ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን በትግራይ ርዕሰ መዲና መቀሌ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች ጋር ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ‹‹ይህ ጀግና የመከላከያ ሠራዊት የብልፅግና ሠራዊት አይደለም። ይህ ሠራዊት የዓብይ ሠራዊት አይደለም፤›› ብለው፣ ‹‹ይህ ሠራዊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ኩራትና መከታ የሆነ የኢትዮጵያ ሠራዊት ነው፡፡ እኛ ከእናንተ የምንፈልገው ፕሮፌሽናልና ጠንካራ ኃይል እንድትሆኑ እንጂ፣ ለአንድ ፓርቲ የምትወግኑና የምትገዙ እንድትሆኑ አይደለም፡፡ ትናንት የነገርኳችሁን አሁንም እደግምላችኋለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከብልፅግና በላይ ናት። ከፓርቲ በላይ ናት። ትልቋን አገር የመታደግ ኃላፊነት ተጥሎባችኋል፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡