Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአማራ ክልል መንግሥት በመተከል የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ

የአማራ ክልል መንግሥት በመተከል የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ለፌዴራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ

ቀን:

በቤንሻንጉል ጉሙዝ  ክልል መተከል  ዞን  በአማራ  ተወላጆች ላይ እየተፈጸመ ያለውን  ዘርን መሠረት ያደረገ ጭፍጨፋ፣  የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነና ማስቆም ካልቻለ፣ የአማራ ክልል መንግሥት ጥቃቱን ለማስቆምና ለማስከበር ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፣ ይሁንታን ለማግኘት ሐሳብ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

‹‹በመተከል ዞን እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ የቤንሻንጉል ክልል ባለሥልጣናት ቀን ቀን ስብሰባ ላይ ከእኛ ጋር ሲላቀሱ ይውላሉ፡፡ ማታ ማታ ግን ግድያውን ማስቆም አልቻሉም፤›› በማለት የተናገሩት የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ናቸው፡፡

bidreporter

በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ ዘር እየተመረጠ በየትኛውም ዓለም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ዘግናኝና ጭካኔ በተሞላበት ድርጊት ሰዎች ሲገደሉ፣ የፌዴራል መንግሥት ግዴታና ኃላፊነቱን ካልተወጣ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃይል ዝግጁ እንደሆነ ኮሚሽነር አበረ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ኮሚሽነሩ  የችግሩን ቀጣይነት አስመልክተው ሲያብራሩ፣ ከአካባቢው አመራሮች ጋር በተደጋጋሚ ውይይት የተደረገ ቢሆንም፣ ‹‹የችግሩ መንስዔዎች ቀን ቀን አብረውን ስብሰባ ላይ ሲላቀሱ ውለው፣ ማታ ግድያውን ማስቆም የተሳናቸው የሕወሓት ርዝራዦች ናቸው፤›› ብለዋል።

‹‹አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የሚገደሉት አማራ ተብለው ስለሆነ ምናልባት የፌዴራል መንግሥት ሥራ በዝቶበት ከሆነ፣ ለእኛ ይስጠን ብሎ ክልሉ ለፌዴራል መንግሥት ሐሳብ አቅርቧል፤›› ሲሉ ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።

አንድ ክልል የራሱን የፀጥታ ችግር ማስከበር ካልቻለ የፌዴራል መንግሥት ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ያሉት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹አቅጣጫ ያስቀምጥልን፣ ሕዝባችን እንታደግ፤›› ሲሉም የፌዴራሉን መንግሥት ጠይቀዋል።

‹‹እንደ ክልል ልናደርግ የምንችለው ወደ ፌዴራል መንግሥት አቤት ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አሁንም በአማራ ክልል በኩል የሕዝብን ደኅንነት ለማስጠበቅ ዝግጁ ነን፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ከፈቀደ ‹‹የአማራ ክልል የአቅም ውስንነት የለበትም›› ያሉት ኮሚሽነር አበረ፣ በሕወሓት ኃይሎች ላይ እንደተደረገው ዘመቻ ከመከላከያ ጋር በመሆን ሥራውን ለማከናወን ፍላጎት እንዳለ ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ሁሉም ኢትዮጵያዊ  ማንም  ይሁን ማን፣ በየትኛውም ቦታ እኩል የመኖር መብት አለው ብለዋል። ‹‹ነገር ግን በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ ያሉ የወያኔ ተላላኪዎች ሰው ሲገደል ከመከላከል ይልቅ፣ ለምን ተገደለ ብላችሁ ጠየቃችሁን ብለው ያኮርፋሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት አካላት የተሰባሰቡበት የአመራር ቡድን በመሆኑ የሰውን ሕይወት ለመታደግ ሲሠሩ አይታዩም፤›› ብለዋል።

 የአማራና የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በጉዳዩ ላይ እየመከሩ እንደሆነ የገለጹት ኮሚሽነሩ፣ ‹‹ለችግሩ መፍትሔ ያመጣሉ ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን እንደ ክልል የፀጥታ ኃይል ትዕዛዝ እየተጠባበቅን እንገኛለን፤›› ብለዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...