Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

የትምህርት ዘርፍ አበርክቶ

ከ1940ዎቹ ጀምሮ ነው በኢትዮጵያና በውጭ የትምህርት ዘርፍ አበርክቷቸውን የጀመሩት፡፡ በ1940 ዓ.ም በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ 1947 ዓ.ም እስከ 1967 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለመጀመርያ ጊዜ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማስተማሪያ የሆኑና ከሁለት አሠርት በላይ ያገለገሉትን አረንጓዴውደኛዬን፣ ሁለተኛው የንባብ መጽሐፌ፣ ሦስተኛው የንባብ መጽሐፌንና የጽሕፈት ፋናን አዘጋጅተዋል፡፡ ሉልሰገድ ዓለማየሁ (ዶ/ር) ይባላሉ፡፡ በ1950 ዓ.ም. ከጠላት ወረራ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከውጭ አገር ዩኒቨርሲቲዎች በዲግሪ እየተመረቁ ከተመለሱት አንዱ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ትምህርት ቤቶች ለማዘመንና ለማደርጀት በተወሰደውርምጃ የቀድሞው ትምህርት ቤታቸው ለነበረው ሚያዝያ 27 ትምህርት ቤት ጅማ የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ አስተዳደራቸው ከአሜሪካ ባመጡት አዳዲስ፣ ሁሉን ተማሪ አካታችና አቃፊ፣ ሽቅብና አግድም ሆኖ ትምህርትን የሚያጎለብት እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ዶ/ር ሉልሰገድ ስለሕይወት ተሞክሯቸው፣ ትምህርትን የማሳደግ ፅናታቸውና በትምህርቱ ዘርፍ ስለነበራቸው አበርክቶ ምሕረት ሞገስ አነጋግሯቸዋለች፡፡

ሪፖርተር፡- ጉለሌ ለሚገኘው መድኃኔዓለም ትምህርት ቤት የመጀመርያው ኢትዮጵያዊ ርዕሰ መምህር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ስለነበረው ሁኔታ ቢያስታውሱን?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- መጀመርያ እንግሊዛዊ ርዕሰ መምህር ነበር ያለው፡፡ እኔም በተጠባባቂ ዳይሬክተርነት ነበር የጀመርኩት፡፡ የመጀመርያው ትኩረቴ የአንደኛ ደረጃውን ትምህርት ቤት ማስተካከል ነበር፡፡ በአንደኛ ደረጃው ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ክፍሎች ከነበሩ መምህራን ብዙዎቹ ከአቅም በታች ነበሩ፡፡ የጡረታ ዕድሜ ገና ያልታወጀ ስለነበረ፣ በመካከላቸውም በሽምግልና የደከሙ አዛውንቶችም ነበሩ፡፡ በጊዜያዊነት እነዚህን አሠልጥኜና አስተካክዬ ዓመቱን ጨረስሁ፡፡ ተጠባባቂ ዳይሬክተርነቴ ከዓመቱ ጋር ቢፈጸምም፣ ሙያዊ ተልዕኮዬ ዕንቅልፍ ስላሳጣኝ እዚያው ማገልገሌን እንድቀጥል ጠይቄ ተፈቀደልኝ፡፡ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ የመድኃኔዓለምን ትምህርት ቤት አሜሪካ ዓይቼ አስቀንቶኝና ጎምጅቼ በነበረው የትምህርት አሰጣጥ፣ ሙያዊ አደረጃጀትና ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ መዋቅር ዘረጋሁ፡፡ ለመማር የመጣውንም ሁሉ ተምሮ፣ አውቆና ለተሻለ ኑሮ ሕይወቱን ለውጦ እንዲያድግ ለማድረግ ባዘልኩት ሙያዊ ጥበብ መድኃኔዓለም ትምህርት ቤትን ከማዘመን አልፌ፣ ለሌሎችም የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች ምሳሌ እንዲሆን አደረግሁ፡፡ በክህሎት እየተመረጡ 12ኛ የደረሱት ፈተናውን ከተቀመጡ በኋላ በቁጥር አነስተኛ የሆኑት ሲያልፉና ሲዘመርላቸው የቀረው ፈተናውን ያላለፈው ብዙኃኑ በተስፋ ቢስነት አንገቱን ደፊ ነበር፡፡ በመድኃኔዓለም ትምህርት ቤት ግን ሁሉም ከስምንተኛ ክፍል ጀምሮ ሯጩም ቀስ ብሎ ደራሹም አብሮ በአንድነት 12ኛ ክፍል ፈፅሞ ብሔራዊ ፈተናን አለፈም አላለፈም በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መፈጸሚያ ምስክር ወረቀት በማግኘት ይመረቁ ነበር፡፡ በአገር ውስጥ ያለው ዩኒቨርሲቲ ባይቀበላቸውም ልጆቼ ያንን እኔ የሰጠኋቸውን የምስክር ወረቀት ይዘው ለመጀመርያ ጊዜ ወደ አሜሪካ በመጓዝ በቀጥታ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት አግኝተው ገብተዋል፡፡ ዶክትሬት ዲግሪ አግኝቶ የተመረቀም አለ፡፡ ያኔ ለነበረኝም ሁሉን አቀፍ ምሥጉን አገልግሎት በተለይ በዓመታዊው የአዲስ አበባ ስታዲዮም የብሩህ ተማሪዎቻችን አቅርቦት በግርማዊ ንጉሠ ነገሥቱና በሕዝቡ ፊት ላተረፍነው ዝና በደጃዝማች ክፍሌ ዕርገቱ አቅራቢነት ታዝዤ በሐምሌ ወር 1956 ዓ.ም. ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ፊት ቀርቤ ላበረከትኩት ከፍተኛ አገልግሎት ምሥጋና ተችርያለሁ፡፡ በጊዜው በመድኃኔዓለም ትምህርት ቤት ይታይ በነበረው ከፍተኛ እንቅስቃሴ ይሰጡኝ ከነበሩት ተጨማሪ ኃላፊነቶች አንዱ በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ጥያቄ በአገራችን የመጀመርያውን የትምህርት ሚኒስቴርን የሕዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳቋቁም ተጠይቄ በጊዜው ከውጭ አገር ትምህርታቸውን ጨርሰው የተመለሱትን አቶ ስብሓት ገብረ እግዚአብሔርን (አባባ ስብሓት)፣ አቶ ሙሉጌታ ኢተፋን አሁን ዶክተርና አምባሳደር፣ ወይዘሮ የሺመቤት ስማቸውን በኋላ የእቴጌ መነን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የነበረችውንና ሌሎች ባለሙያዎች ጨምሬ በማዋቀር በ1955 ዓ.ም. ጠንከራ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አቋቁሜ የመጀመርያውን የትምህርት ዜና መጽሔት አሳትሜያለሁ፡፡ ሪፖርተር፡- በ1949 ዓ.ም. ነበር ለተጨማሪ ትምህርት ወደ አሜሪካ ያቀኑት፡፡ በዚያ ቆይታዎ ለኢትዮጵያ አበርክቻለሁ የሚሉት አለ?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- አሜሪካ በደረስሁበት በ1949 ዓ.ም. በግሌ በመነሳሳት የሚያጋጥመኝ ዕድል እንዳያመልጠኝ እጥር ነበር፡፡ ዋናው ተልዕኮዬ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የትምህርት መጻሕፍት ወርክ ሾፕ ክትትሌ ላይ ጊዜዬን እያብቃቃሁ በማገኘው ክፍተት ወደ ቮይስ ኦፍ አሜሪካ (ቪኦዴ) ቢሮ ዋሺንግተን ዲሲ መሄድ ጀመርሁ፡፡ ከዚያም ለቪኦኤም ሆነ ለኢትዮጵያ የመጀመርያዎቹ ከአሜሪካ የተላኩ ፕሮግራሞች፣ የመርሊን ዘ ስቶሪ ቴለር ተረቶች፣ ጃዝ ሙዚቃዎችና እንግሊዝኛ ቋንቋ በሬዲዮ ለኢትዮጵያ አዳማጮች በአማርኛ ቋንቋ አስተላለፍሁ፡፡ በአገራችን በዚያን ጊዜ የፕሮግራም አቅራቢ ስም ማውሳት ጨርሶ በማይታወቅበትና፣ ፕሮግራሙም በሙዚቃና ድምፃ ድምፅ በማይቀነባበርበት ወቅት፣ በአገራችን ራዲዮ ጣቢያ ላይ፣ የስቱዲዮ አቀናባሪዎችና ዕለታዊ ወሬ አቅራቢዎች እንደ ጉድ እየተመለከቱኝ፣ ራሴ የፕሮግራሙ አቀነባባሪ፣ መሪና አቅራቢም በመሆንና ለዚሁም ስሜን በማወጅ አስተላልፍ ነበረ፡፡ ይኼውም ፕሮግራም በመጀመርያ የልጆች ጊዜ ቀጥሎ የነገው ሰው የተባለ በየሳምንቱ ቅዳሜ በዘጠኝ ሰዓት ላይ ለሁሉም ዕድሜ ልጆች በናፍቆት የተጠበቀ የመዝናኛ መማሪያ ፕሮግራም ነበር፡፡ በጥር ወር 1969 ዓ.ም. በትምህርት ሙያ ጥልቀት ጥናት የቀረኝን ማስትሬትና ዶክትሬት ፈጽሜ ከአሜሪካ እንደተመለስሁ በትምህርት ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተርነት ሠርቻለሁ፡፡ በጎንደርና በአሥመራ ለረዥም ጊዜ ቆይቶ የነበረውን የተማሪዎች አድማ አብርጄ ትምህርቱ በሰላም እንዲቀጥል አድርጌያለሁ፡፡ ቀጥሎ በምርጫዬ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መምህራን ማሠልጠኛ ኮተቤ ደብር ለራሴ በፈጠርሁት የማዕረግ ስም ‹‹ርዕሰ መምህር››ነት ተመድቤ አሸቅበው የሚያዩ ራሳቸውን ለማሳደግ ወሰን፣ ልክና ገደብ ሳይሰጡ፣ ለሚያስተምሩት አዳጊ ልጅ ያላቸውን ሁሉ መስዋዕት በማድረግ የሚያስተምሩ፣ ወጣቱን በዕውቀት እንዲያንሰራራ፣ ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ ባለመቆጠብ አድገው ለማሳደግና ለራሳቸውም ዕድገት ገደብ የማያበጁ ሃይማኖት፣ ጎሳና ዘር ያልለያያቸው፣ መለያየትንም የሚፀየፉ፣ ለለውጥና ዕድገት አሸቅበው፣ አርቀውና አሸጋግረው የሚመለከቱ የኮተቤው፣ የኮተቤዎቹ ብዬ የሰየምኋቸውን ኢትዮጵያውያን ገንብቼ አሠልጥኛለሁ፡፡ ከየተመደቡባቸውም ክፍላተ አገሮች ይጽፉልኝ የነበሩት በእጄ የሚገኙ ደብዳቤዎች ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡ ታሪካቸውም በኮተቤዎቹ ህያው ዓመታዊ መጻሕፍትና ከየተመደቡባቸው ክፍላተ አገሮች ይጽፏቸው በነበሩት ደብዳቤዎቻቸው ተዘክሯል፡፡ በ1967 ዓ.ም. ደርግ ሥልጣን እንደተቆናጠጠ በኢትዮጵያ የመጀመርያው ብሔራዊ የከፍተኛ ትምህርት ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ በመሆን ተሹሜ የኢትዮጵያን የከፍተኛ ትምህርት መስፋፋት፣ አደረጃጀት፣ አቅጣጫ፣ አስተዳደርና ዕድገት መመርያና፣ መተዳደሪያ ደንብ ካዘጋጀሁና የገዥዎች ቦርድ አባላት ምደባ ካጠናቀቅሁ በኋላ፣ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተቀጥሬ ከ1969 ዓ.ም. እስከ 1982 ዓ.ም. ድረስ አገልግያለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በዩኔስኮ ያበረከቱት አገልግሎት ምን ይመስላል?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- በታኅሣሥ ወር 1969 ዓ.ም. ዩኔስኮ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኬፕ ኮስት ኬፕ ኮስት ጋና ልኮኝ የዩኒቨርሲቲውን የትምህርት ፕላንና አስተዳደር ኢንስቲትዩት አቋቁሜያለሁ፡፡ የማስተማር መማር ሙያዊ ሒደትን፣ ተማሪን በክህሎት ባለመለያየት ሁሉም ሊደርሱ ከሚችሉበት ከፍታ እንዲደርሱ ጥልቅ ግንዛቤ በማስጨበጥ በርከት ያሉ የአንድና የሁለት ሳምንታት ኮርሶችን ለትምሀርት ቤቶች ኃላፊዎችና መሪ መምህራን በመስጠት የአገሩን ትምህርት በለውጥ አዘምኛለሁ፡፡ ከጋና ለጥቆ ከታኅሣሥ 1970 ዓ.ም. ጀምሮ የናይጄሪያውን በአፍሪካ ቀደምቱ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ኢባዳን፣ ፋኩልቲ ኦፍ ኤጁኬሺን ሥር ዴፓርትሜንት ኦፍ ኤጁኬሺናል ፕላኒንግ ኤንድ አድሚኒስትሬሺንን ለማቋቋም ከተላኩት አምስት ዓለም አቀፍ የዩኔስኮ ኤክስፐርቶች አንደኛው በመሆን በትምህርት አመራርና ሱፐር ቪዢን ዘርፍ አሠልጣኝነት ተመድቤ ሠርቻለሁ፡፡ የኢባዳን ተልዕኳችን ጠንካራ የሆነ በሦስቱም ከፍተኛ ማዕረጎች፣ በባችለርስ በማስትሬትና በዶክትሬት ዲግሪ የትምህርት መሪዎችን ማሠልጠን ሲሆን፣ ዲፓርትመንቱን በማቋቋም፣ በማጎልበትና ጠንካራ መሪዎችን በማሠልጠን በቆየንባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ፣ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ለመጀመርያ ጊዜ በከፍተኛ ቁጥር የተመረቁ በዕውቀትና ሙያ ብስለት የዳበሩ የትምህርት መሪዎችን በሦስቱም ዲግሪዎች አሠልጥነን አፍርተናል፡፡ እኔና የዩኔስኮ ባልደረቦቼ ዲፓርትመንቱን ለማቋቋም ኢባዳን እንደደረስን የዩኒቨርሲቲው አቋም የብሪቲሽ አወቃቀርና ሒደት የተከተለ ነበረ፡፡ በደረስሁበት ዓመት ግን ይህ ተለውጦ ወደ አሜሪካን ክሬዲት ሰዓት አወቃቀር እንዲለወጥ ተወስኖ አገኘሁት፡፡ የዩኔስኮ ጓደኞቼም ሆኑ ነባር የዩኒቨርሲቲው ባለሥልጣናት በብሪቲሽና መሰል ሒደት ካለው ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ስለነበሩ ለጊዜው በለውጡ ትንሽ ግራ ተጋብተው ነበር፡፡ እኔ የከፍተኛ ትምህርቴን በሙሉ የተከታተልሁት በአሜሪካ ሆኖ የሥልጠናዬ ዘርፍ አካልም ሥርዓተ ትምህርት በመሆኑ፣ ወዲያው የራሳችንን ዲፓርትመንት ሥርዓተ ትምህርት ከጓደኞቼ ጋር በመመካከር መልክ ስንያስይዝ ሌሎችንም ፋኩልቲዎችና ዴፓርትሜንቶች በማማከር ረድቻለሁ፡፡ በየደረስሁበት ዓላማዬ በቂና ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ማስተማርና ለተማሪው ፍሬያማነትና ብቃት የተጎናጸፈ፣ አንዱንም ከሌላው በማነፃፀር ልዩነት ሳይደረግበትና ሳይዳላበት እንዲያድግና ለፍሬያማ ኑሮ መለወጥ እንዲችልና እንዲበቃም የትምህርት አመራርን፣ አስተዳደርንና ቁጥጥርን በጥልቀት በማስተላለፍ ትምህርትን በማሻሻል በመቆጣጠርና በማዘመን ደክሜያለሁ፡፡

ሪፖርተር፡- በዩኔስኮ ውስጥ ሲሠሩ የእስዋዚላንድን [ስዋቲኒ] ትምህርት ከወደቀበት የታደጉበትን አሠራር ቢነግሩን?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- በ1977 ዓ.ም. እስዋዚላንድ ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ከወጣች በኋላ ትምህርቱ ደረጃው ወድቆ ነበር፡፡ የተማሪዎች በእንግሊዙ የኬምብሪጅ ኦቨርሲስ ሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ውጤቶች በማሽቆልቆሉ ከፍተኛ ሥጋት ላይ ነበረች፡፡ ዩኤስኤ አይዲና የተመድ ባለሙያዎች እያደርጉ የነበረው ጥረት ቁልፉን ማግኘት አልቻለም፡፡ በተከታታይ ለተሻለ ማስተማሪያ መንገድ ፍለጋ፣ አንድ እንግሊዛዊ ባለሙያ ያቀረበው ጥናት ይፋ በሚሆንበት ጉባዔ ላይ ዩኔስኮን ወክዬ እንድሳተፍ ተላክሁ፡፡ ለአገሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና ሽማግሌዎች የቀረበው ጥናት እንደቀደሙት ጥናቶች ሁሉ ችግሮችን ከመዘርዘር አልፎ መፍትሔ የሌለው መሆኑን ለአገሩ የትምህርት ዋና ኃላፊ አሳየሁት፡፡ ታዲያ ምን እናድርግ? ሲል፣ ከዩኔስኮ በተላክሁበት አጭር ጊዜ ውስጥ ሁለት ጥራዝ መፍትሔዎች ያልኳቸውን አስተሳሰቦች አቀረብሁ፡፡ ወዲያውም በከፍተኛ አማካሪነት ዩኔስኮ ላከኝ፡፡

ሪፖርተር፡- በእስዋዚላንድ የወደቀውን ትምህርት ያነሱት ማስተማርና ማስተዳደር የተለያዩ ናቸው ብለው በዘረጉት አሠራር ነበር፡፡ ማስተማርና ማስተማርን ማስተዳደርን እንዴት ይገልጹታል?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- ማስተማርናማስተማርንማስተዳደርሁለትየተለያዩኃላፊነቶችናተግባሮችናቸው፡፡አስተማሪልጁያላወቀውንለማሳወቅበክፍልውስጥሲጥር፣ርዕሰመምህሩ ወይም አስተዳዳሪውበማንኛውምመንገድየመምህሩሥራበቀላል፣በተቀላጠፈናየክፍሉንተማሪዎችበሙሉያለምንምአድልኦእያንዳንዱልጅእንዲማር፣እንዲለወጥናበዕውቀትእንዲመጥቅከመምህሩጎንሆኖመምህሩንየሚረዳናየሚደግፍነው፡፡ስህተትምጎርጓሪሳይሆንመንገድጠራጊ፣ሙያዊ ዕርዳታሰጪናየሙያአጋዥነው፡፡የትምህርትቤቶችየተዋረድሠራተኞችበሙሉለልጆቻቸውእንጂበልጆቻቸውላይየመጡአይደሉም፡፡በትምህርት ሒደትሁሌምፈተናንየሚወድቀውአስተማሪውእንጂተማሪውአይወድቅምየሚባለውምለዚሁነው፡፡በእስዋዚላንድይህንለማስገንዘብየአሥራአምስትቀንወርክሾፕከጠዋትጀንበርእስከምሽቱሁለትሰዓትድረስየተራዘመሌክቸርስ፣በክፍልውስጥናውጪተማሪዎችየትምህርትቤቱዋናተዋናይ መሆናቸውን ነገርኩ፡፡በትምህርትቤቱየሚደረገውማንኛውምነገርተማሪዎች ሊደርሱየሚችሉበትሥፍራናደረጃሁሉእንዲደርሱመሆኑን አስገነዘብሁ፣አስጨበጥሁ፡፡ለዚሁምእኔንመሰልአስተሳሰብያላቸውንከፍተኛምሁራንከዩኒቨርሲቲኦፍኢባዳን፣ከእንግሊዙዩኒቨርሲቲኦፍሳሴክስ፣ከስዊድንናከዋናውመሥሪያቤትዩኔስኮቁንጮየሆኑምሁራንንአምጥቼተካፋይአደረግሁ፡፡ የአገሩምትምህርትቤቶች፣በባህርማዶውካምብሪጅኦቨርሲስፈተናውጤትተምዘግዝገውወጥተዋል፡፡ከቀድሞውጤቶቻቸውያልተሻሻሉትሁለት ትምህርትቤቶችውስጥ የአንዱትምህርትቤትርዕሰመምህርበሕመምምክንያትበወርክሾፑያልተሳፈሲሆን፣የሁለተኛውርዕሰመምህርየወርክሾፑንኮርስተከታትሎእንዳበቃበሹመትወደትምህርትቤቱባለመመለሱነው፡፡

ሪፖርተር፡- ትምህርተ ባህረ ሐሳብ ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ምን ለመግለጽ ነው?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- ትምህርተ ባህረ ሐሳብ ትምህርት ሰው በተፈጥሮው የታደለውን፣ ከእናት አባቱ የወረሰውንና ከቤተሰብና ከአካባቢው ያካበተውን ዕውቀት ማበልፀጊያ ነው፡፡ ኮትኩቶ ማስፋፊያና ፊት ለፊትና ወደ ላይ ማደጊያም ነው፡፡ ሁሌም ለተሻለ ኑሮና ዕድገት የመለወጥ እመርታዎችን ማስጨበጥ ታላቁ መወጣጫ መሰላልና፣ ከፍታቸውም መድረሻ  ክንፍ ነው፡፡ የትምህርትም ዋናው መንጠራሪያ፣ ግብና ዓላማም ሰው በመወለድ ከቤተሰብ የወረሰውን፣ በአብሮነት ከአካባቢዎች ያገኘውንና በመደበኛ ትምህርት መገብያዎች በየደረጃው የቀሰመውን፣ ከትምህርት ቤቶች ያካበተውን ዘርፈ ብዙ ዕውቀት በሥራ ላይ ማዋል ነው፡፡ ትምህርትም መማርን ሲያስቀድም፣ ተምሮ የተገኘ ዕውቀትን ቀና ብሎ አሸቅቦና አሻግሮ፣ በትህትና፣ በብልኃትና በድፍረት ሲያስፈልግም በመስዋዕትነት ለሰው ልጆች ትንሳዔ ለማዋል ወደዚህ ዓለም የተመጣበትን ቅዱሱን ግብ ለአገር ለወገን በማዋል አሻራን ማሳረፍ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- በኢትዮጵያም የትምህርቱን ዘርፍ ለማሻሻል ትምህርት ቤቶች ከፍተው ተሰማርተው ነበር፡፡ ከዚህ ባለፈ በውጭ ያካበቱትን ልምድ መንግሥት እንዲጠቀምበት አልሞከሩም?

ዶ/ር ሉልሰገድ፡- ትምህርት ሚኒስቴር ከ1990ዎቹ ጀምሮ በተደጋጋሚ ተመላልሼ ጠይቄያለሁ፡፡ የሚሰማኝ ግን አላገኘሁም፡፡ የእኔ ፍላጎት ተማሪ ሰነፍ ስለሆነ መውደቅ የለበትም፡፡ የሰነፈው በመምህሩ ምክንያት እንጂ በራሱ አይደለም እላለሁ፡፡ ተማሪዎችን በሙሉ ትኩረት ሰጥተንና መምህራን በአግባቡ ሠልጥነው ትኩረታቸው ሁሉን ተማሪን በአንድ ላይ ማብቃት እንዲችሉ ማድረግ ላይ ከሠራን የትምህርቱን ጥራት እናስጠብቃለን፡፡ ተማሪዎችን ብቁ እናደርጋለን፡፡ በትምህርቱ ዘርፍ በርካታ አሠራሮችና ሐሳቦችን ለማካፈል ፈልጌ ብመላለስም ብዙም የሚቀበለኝ አላገኘሁም፡፡ አሁንማ አርጅቻሁ፡፡ ላይ ወጥቼ ታች ወርጄ መሥራት ባልችልም የእኔን ዕውቀት ፈልጎና ተጠቅሞ ብቁ ተማሪ ማፍራት ለሚፈልግ ሁሉ ልምዴንና ተፈትነው ውጤታማ የሆኑ አሠራሮችን አካፍላለሁ፡፡ የመንግሥትም ሆነ የግል ትምህርት ቤቶች ምክር ቢጠይቁኝ ልተባበር እችላለሁ፡፡

ተዛማጅ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች ለማግኘት

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

ተዛማጅ ፅሁፎች

ከሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች እስከ ግለሰቦች የሚደርሰው ወገን ፈንድ

ወገን ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ሕጋዊ ዕውቅና በማግኘት ከኢትዮጵያና ከተለያዩ አገሮች ልገሳን ለማሰባሰብ ‹‹ወገን ፈንድ›› የሚባል የበይነ መረብ (ኦንላይን) የድጋፍ ማሰባሰቢያ ድረ...

ግዴታን መሠረት ያደረገ የጤና መድኅን ሥርዓት

የኢትዮጵያ ጤና መድኅን ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከገባ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ማኅበረሰብ አቀፍና የማኅበራዊ ጤና መድኅን ሥርዓቶችን መሠረት አድርጎም ይሠራል፡፡ የማኅበረሰብ አቀፍ ጤና መድኅን ሥርዓት በኢመደበኛ...

የመሠረተ ልማት ተደራሽነት የሚፈልገው የግብርና ትራንስፎርሜሽን

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ተቋም አርሶ አደሩን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ በማድረግ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚውን የማሳደግ ዓላማ ይዞ የተመሠረተ ነው፡፡ ተቋሙ የግብርናውን ዘርፍ ሊያሳድጉ የሚችሉ ጥናቶችን...