Saturday, December 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየበይነ መረብ ልመና

የበይነ መረብ ልመና

ቀን:

እንደተለመደው የገጽ ለገጽ ልመና ወይም በአካል ቦታው ተገኝቶ መለመን የማይጠበቅበት የልመና ዓይነት ብቅ ማለት ከጀመረ ሰንብቷል፡፡ በማኅበራዊ ትስስር ገጽ በሚደረግ ልመናና በሚቀመጥ የባንክ ደብተር ቁጥር ብዙዎች ተረድተው ብሎም ከችግራቸው ወጥተው ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ እከሌ ታሟል ብሎ ከእነ ፎቶውና አድራሻው መለጠፍ፣ እከሌ ቤቱ በላዩ ላይ ሊፈርስ ነው ብሎ የዕርዳታ ጥሪ መለጠፍና እንዲረዱ ማድረግ ተለምዷል፡፡ ቴክኖሎጂው መርዳት ለሚገባቸው ሰዎች ለመድረስ ዕድል ቢፈጥርም በዚያው ልክ ለማታለል ብቻ የሚደረጉ ልመናዎችም አሉ፡፡

ከማኅበራዊ ትስስር ገጽ ለልመና አመቺ የሆነው ፌስቡክ አካውንት የሚከፈተው በመልከ መልካም ሰዎች ፎቶዎች አማካይነት ነው፡፡ እነዚህ አካውንቶችን ሌሎች የሚደምሯቸው የጓደኛ ጥያቄው ሲመጣ የጋራ ጓደኞቻቸውን ብዛት ማየት እንጂ መግለጫቸውን በመመልከት እንዳልሆነ ያነጋገርናቸው ነግረውናል፡፡

የበይነ መረብ ልመናው ከመደረጉ በፊት ተመፅዋቹ ሰጪውን ግለሰብ በሳቢ አጻጻፍ በደንብ ይግባባሉ፡፡ ልመናውን የሚጀምሩትም ከፌስቡክ ጓደኛቸው ጋር ከተግባቡ በኋላ ነው፡፡ በፌስቡክ ጓደኛቸው ከተላከላቸው የልመና መልዕክት ረድተው በምላሹም ጓደኛ የተባሉት የጠፉባቸው ግለሰብ እንደነገሩን በመልከ መልካም ሴትና ወንድ ከተከፈቱ የፌስቡክ ገጾች አንዳንዶቹ በወንድ ፎቶ የከፈቱት ሆነው ግን ሴት ሆኗ የምትገኝበት እንዲሁም በሴት ተከፍቶ ወንድ ሆኖ የሚገኝበት አጋጣሚ የጎላ ነው፡፡

ከተሳካላቸው በባንክ አካውንት ገንዘብ እስከማስላክ የሚደርሱም አሉ፡፡ በዚህ ሥልት ገንዘብ የሚልኩት፣ ‹‹እኔ የባንክ አካውንት የለኝም በዘመድ አካውንት ላኪ ወይም ላክ፤›› በማለት ልመናቸውን ገንዘብ የማግኛ ሥልታቸው ማዘመን የሚቀጥሉ እንዳሉ የደረሰባቸው ሰዎች ነግረውኛል፡፡ ገንዘቡን ካገኙ በኋላ ደብዛቸው እንደሚጠፋ ይጠቁማሉ፡፡ ይህ ሲሆን ታዝበው ዝም ከማለት በዘለለ ምንም እንዳላሉም ነግረውናል፡፡

ከባንክ ከማስላክ ጎን ለጎን ሞባይል ካርድ ሙሉልኝ የተለመደ ነው፡፡ መፅዋቹ በዚህም እጅ ካልሰጠ የድምፅ መልዕክት ጽሑፍ፣ ኢንተርኔት ፓኬጅ እንዲሞሉ ተማፅኖ ይቀርብላቸዋል፡፡

በበይነ መረብ በሚደረገው የምፅዋት ጥየቃ አንዳንዶች ልብ በሚነካ አጻጻፍ ይሳተፋሉ፡፡ ሙሉ ስም፣ የባንክ ደብተር ቁጥር ሁሉ ያስቀምጣሉ፡፡ በሚከፈተው የባንክ አካውንት የሚልከው ግለሰብ በተግባቦትና በብዙ ቀረቤታ በመሆኑ በማፈር ወደ ሕግ ከመሄድ ይልቅ መተውን ይመርጣሉ፡፡ 

የበይነ መረብ ምፅዋት ለበጎ ተግባር

በበይነ መረብ ልመና የዘመነና ሳቢ በሆነ መንገድ የሚደረግ ነው፡፡ በዚህ ልመና የሚሳተፉ ሰዎች በሁለት መልኩ መመልከት ያስችላል፡፡ የመጀመርያዎቹ ለማጭበርበርና ለማታለል የሚደረጉ ሲሆን፣ አሁን ላይ እየተበራከተ ያለው ደግሞ በበይነ መረብ ምፅዋት በመጠየቅ ለበጎ ነገር የሚያውሉም አሉ፡፡

በኢትዮጵያ በሚከሰቱ የተለያዩ ግጭቶችና መፈናቀሎች ለሚጎዱ ዜጎች፣ ለታመሙ፣ ለተቸገሩ፣ ቤት ለፈረሰባቸው የሚለምኑ ብዙ ወጣቶች አሉ፡፡ እነዚህ ወጣቶች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚገኘውን ገንዘብ ለዜጎች በማድረስ ግዴታቸውን ይወጣሉ፡፡ በምሳሌነት ከሚጠቀሱት ውስጥ ያሬድ ሹመቴና ጓደኞቹ በግንባር ቀደምነት ስማቸው ይጠቀሳል፡፡ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ ሳቢያ በሚከሰቱ አደጋዎች ለተጎዱ የተለያዩ ምግብና አስፈላጊ ነገሮች ለማድረስ በይነ መረብን ይጠቀማሉ፡፡  

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች አጋርነታቸውንና አብሮነታችን አንፀባርቀዋል፡፡ በበይነ መረብ የሚደረገው ልመና ብዙ አይነገርለት እንጂ የብዙዎችን ሕይወትም ቀይሯል፡፡ የብዙ እናቶች፣ ወጣቶች፣ ሕፃናት ሕይወት በዚሁ መገናኛ መስመር ተቀይሯል፡፡

ከአገር ውጭ ሆነው ኢትዮጵያውያንን የሚረዱና የሚያግዙ ሰዎች እንዲሁ በበይነ መረብ በሚደረግ የእርዳታ (የልመና) ጥሪ ነው፡፡ በሶማሌ፣ በጌዴኦና ጉጂ፣ በመተከል፣ በቡራዩ አካባቢ ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ዜጎች ምግብን፣ አልባሳትና ሌሎችም ዕርዳታዎች በእነዚህ በጎ አሳቢ ወጣቶች ምክንያት ደርሷቸዋል፡፡ የዚህ የበይነ መረብ ምፅዋት በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ተወላጆች ጭምር ያሳተፈ ነው፡፡

በግለሰብ ደረጃ ሕመም ሲገጥማቸው በውጭ የሚኖሩና በአገር ውስጥ የሚኖሩ በጎ አሳቢዎች በበይነ መረብ በሚደርሳቸው መረጃ የብዙዎችን ሕይወት እንዲታደጉ ምክንያት ሆኗል፡፡ ለተለያዩ ንቅናቄዎች ይኼው በይነ መረብ ብዙ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ በምሳሌነት የሚነሳው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ ያለው ለሌለው ለማካፈል ወደ ኋላ ያለ የለም፡፡ ሁሉም በየአቅሙ ሲደግፍና ሲያግዝ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ባለሀብቱ በዚሁ በይነ መረብ ጥሪ አማካይነት በገንዘብ፣ በዓይነት እንዲሁም ሕንፃዎቻቸውን ሳይቀር ለኮሮና ቫይረስ ጊዜያዊ አገልግሎት እንዲሰጡ መፍቀዳቸው የሚታወስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በይነ መረብ ተጠቃሚዎች በሚደረጉ ድጋፎች ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ብዙዎች ይመክራሉ፡፡ የበይነ መረብ ልመናን በዓለም የሚገኙ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ያጋጠማቸውን ሪፖርት ማድረጋቸውን ፌስቡክ በ‹‹ኸልፕ ኮሙዩኒቲ›› ገጹ አስፍሯል፡፡ ብዙዎች ከተዋወቋቸው የፌስቡክ ጓደኞች ልመና እንደሚገጥማቸው ዘፈን ላወጣ ነው፣ ለጀመርኩት ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ አጣሁ፣ የሚሉና ሌሎም እንደሚያጋጥሟቸው ገጹ አሥፍሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...