Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትሁለት አትሌቶች ዶፒንግ በመጠቀማቸው ለአራትና ስምንት ዓመት ታገዱ

ሁለት አትሌቶች ዶፒንግ በመጠቀማቸው ለአራትና ስምንት ዓመት ታገዱ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽሕፈት ቤት የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) የሕግ ጥሰት በፈጸሙ አትሌቶች ላይ የቅጣት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው የማራቶንና የረዥም ርቀት ተወዳዳሪዎች ወንድወሰን ተሰማና ኢዮብ ኃብተ ሥላሴ ሲሆኑ፣ ሁለቱ አትሌቶች ተጠቅመዋል የተባለውን አበረታች ቅመም መጠቀም አለመጠቀማቸው እስኪረጋገጥ ድረስ ጊዜያዊ ዕገዳ ተጥሎባቸው የቆዩ ስለመሆናቸው ጭምር ጽሕፈት ቤቱ በመግለጫው አካቷል፡፡

መግለጫው ጉዳያቸው እስኪጣራ ጊዜያዊ ዕገዳ ተጥሎባቸው የቆዩት ሁለቱ አትሌቶች፣ ‹‹ኢዮብ ኃይለ ሥላሴ እ.ኤ.አ. የካቲት 03 ቀን 2020 ታይላንድ በተካሄደው ውድድር ላይ ካቲኖን (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ ተረጋግጧል፤›› ብሏል፡፡

ይህንኑ ተከትሎ አትሌቱ እ.ኤ.አ. ከሚያዝያ 3 ቀን 2020 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ዓመታት በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት የተጣለበት ሲሆን፣ ውሳኔ ከመተላለፉ በፊት በውድድሩ ያገኘው ውጤትና ውጤቱን ተከትሎ የሚሰጥ ማንኛውም የዕውቅና ሽልማት እንዲሰረዝ ተደርጓል፡፡

እንደ ኢዮብ ሁሉ ወንድወሰን ከተማ ቀደም ሲል ካቲኖን (Cathinone) የተባለውን የተከለከለ የስፖርት አበረታች ቅመም መጠቀሙ በመረጋገጡ እ.ኤ.አ. እስከ የካቲት 1 ቀን 2024 ድረስ በማንኛውም ውድድር ላይ እንዳይሳተፉ ዕገዳ ተጥሎበት ቆይቷል፡፡ ይሁንና አትሌቱ ጉዳዩ እንደገና እንዲታይለት የተሳሳት የሰነድ ማስረጃ በማቅረብ የሕግ ጥሰቱን የማጣራት ሒደቱን በተለየ መልኩ በማስተጓጎልና በድጋሚ ለማጭበርበር በመሞከር ተደራራቢ የሕግ ጥሰት በመፈጸም ተጠርጥሮ ጉዳዩ እንደገና ሲጣራ መቆየቱን የኢትዮ ናዶ መግለጫ ያስረዳል፡፡

በመሆኑም አትሌት ወንድወሰን ያቀረባቸው ሰነዶች የሐሰት መሆናቸው በመረጋገጡና በፀረ ዶፒንግ ሕግ አንቀጽ 2.5 ላይ የተደነገገውን የፀረ ዶፒንግ እንቅስቃሴውን የማስተጓጎልና አቅጣጫ የማሳት የሕግ ጥሰት መፈጸሙ በመረጋገጡ፣ አትሌቱ ቀደም ሲል ከተጣለበት የአራት ዓመት የዕገዳ ቅጣት በተጨማሪ የመጀመርያው የዕገዳ ቅጣት ከሚያበቃበት የካቲት 1 ቀን 2024 ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት ማለትም እስከ የካቲት 1 ቀን 2032 ድረስ በማንኛውም ስፖርታዊ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ የዕገዳ ቅጣት የተላለፈበት መሆኑ ኢትዮ ናዶ በመግለጫው ይፋ አድርጓል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...