Sunday, June 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የኢትዮጵያ ባንኮች የተበላሸ ብድር ምጣኔ አነስተኛ መሆኑ ተጠቆመ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ የተበላሸ ብድር መጠን ዝቅተኛ መሆኑና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተጠቆመ፡፡ በትርፋማነትም ከብዙ አገሮች ብልጫ እንዳለው ተገልጿል፡፡

ታዋቂ የኢኮኖሚ ባለሙያ ዓለማየሁ ገዳ (ፕሮፌሰር) ሰሞኑን ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ፣ ኢትዮጵያ ከተሰብሳቢ ብድር አንፃር የተሻለ አፈጻጸም ያላት ስለመሆኑ አመላክተዋል፡፡

እንደ ዓለማየሁ (ፕሮፌሰር) ገለጻ ኢንዱስትሪው ከአፍሪካዊ አቻዎቹ አንፃር ሲታይ በእጅጉ የተሻለ ነው፡፡ ሆኖም ስለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ60 በመቶ በላይ አገልግሎቱና እንዲሁም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራላይዞች የሚያቀርቧቸው ብድሮች የብድር ፖሊሲያቸው ለአሠራር ሥጋቶች የተጋለጡ ስለመሆናቸው ግን ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

ከካፒታል ትርፋማነት አንፃርም የኢትዮጵያ ባንኮች የትርፋማነት ምጣኔ 24 በመቶ ሲሆን፣ ይህም 21 በመቶ ከሆነው ከአማካይ የአፍሪካ ባንኮች ምጣኔ አንፃር ሲታይ በመጠኑ ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በኢትዮጵያ የሊክዊዲቲ ምጣኔውም በጥቅሉ በአበረታች አቋም ላይ የሚገኝ መሆኑን የገለጹት ፕሮፌሰሩ፣ የሀብት ምጣኔው ከጠቅላላው ተቀማጭ 17 በመቶ ገደማ እንደሚሆንም አመልክተዋል፡፡

አፍሪካዊ ባንኮች ባለቤትነትና ውጤታማነትን በተመለከተም የፕሮፌሰሩ ምልከታ፣ የታላላቅ የውጭ አገር ባንኮች ተሳትፎ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ፋይናንስ በማድረግ በኩል ያላቸውን ከፍተኛ የተደራሽነት አስተዋጽኦ ጠቁመው፣ የውጭ ባንኮች በሀብታቸውና በቅርንጫፎቻች መጠን የገዘፈ ተፅዕኖ በኢንዱስትሪው ላይ በማሳረፍ፣ ጤናማ ያልሆነ ውድድር እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡ ዘርፉንም ሆነ ተበዳሪዎችን በሚመለከት ተጨባጭና ረቂቅ መረጃዎችን በማግኘት አቅም ያላቸው የውጭ ባንኮች በተበዳሪዎች በመልቀም ነፃ ተወዳዳሪነትን የሚረብሽ አቅጣጫዎችን እንዲከተሉ እንደሚያደርግም አክለዋል፡፡ ይህም አቅማቸው ያነሰውን የአገር ውስጥ ባንኮች የብድር ሥርዓት በእጅጉ ተጎጂ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል፡፡ የውጭ ባንኮች ተሳታፊነት የዘርፉን የውድድር መጠን ያሳድጋል ወይም ይጎዳል ብለው ለመደምደም ግን የሚቸገሩ መሆኑን ፕሮፌሰሩ ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡

ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮች የአገልግሎት ወጪ በአጠቃላይ የባንኮች ሀብት ረገድ ያለው ምጣኔ 5.4 በመቶ ሲሆን፣ ከሰሜን አፍሪካው 1.7 በመቶ ምጣኔ ጋር ሲነፃፀር ውጤታማነታቸው በእጀጉ አናሳ መሆኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች