የኢትዮጵያ ድምፃውያንን ሥራዎች በአውታር መተግበርያ ለማስተላለፍ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የሙዚቃ ባለሙያዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የተነገረለትና ለአምስት ዓመታት የሚቆየውን ስምምነት የፈጸሙት አውታር መልቲ ሚዲያና ቢጂአይ ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ ታኅሣሥ 15 ቀን 2013 ዓ.ም. በተደረገው ስምምነት ላይ ታዋቂ የሙዚቃ ባለሙያዎች፣ ደራሲዎችና አቀናባሪዎች ተገኝተዋል፡፡ ፎቶዎቹ የሥነ ሥርዓቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡