Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ እንዲተገበር ዳግም ጥሪ ቀረበ

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ እንዲተገበር ዳግም ጥሪ ቀረበ

ቀን:

በኅብረተሰቡ እየተዘነጋ ያለው የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ እንዲተገበር ጤና ሚኒስቴር ዳግም ጥሪ አቅርቧል፡፡

በአሥር ክፍሎች የቀረበው መመርያ በዋናነት በሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ የመንግሥትና የግል ሴክተሮች ያለው መዘናጋት እንዳይኖር የሚመራ ሲሆን፣ ኅብረተሰቡ ወደ ነበረበት የጥንቃቄ ዕርምጃ እንዲመለስ  የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ማክሰኞ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች መዘናጋት በመጨመሩ፣ የሚያዙ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ቁጥራቸው ከፍ እያለ መምጣቱ ተገልጿል፡፡

ጥንቃቄ ማድረግና የመከላከያ መንገዶችን መተግበር ከምንጊዜውም በላይ አስፈላጊ መሆኑን የሚገልጹት ሚኒስትሯ፣ በዓለም መልኩን ቀይሮ እየመጣ ላለው ወረርሽኝ የመጀመርያ ዕርምጃ  ቅድመ መከላከል መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሀረላ አብዱላሂ በበኩላቸው፣ አሁን በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከሌሎች አገሮች ጋር በማነፃፀር ብቻ መዘናጋት እንደማይገባ በማስገንዘብ፣ የሌሎች አገሮች የመመርመር አቅማቸው ከፍ ያለ በመሆኑ እንጂ፣ በኢትዮጵያ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከዚህ በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው መመርያ ውስጥ በስብሰባ፣ በቀብር ሥርዓት፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት፣ የአደባባይ በዓላት አከባበር ላይ ስለሚወሰዱ ጥንቃቄዎች የሚተነትን ነው፡፡

በሌላ በኩል መመርያው መተግበር የማንኛውም ሰውና ተቋም ግዴታ ሲሆን በተደነገጉት ክልከላዎችና ግዴታዎችን የተላለፈ ሰው አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን ይጠቁማል፡፡

መመርያው በጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተዘጋጀ ሲሆን፣ የመንግሥትና የግል ተቋማት እንዲሁም ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች ወረርሽኙን ለመከላከል ለመቆጣጠር እንዲተገብሩት በድጋሚ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ጥብቁ መመርያ

መሰንበቻውን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥብቅ መመርያ መሠረት ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግሥታዊና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግና ተገልጋዮችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በተቋሙ ላይ ተጥሏል፡፡

 የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አሽከርካሪ፣ አገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን በተመለከተ በሕግ ከተወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት መስጠት እንደሌለበት መግለጫው አመልክቶ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሠሪዎች በተመለከተ በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውኃ፣ ሳሙና፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያ እንዲሁም የፀረ ተህዋሲያን ግብዓት የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የዘርፉ መሥርያ ቤቶች በየመስካቸው የሚያወጧቸው መመርያዎችና አሠራሮች የኮቪድ-19 በሽታን ለመግታት ወይም ለመቀነስ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመርያ ውስጥ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች የማይቃረኑና ተጣጥመው የወጡ መሆን እንዳለባቸው፣ በዚሁ መመርያ የተደነገጉ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን፣ ማንኛውም ሰው ከ25/01/2013 ጀምሮ መመርያው የፀና መሆኑን አውቆ ተግባራዊና ተፈጻሚ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡    

ተተኳሪ ጉዳዮች

ኮቪድ-19 በወረርሽነት ዓለምን ካካለለ ዘጠኝ ወር ሆኖታል፡፡ በእነዚህ ወራት ሕዝበ ዓለም ከኮሮና ቫይረስ እንዲጠበቅ፣ በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራኛ እንዳይያዝ የጤና ባለሙያዎችና ዓለም አቀፋዊም ሆነ አገራዊ ተቋማት ማስገንዘቢያዎችን ከመስጠት ችላ ያሉበት ጊዜ አልነበረም፡፡

ኮቪድ-19 የሚተላለፍበት መንገድ አስመልክቶ እስካሁን ያለው አቋም፣ በሽታው ከሕመምተኛው አፍንጫ ወይም አፍ በሚወጣ ጥቂት ፈሳሽ አማካይነት የሚተላለፍ መሆኑ ነው፡፡ ኮቪድ-19 ያለበት ሰው ሲያስነጥስም ሆነ ሲተነፍስ ወደ ሌሎች ከማስተላለፍ ባለፈ፣ ከሕሙማን የሚወጣ ፈሳሽ ያረፈበትን ቦታ የነኩ ሰዎችም በበሽታው በቀላሉ ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ሰዎች ከሰዎች ጋር ያላቸው ቅርርብ ከአንድ ሜትር በላይ መሆን አለበት የተባለውም በሽታው በትንፋሽ ስለሚተላለፍ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ የተደረጉ ጥናቶች የሚያሳዩት ቫይረሱ በአየር ውስጥ ሳይሆን በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች የመተንፈሻ አካላት ከወጡ ፍሳሾች ጋር በሚኖር ንክኪ ብቻ የሚተላለፍ መሆኑን ነው፡፡

ይሁን የቅርብ መረጃዎች የኮሮና ቫይረስ በአየር ላይ የመተላለፍ ዕድሉ ሰፊ መሆኑ እየገለጹ ናቸው፡፡ ይህን ተከትሎ የዓለም ጤና ድርጅት በቫይረሱ የመጋለጥ ወይም ያለመጋለጥ ዙርያ የቀረቡ ጥናቶች ላይ እየመከረ መሆኑ ተዘግቧል፡፡ በአየር ላይ ቫይረሱ በመቆየት ወደ ሌላ ሰው ሊተላለፍ ስለሚችል ተገቢው ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበትም ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ -19) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት አገላለጽ፣ ኮሮና ቫይረስ የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን የያዘ የቫይረስ ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰዎችና በእንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ በሰዎች ላይ የሚከሰተው ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በመጉዳት ከተራ ጉንፋን እስከ ከፍተኛ የመተንፈሻ አካል ችግር የሚያደርስ ነው፡፡

ኅብረተሰቡ በሽታው በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ሳይዘናጋ የሚተላለፉ መልዕክቶችንና መከላከያ መንገዶችን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች በሚያገኝበትም ወቅት በተዘረጉ የነፃ የስልክ መስመሮች በመደወል እንዲያሳውቅና የበሽታውን ሥርጭት በመቆጣጠር በኩል የድርሻውን እንዲወጣ አሳስቧል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፣ በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118 276796 ወይም በኢሜይል አድራሻ [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

በተጨማሪም ለተለያዩ ጉዳዮች በአንድ ቦታ መሰባሰብን በማስወገድ፣ እጅን አዘውትሮ በመታጠብ፣ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ቦታዎች ላይ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) በማድረግ፣ በአካል ንክኪ የሚደረግ ሰላምታን በመተውና አካላዊ መራራቅን ተግባራዊ በማድረግ የበሽታውን ሥርጭት እንዲከላከል ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ኅብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳሰበው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ዕለት ዕለት በሚደረገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በበሽታው መያዝን የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን ‹‹›› ሕጎች በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት ሁሉም እንዲከላከልም በጥብቅ አሳስበዋል፡፡

አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...