Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊኢትዮጵያ በዕርዳታ ከሚቀርበው አንድ ቢሊዮን የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት ተጠቃሚ እንደምትሆን ተገለጸ

ኢትዮጵያ በዕርዳታ ከሚቀርበው አንድ ቢሊዮን የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት ተጠቃሚ እንደምትሆን ተገለጸ

ቀን:

አቅም ለሌላቸው የዓለም አገሮች የሕክምና ክትባቶችን በዕርዳታ የሚያቀርበው ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት፣ በዕርዳታ ለማቅረብ ካቀደው አንድ ቢሊዮን የኮሮና መከላከያ ክትባት ኢትዮጵያ ተጠቃሚ እንደምትሆን አስታወቀ። 

ኮቫክስ የተባለው ዓለም አቀፍ ጥምረት ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ፣ በአሁኑ ወቅት እየተመረቱ የሚገኙትና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ክትባቶች ሥርጭት ያለ መድልኦ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው አገሮችም ሊደርሱ እንደሚገባ አስታውቋል።

ፍትሐዊ የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት ሥርጭት እንዲኖርም ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላላቸው 92 የዓለም አገሮች፣ አንድ ቢሊዮንመከላከያ ክትባቶችን በዕርዳታ እንደሚያቀርብ ጠቁሟል፡፡

የክትባት ዕርዳታውን ከሚያገኙ አገሮች መካከልም ኢትዮጵያ አንዷ እንደምትሆን፣ ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት ለሪፖርተር ያደረሰው መረጃ ያመለክታል። 

በዚህ ጥምረት ውስጥ በርካታ የአውሮፓ አገሮች የገንዘብ ዕርዳታ በማድረግ ተሳታፊ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የዓለም የጤና ድርጅት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት መርጃ (ዩኒሴፍ)፣ የዓለም ባንክ፣ ክትባቶቹን በማምረት ላይ የሚገኙ የክትባት ኢንዱስትሪው ተቋማት፣ የግንባር ቀደሙ ቢሊየነር ቢል ጌትስ ፋውንዴሽን ቢልና ሚሊንዳ ጌትስና የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡

ኮቫክስ በተባለው ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካይነት የሚቀርበውን የኮሮና ወረርሽኝ ክትባት ከአምራቾች ገዝተው ለተመረጡት 92 አገሮች እንዲያሠራጩም፣ ዩኒሴፍና ፓን አሜሪካን የጤና ድርጅት ተመርጠዋል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ 92 አገሮች በዕርዳታ ከሚቀርበው የኮሮና መከላከያ ክትባት ውስጥ፣ ለቫይረሱ በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ የኅብረተሰብ ክፍሎችና ቫይረሱን በመከላከል የሥራ ዘርፎች ግንባር ቀደም ሠራተኞች የሆኑ የጤና ባለሙያዎች በቅድሚያ ተጠቃሚ እንደሚሆኑም ተገልጿል።

የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (/) ኮቫክስ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት በዕርዳታ ከሚያቀርበው ክትባት መጠቀም እንድትችል በኢትዮጵያ በኩል ጥያቄ መቅረቡን ያረጋገጡ ሲሆን፣ ክትባቱ ሲቀርብም በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በዕርዳታ የሚቀርበውን አንድ ቢሊዮን ክትባት ለመግዛት የሚያስፈልገውን ወጪ ለመሸፈን ጥምረቱ ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ ሲሆን፣ ሰሞኑን በጥቅሉ 850 ሚሊዮን ዶላር ከአውሮፓ ኅብረት አባል አገሮች፣ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክና ከአውሮፓ ኅብረት ኮሚሽን ማግኘቱ ተገልጿል።

የኮሮና ወረርሽኝ መከላከያ ክትባትን ለመውሰድ በአፍሪካ አኅጉር ያለው ፍላጎት ምን እንደሚመስል ለማወቅ በአፍሪካ የበሽታ መከላከያ ማዕከል በሆነው Africa CDC አማካኝነት የዳሰሳ ጥናት ያከናወነ ሲሆን በዚህም ኢትዮጵያን ጨምሮ በ15 የአፍሪካ አገሮች ላይ ጥናቱ ተከናውኗል።

በጥናቱም ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ከ15 ሺሕ በላይ ወካይ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተጠይቀው መረጃ ሰጥተዋል። በውጤቱም አትዮጵያዊያን ክትባቱን ለመውሰድ ከሌሎቹ የአፍሪካ አገሮች የተሻለ ፍላጎት እንዳሳዩ ማዕከሉ ሰሞኑን ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ 94 በመቶ ክትባቱን የመውሰድ ፍላጎት መኖሩ በጥናቱ የተረጋገጠ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ ቀጥሎ 93 በመቶ ናይጄሪያዊያን ክትባቱን ለመውሰድ ፍላጎት አሳይተዋል።  በሴኔጋል ያለው ፍላጎት 65 በመቶ ሲሆን፣ በዴሞክራቲክ ኮንጎ ያለው ፍላጎት ደግሞ 59 በመቶ እንደሆነ መረጃው ያሳያል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...