Saturday, July 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጃንሜዳ ጊዜያዊ አትክልት ተራ ወደ ኃይሌ ጋርመንት የማዘዋወሩ ሥራ ተጠናቀቀ

የጃንሜዳ ጊዜያዊ አትክልት ተራ ወደ ኃይሌ ጋርመንት የማዘዋወሩ ሥራ ተጠናቀቀ

ቀን:

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በጊዜያዊነት ወደ ጃንሜዳ ተዛውሮ የቆየው አትክልት ተራ በቋሚነት አገልግሎት እሚሰጥበት ወደ ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ መዛወሩንና በዛሬው ዕለት ታኅሳስ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. የማፅዳት ሥራ እንደሚከናወን የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ጃንሜዳ ለመጪው ለጥምቀት በዓል እንዲደርስ፣ ስፖርታዊና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎቶችን መስጠት እንዲችል በዛሬው ዕለት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ወጣቶች፣ የፅዳት ባለሙያዎች ጨምሮ የማፅዳትና የማሳመር ሥራ እንደሚሠሩ አስተዳደሩ ገልጿል፡፡

ኃይሌ ጋርመንት አካባቢ እየተገነባ ያለው የገበያ ማዕከል በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን የመንገድ፣ የመብራት፣ የመፀዳጃ ቤትና አስፈላጊ መሠረተ ልማቶች ዝርጋታ እየተጠናቀቀ መሆኑንም ተነግሯል፡፡

በመጠናቀቅ ላይ ያለው የገበያ ማዕከሉ ከ120 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ 3,600 ካሬ ሜትር የመኪና ማቆሚያና 300 ሜትር በ40 ሜትር ስፋት ያለው ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኝ መንገድ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካይነት በአንድ ቢሊዮን ብር ወጪ እየተገነባ ያለው የአትክልት ገበያ ማዕከል፣ 80 ሺሕ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያርፋል፡፡ በመጀመርያው ምዕራፍ የሚገነቡት 14 ሼጆች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሼዶች 70 ሜትር በ6.6 ሜትር ስፋት አላቸው፡፡ 588 የሚሆኑ የመገበያያ ሱቆችም ይኖሩታል ተብሏል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...