Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሚኒስትሮች ምክር ቤት የካፒታል ገበያ ረቂቅን ጨምሮ ሦስት አዋጆች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ...

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካፒታል ገበያ ረቂቅን ጨምሮ ሦስት አዋጆች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ ለፓርላማ መራ

ቀን:

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅ፣ የተቀማጭ ገንዘብ መድኅን ፈንድና የመከላከያ ሠራዊት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ በማፅደቅ ለፓርላማው መርቶታል፡፡

ምክር ቤቱ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ፣ ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት ብልፅግና በጣም አስፈላጊ ነው ያለውን የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅ አፅድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል፡፡

የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጁ ፀድቆ ወደ ሥራ ሲገባ በኅብረተሰቡ አማራጭ የቁጠባ መንገዶችን በማቅረብ የኢኮኖሚውን የፋይናንስ ቁጠባ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ በዚህም ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥ ቁጠባ ፋይናንስ እንዲደረግ በማድረግ ከውጭ ያለውን ጥገኝነት እንደሚቀንስ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈ የካፒታል ገበያ የአገሪቱን የክፍያ ሚዛን በማስተካከል ለማክሮ ኢኮኖሚው መረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም ተገልጿል፡፡

ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ በባንኮችና በኢንቨስትመንት የፋይናንስ ተቋማት ገንዘብ የሚያስቀምጡ አካላትን ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዳ፣ የኢትዮጵያ የተቀማጭ ገንዘብ መድኅን ፈንድ ለማቋቋም በወጣ ረቂቅ ደንብ ላይ መወያየቱን ታውቋል፡፡  

የገንዘብ አስቀማጩን ጥቅም ለመጠበቅ መንግሥት በፋይናንስ ተቋማቱ ላይ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡

በዚህም ጠንካራ የፋይናንስ ቁመና ያለው ግልጽ የተቀማጭ ገንዘብ መድኅን ሥርዓት በተፋጠነ ሁኔታ ብዛት ላላቸው አስቀማጮች ገንዘባቸውን በመመለስ፣ በፋይናንስ ሥርዓቱ ላይ ያለው የሕዝብ አመኔታ እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል የመከላከያ ሠራዊትን አደረጃጀትን፣ አሠራርና ዘመኑን ባገናዘበ ሁኔታ ዘመናዊ በሆነና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን የበለጠ ለማምጣት ያስችላል የተባለውን፣ የመከላከያ ሠራዊት አዋጅ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ለፓርላማ ልኳል፡፡

ሪቂቅ አዋጁ ሠራዊቱ እናት አገሩን አሁን ካለው በበለጠ ዘመን ሊያገለግል የሚችልበትን ዕድል መፍጠርና አገሪቱ ወጪ አውጥታና ጊዜ ወስዳ ያሠለጠነቻቸውና ለግዳጅ ያሰማራቻቸው የመከላከያ አባላት፣ ብቁና ዘመኑን የሚመጥኑ እስከሆኑ ድረስ በሠራዊቱ ሊኖራቸው የሚገባውን የአገልግሎት ዘመን እንደገና ለመፈተሽና ለማየት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የሠራዊት አባላቱና ኃላፊዎች ልዩ የማዕረግ ዕድገትና ሽልማት ሊያገኙ የሚችሉበት አዳዲስ አሠራሮችን ያካተተ ረቂቅ አዋጅ መሆኑ ተመላክቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...