Sunday, June 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ትልልቅ ግቦችን የሚያስፈጽሙ ተቋማትን መፍጠር ለልማት ዕቅዱ ስኬት ወሳኝ መሆኑ ተነገረ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በፕላንና ልማት ኮሚሽን ተዘጋጅቶ ታኅሳስ 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚኒስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ተጨባጭ ውጤት የሚመጣው፣ ከፌዴራል እስከ ክልል ያሉ ተቋማት የልማት ግቦቹን ለማስፈጸም የሚያስችሉ ተቋማትን በመፍጠር አቅም ሲገነቡ እንደሆነ የኮሚሽኑ ኃላፊዎች አስታወቁ፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ማክሰኞ ታኅሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል ከሚዲያ ተቋማት ጋር በአሥር ዓመቱ ብሔራዊ የልማት ዕቅድ፣ ዝግጅት፣ ሒደትና በልማቱ ዕቅዱ አተገባበር ዙሪያ በሚዲያዎች ሚናና ተሳትፎ ላይ ውይይት ሲያካሂድ ነው፡፡

ውይይቱን የመሩት የፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የልማት ጥራት ዋነኛ መለኪያ የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታ መፍጠርና ዘላቂ የፋይናንስ አማራጮችን መዘርጋት በመሆኑ፣ ኮሚሽኑ ያለ ምንም የፖለቲካ ተፅዕኖ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ ዕቅድ ማዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

አዋሽ ባንክ የጨረታ ማስታወቂያ

ዕቅዱ የአንድ መንግሥት ፓርቲ ዕቅድ እንዳልሆነና ይልቁንም ከ100 በላይ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሙያና ሲቪክ ማኅበራት፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ አካል ጉዳተኞችና ሌሎችም ዜጎች፣ ሐሳባቸውንና አስተያየታቸውን ያሠፈሩበት መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ነመራ ገበየሁ (ዶ/ር) የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ናቸው፡፡

የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ ሁኔታን በመፍጠር ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብና ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ ተቋማት በለውጡ ሒደት ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው፣ ጠንካራ ተቋማት ካልተፈጠሩ አገራዊ የልማት ዕቅዱ ዕውን ሊሆን እንደማይችል ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት ብዙው የፋይናንስ እንቅስቃሴ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብቻ እንዲወሰን በመደረጉ፣ የግሉን ዘርፍ የኢኮኖሚ ሚና አቀጭጮት እንደነበር የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፣ በአዲሱ የልማት ዕቅድ ግን የግሉ ዘርፍ ከፊት የሚሠለፍበት ገበያ መር ኢኮኖሚ እንደሚገነባ ጠቁመዋል፡፡

ነመራ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በልማት ዕቅድ አተገባበር ላይ የክልልና የፌዴራል ተቋማት ተናቦ መሥራት ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህንንም በተጨባጭ ለመተግበር በቅርቡ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችንና የፌዴራል ተቋማትን የሚያገናኝ ውይይት መርሐ ግብር ኮሚሽኑ ያዘጋጃል ብለዋል፡፡

በኤልያስ ተገኝ

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች