Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለምርጫ ሰነዶች ቁሳቁስ ጥበቃና አጠቃቀም መመርያ አስተያየት መቀበል ተጀመረ

ለምርጫ ሰነዶች ቁሳቁስ ጥበቃና አጠቃቀም መመርያ አስተያየት መቀበል ተጀመረ

ቀን:

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ የሚውሉ የምርጫ ማስፈጸሚያና የድምፅ መስጫ መሣሪያዎች፣ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ድልድል፣ ሥርጭት፣ አጠቃቀም፣ ርክክብና አወጋገድ ረቂቅ መመርያ አሰናድቶ ከሚመለከታቸው አካላት አስተያየት ለመሰብሰብ የአንድ ሳምንት ጊዜ ሰጠ፡፡ ከሰኞ ታኅሳስ ጀምሮ አስተያየት መቀበል መጀመሩን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

መመርያው ‹‹ለምርጫ ማስፈጸሚያ የሚውሉ ሰነዶችና ቁሳቁስ ልዩ ጥንቃቄና ጥበቃ፣ እንዲሁም ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው›› በማለት ከፋፍሏቸዋል፡፡ ሰነዶቹንና ቁሳቁሶችን በምርጫ ሒደት የሚረከብ ማንኛውም ሰው በማጓጓዝም ሆነ በማከማቸት ጊዜ ኃላፊነት እንደሚኖርበት፣ የርክክብ ክፍተት ሳይኖር እንዳይጓጓዙ ሲል ያስገድዳል፡፡

 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

መመርያው ልዩ ጥንቃቄ የሚያስፈልጋቸው ያላቸው ሰነዶች የመራጮች መዝገብ፣ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድና የመራጮች መመዝገቢያ መዝገብ፣ የምርጫ ኮሮጆ ወይም የምርጫ ሳጥኖች፣ የድምፅ መስጫ ወረቀት፣ የምርጫ ኮሮጆ መቆለፊያ (ማሸጊያ) ቁልፎች፣ ማኅተሞችና መርገጫዎች፣ የማይለቅ የመራጭነት ምልክት ማድረጊያ ቀለም፣ ማናቸውም መረጃ ተሞልቶባቸው የተፈረሙና ማኅተም የተደረገባቸው ፎርሞች፣ የውጤትና የማዳመሪያ ቅጾች፣ እንዲሁም ከተከፈቱ መከፈታቸው የሚያስታውቁ መያዣዎች ናቸው፡፡

ጥበቃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው የሚላቸው ደግሞ የሥነ ዜጋና የመራጮች ትምህርት መስጫ ሰነዶች፣ ለምርጫ አስፈጻሚ፣ ለዕጩ ወኪል፣ ለታዛቢና ለጋዜጠኛ የሚያዘጋጀው መታወቂያ ወይም ባጅ፣ የዕጮዎች የምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የዕጩ ወኪሎች ዝርዝር፣ የምርጫ ሕግ አዋጅ፣ ደንቦችና መመርያዎች፣ የምርጫ ማስታወቂያ፣ ለሥነ ዜጋና ለመራጮች ትምህርት አገልግሎት የሚውል ቴፕ ሪከርደር ወይም ሬዲዮ ወይም ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ ናቸው፡፡ እንዲሁም ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ወጪዎች መመዝገቢያነት የሚያገለግሉ የሒሳብ መዝገብና  ደረሰኞች፣ የምርጫ መሣሪያዎች፣ ሰነዶች ወይም ቁሳቁስ መረካከቢያ ደረሰኝ ወይም ሰነድ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዕጩ ወኪሎች የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብን ስለማክበርና  ማስከበራቸው ፊርማቸውን የሚያኖሩበት ሰነድ፣ ዕጩዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን የሚያስተዋውቁባቸው ፖስተሮች፣ በየደረጃው ያሉ የምርጫ አቤቱታ ሰሚ ኮሚቴዎች አቤቱታ የሚቀበሉበትና መልስ የሚሰጡበት ያልተሞላ፣ ማኅተም ያልተደረገበትና ያልተፈረመበት ቅጽ፣ የምርጫ አፈጻጸም ማስታወቂያ ፖስተሮች፣ ፖስት ካርዶች ወይም በራሪ ጽሑፎች፣ አስክሪቢቶዎችና እርሳሶች፣ ጊዚያዊ ድምፅ የተሰጠባቸው የምርጫ ወረቀቶች ማስቀመጫ ፖስታ፣ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ መሣሪያዎችና ሌሎች አስፈላጊ የምርጫ ሰነዶችና ቁሳቁስ እንደሆኑም ይዘረዝራል፡፡

‹‹የድምፅ መስጫ ወረቀቶች፣ የውጤት መረካከቢያ ቅጾች፣ ቃለ ጉባዔዎችና ሌሎች በምርጫው ሒደት በሥራ ላይ የዋሉ ሰነዶች መወገድ ያለባቸው የምርጫው ሒደት ከተጠናቀቀ፣ ማናቸውም በምርጫ ሒደትና ውጤቱ ላይ የተነሱ አስተዳደራዊ ወይም ሕጋዊ የአቤቱታ ሒደቶች ከተቋጩ፣ ድጋሚ ቆጠራ እስከ መጨረሻው ደረጃ ከተጠናቀቀና የምርጫ ውጤቱ መጨረሻ መሆን ሲረጋገጥ ብቻ ነው፤›› በማለት መመርያው የሚያብራራ ሲሆን፣ ከዚህ ውጪ ከምርጫው ዕለት ጀምሮ አንድ ዓመት እስኪያልፍ ተመሳሳይ የማስወገድ ሥራ ሊከናወን እንደሚችል ይጠቁማል፡፡

እነዚህ ቁሳቁስና ሰነዶች አካባቢን ሳይጎዱ በመልሶ መጠቀም ሒደት ወይም በሌላ አመቺ በሆነ መንገድ፣ በቦርዱ ጥብቅ ክትትል ይወገዳሉ ሲልም ረቂቅ መመርያው ይደነግጋል፡፡

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን አገራዊ ምርጫ ለማካሄድ የተለያዩ ዝግጅቶችን እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...