Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ካቢኔ ተቋም የመፍጠር ፈተና

የኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ካቢኔ ተቋም የመፍጠር ፈተና

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሰኞ ታኅሳስ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ባካሄደው ጉባዔ ለቀጣዮቹ አራት ዓመታት ፌዴሬሽኑን የሚያስተዳድሩ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን አስመርጧል፡፡ የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና ካቢኔያቸው አትሌቲክሱ የኅብረተሰቡን ፍላጎት ባስጠበቀ መልኩ ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የሚያስችል ብሔራዊ ተቋም የመፍጠር ቁመና ሊኖረው ይገባል ተብሏል፡፡

ለሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት የተመረጡት አትሌት ገዛኸኝ አበራና ወ/ሮ ሰሃራ ሐሰን ከኦሮሚያ፣ ወ/ሮ አበባ ዮሴፍና አቶ በላይነህ ክንዴ ከአማራ፣ በዛብህ ወልዴ (ዶ/ር) እና ወ/ሮ ትልቅሰው ገዳሙ ከአዲስ አበባ፣ አቶ ተፈራ ሞላ ከደቡብና ወ/ሮ ፎዚያ እንድሪስ ከአፋር አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ናቸው፡፡

በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወቅትንና ጊዜውን የሚመጥን ተቋማዊ ቁመና በመፍጠር ረገድ አሁንም ብዙ እንደሚቀረው የሚናገሩ አሉ፡፡ ለዚህ ችግር በዋናነት ማሳያ ተደርጎ የሚቀርበው ክለቦች በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ መድረክ ላይ በተወካይ ካልሆነ ምንም ዓይነት ድምፅ የላቸውም የሚለው አንደኛው ሲሆን፣ ሌላው ደግሞ የአትሌት ማናጀሮችና የክለቦች ግንኙነት ምንም ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ ያልተበጀለት መሆኑ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ መነሻነት በ24ኛው የኢትዮጰያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጉባዔ ላይ የተሳተፉ የአዲስ አበባ ክለቦች ተወካዮች፣ ክለቦች ለአትሌቶችና ለአሠልጣኞ በጀት ከመመደብ ባለፈ አንዳችም ጥቅም እንደማያገኙ አስታውቋል፡፡ የአትሌት ማናጀሮችና የክለቦች ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት በሕግ ተደንግጎ መቀመጥ ሲገባው ባለመቀመጡ ክለቦች በአትሌቶቻቸው ማዘዝም ሆነ መወሰን እየቻሉ አይደለም፡፡

አትሌቶችን በፈለጉት ጊዜና ሰዓት ማግኘትም ሆነ ማዘዝ የሚችሉት የአትሌት ማናጀሮች ብቻ ናቸው፡፡ ክለቦች በጀት ይመድባሉ፣ አሠልጣኝና አትሌት ይቀጥራሉ ሠልጣኞች ለዕውቅና ሲበቁ ያሳደጋቸውን ክለብ ዞር ብለው አያዩትም፡፡ በዚህ የተነሳ የበርካታ ክለቦች ህልውናና ቀጣይ ዕጣ ፈንታ አሳሳቢ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በመሆኑም ብለው ጉባዔው ለዚህ ችግር የመፍትሔ አቅጣጫ ሊያስቀምጥ እንደሚገባ ሲያሳስቡ ተደምጠዋል፡፡

የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉና የጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ቢልልኝ መቆያ የክለቦቹ ተወካዮች ላቀረቧቸው ቅሬታዎች የሰጡት መልስ፣ የክለቦቹ ጥያቄ አግባብነት ያለው በመሆኑ ጉዳዩ በሒደት ታይቶ ምላሽ እንደሚያገኝ ነው፡፡

ጉባዔው ከተጠናቀቀ በኋላ ሪፖርተር በዚህ ጉዳይ ካነጋገራቸው የጉባዔው አባላት አንዳንዶቹ፣ ክለቦቹ የሚያነሱት ፍትሐዊ ጥያቄ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ የኮማደር ደራርቱ ቱሉ አዲሱ ካቢኒ በተለይ ተቋም ለመፍጠር በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ  ትልቅ ፈተና ከሚሆኑበት ተግዳሮቶች አንዱና ዋነኛው ይህ ጉዳይ እንደሚሆንም ይጠቁማሉ፡፡ አሁን ላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዕድገት ዓይነተኛ ሚና እንዳላቸው ከሚታወቁ ትልልቅ ክለቦች ውስጥ አንዳንዶቹ በመኖርና ባለመኖር ሲንገዳገዱ መታየታቸውንም ለአብነት ያነሳሉ፡፡

ከዚህ በተጓዳኝ ከጉባዔው ተሳታፊዎች ብዙዎቹ ሲያነሱት የነበረው ጉዳይ የኢትዮጵያ አትሌቲከክስ ፌዴሬሽን ስለሚያደርግላቸው ድጎማ ማነስ ነው፡፡ ክለቦቹም ሆነ አትሌቲክሱ ወቅቱንና ጊዜውን የሚመጥን አደረጃጀት ይኖራቸው ዘንድ ስትራቴጂካዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሲያደርጉ አልታዩም፡፡

በጉባዔው የመናገር ዕድል ያገኙት ብዙዎቹ ተሳታፊዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ‹‹የባዶ እግር ቱሩፋቶች›› በሚል ከሜልቦርን እስከ ሪዮ ዴጀኔሮ ኦሊምፒክ የተሳተፉ አትሌቶች እንዲታሰቡ ያደረገበት መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡  

በሌላ በኩል ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ እንደሚያደርገው ሁሉ ዘንድሮም በውድድር ዓመቱ ውጤታማ ለሆኑ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ክለቦች ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል፡፡ በዚሁ መሠረት የኦሮሚያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 240 ሺሕ፣ የአማራ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 180 ሺሕ፣ የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 140 ሺሕ፣ ለደቡብ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 100 ሺሕ፣ ቤንሻንጉል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 80 ሺሕ፣ ሐረሪ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 60 ሺሕ፣ ድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 40 ሺሕና ጋምቤላ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 20 ሺሕ ብር ለግሷል፡፡

ከክለቦች መከላከያ 300 ሺሕ፣ ፌዴራል ፖሊስ 240 ሺሕ፣ ጥሩነሽ ዲባባ 180 ሺሕ፣ ኦሮሚያ ፖሊስ 140 ሺሕ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 100 ሺሕ፣ ደቡብ ፖሊስ 80 ሺሕ፣ ሲዳማ ቡና 60 ሺሕና የኦሮሚያ ውኃ ሥራዎች ክለብ 40 ሺሕ ብር ለግሰዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...