Monday, July 22, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ለሚሰማሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር 5.5 ቢሊዮን ብር ተመደበ

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከዓለም ባንክ በተገኘ 5.5 ቢሊዮን ብር ድጋፍ በአገር አቀፍ ደረጃ በአነስተኛና በመካከለኛ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለሚሰማሩ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በዝግጅት ላይ መሆኑን፣ የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ይህንን ያለው ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡ በወቅቱም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አመራሮች፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓት አቅራቢ ድርጅቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔዎችና ሌሎች ተቋማት በተገኙበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አስፋው አበበ እንደተናገሩት፣ በአገሪቱ 20 ሺሕ የሚሆኑ አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች ይገኛሉ፡፡ እነዚህን አምራቾች ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ዘላቂ የሆነ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የሚሠራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

https://www.reportertenders.com/article/7095

ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥረው ይህ ፕሮጀክት፣ ከዚህ በፊት የተጀመሩና የተስተጓጎሉ ነገሮች ተስተካክለው፣ በተሳካ ሁኔታ የሚቀጥሉበት መንገድ የሚያመቻች መሆኑን አክለዋል፡፡

ከዚህ በፊት ይደረግ የነበረው ድጋፍ ጥናት ላይ ያልተመሠረተና ቅንጅታዊ አሠራር ያልታየበት በመሆኑ፣ ከዘርፉ ሊገኝ የሚገባውን ውጤት ማግኘት አለመቻሉን አቶ አስፋው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የተገኘውን የገንዘብ ድጋፍ በመጠቀም ትክክለኛ ፍላጎታቸውን አቅርበው ወደ ሥራ ዘርፉ ውስጥ መግባት የሚችሉበት መንገድ የተመቻቸ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአገሪቷ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥ ችግር በመኖሩ የሚፈለገውን ያህል ዘላቂ የሆነ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚቻለው የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ላይ በመሥራት፣ እንዲሁም የፋይናንስ፣ የግብዓት፣ የማምረቻ ቦታ ይዞታ ለሥራ አጦች በማሟላት ጭምር ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ሥራ አጥነትን ለመቀነስና ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ መሠረት መጣል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

ለአነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ተብለው የሚቀርቡ የመሥሪያ ቦታ፣ የግብዓትና የብድር አቅርቦት ለሌላ ዓላማ የሚያውሉ ተቋማትን በመለየት በዘርፉ ላይ መሥራት ያስፈልጋል ሲሉ ምክትል ከንቲባዋ አስረድተዋል፡፡

በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የከተማ አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአነስተኛና መካከለኛ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድጉ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል የመሠረተ ልማትና የጥሬ ዕቃ ግብዓት እጥረት መኖር፣ እንዲሁም የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ችግር መስተዋሉ መሆኑ በውይይቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች