የዋና መሥሪያ ቤቱ ግንባታ እ.ኤ.አ. በ2015 እንዲጀመር ታቅዶ እነዚህን በመሳሰሉ ምክንያቶች የዘገየ ቢሆንም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬቱን አዘጋጅቶ ‹‹የአፍሪካ መንደር›› ተብሎ በሚጠራው ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ ለተቋሙ ማስረከቡም ለዚህ ፍላጎት አለመሳካት የራሱን ሚና ተጫውቷል፡፡

ይኼ የዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የቫይረሶችና ባክቴሪያዎች ላቦራቶሪ፣ ቢሮዎችና አፓርትመንቶችን የሚይዝ ሲሆን፣ የሕንፃዎቹ ንድፎች የተሠሩት ከዘረመል ማጉያ መነጽር (ማይክሮስኮፕ) ምሥልና የአፍሪካ የዕንጨት ቅርፃ ቅርፅ ጥበብ በመቅዳት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...