Friday, April 19, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የእናት ባንክ ፕሬዚዳንት ኃላፊነታቸውን በመልቀቃቸው ምክትላቸው በተጠባባቂነት ተሰየሙ

ተዛማጅ ፅሁፎች

እናት ባንክን ላለፉት ሰባት ዓመታት በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግልየ የቆዩት አቶ ወንድወሰን ከበደ ኃላፊነታቸውን መልቀቃቸው ታወቀ፡፡ ምክትላቸው ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሆነው ተሰይመዋል፡፡

አቶ ወንድወሰን ኃላፊነታቸውን የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው መሆኑን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የእናት ባንክ የዳክሬክተሮች ቦርድ ግን የመልቀቂያ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ላልተወሰነ ጊዜ በአማካሪነት እንዲያገለግሉ ያቀረበላቸውን ጥያቄ መቀበላቸውንም ለማወቅ  ተችሏል፡፡

አቶ ወንድወሰን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ለረዥም ዓመታት በማገልገል ከሚታወቁ የባንክ የሥራ መሪዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ከ40 ዓመታት በላይ በኢንዱስትሪው የቆዩት አቶ ወንድወሰን የኢትዮጵያ ልማት ባንክንና እናት ባንክን በፕሬዚዳንትነት በመምራት የሚታወቁ ሲሆን፣ በኢንዱስትሪው በቆዩባቸው 40 ዓመታት ውስጥ አብዛኛውን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ የሠሩ ናቸው፡፡

የአቶ ወንደሰን ከእናት ባንክ ፕሬዚዳንትነት መልቀቅን ተከትሎ የእናንት ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ ኤርሚያስ አንድአርጌን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት ሆነው እንዲሠሩ ሰይሟቸዋል፡፡

አዋሽ ባንክ የጨረታ ማስታወቂያ

አቶ ኤርሚያስ በእናት ባንክ ውስጥ ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በምክትል ፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ ሲሆን፣ እናት ባንክ ከመቀላቀላቸው ቀደም ብሎ በአቢሲኒያ ባንክ ውስጥ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ በአጠቃላይ ከሃያ ዓመታት በላይ በኢንዱስትሪው ውስጥ የቆዩት አቶ ኤርሚያስ እናት ባንክን በማደራጀቱ ሒደት ላይ ተሳታፊም ነበሩ፡፡

እናት ባንክ የአቶ ኤርሚያስን ሹመት ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በማቅረብ ሹመቱ እንዲፀድቅለት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እናት ባንክ ከአገሪቱ ባንኮች አደረጃጀት ለየት ባለ መልኩ የተቋቋመ ሲሆን፣ ወደ 20 ሺሕ ከሚጠጉት የባንኩ ባለአክሲዮኖች ከ65 በመቶ በላይ ሴቶች ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች