Tuesday, January 31, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየቆላ ዝንብን ለመከላከል የተሰጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለሦስት ዓመታት ያለ ሥራ መቆማቸው...

የቆላ ዝንብን ለመከላከል የተሰጡ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ለሦስት ዓመታት ያለ ሥራ መቆማቸው ተነገረ

ቀን:

ከዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት በኢትዮጵያ የቆላ ዝንብን ለመካላከል እንዲያግዙ ወደገር የገቡ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በአገር ውስጥ መመርያ ባለመኖሩ ምክንያት በሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ተይዘው ያለ ሥራ ለሦስት ዓመታት መቆማቸው ተነገረ።

የኢትዮጵያ የቆላ ዝንብና የገንዲ በሽታ መቆጣጠሪያ ተቋም፣ የቆላ ዝንብን በእጅጉ ለመካለከል ያግዘኛል ያላቸውንናተቋሙ የተሰጡትን ሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ እንዴት ማንቀሳቀስ እንደሚቻል የሚፈቅድ መመርያ ይውጣ በማለት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጠይቋል።

 የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዳኛቸው በየነ (/) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ችግሩን ለመፍታት ያልተሞከረ ጥረት እንደሌለና በግብርና ሚኒስቴር በኩልም ጥረት ቢደረግም፣ በሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን በኩል ከደኅንነት ጋር በተገናኘ ለዓመታት የተያዙትን አውሮፕላኖች ወደ ሥራ ማስገባት አልተቻለም።

የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ድርጅት በአፍሪካ በቆላ ዝንብ ከተወረሩ አገሮች ኢትዮጵያን እንደ ማዕከል ቆጥሮ  በመጀመርያ የሰጠ ቢሆንም፣ አውሮፕላኖቹን ወደ ሥራ ማስገባት ባለመቻሉ የፓርላማውንገዛ እንደሚሹ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

 ‹‹የአርብቶ አደሮችን የቁም እንስሳት በከፍተኛ ሁኔታ እየጎዳ የሚገኘውን የቆላ ዝንብ ለማስወገድ፣ የሚያግዙት አውሮፕላኖች ተንቀሳቅሰው እንዲሠሩ የሚፈቅድ እንዲዘጋጅልን  እንጠይቃለን፤›› ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል።

የገንዲ በሽታ አብዛኞቹን የቁም እንስሳትን የሚያጠቃ ሲሆን፣ በሽታውን የሚያስተላልፈው የቆላ ዝንብ በተለይም በምዕራብ ኢትዮጵያ በእንስሳት ላይ ቀላል የማይባል ችግርየፈጠረ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በበሽታው የተጠቁ እንስሳት ምንምይነት ጥቅም አይሰጡም ሲሉ አስረድተዋል።

እንደ ዳኛቸው (ዶ/ር) ወደ አገር ቤት የገቡት ሰው አልባ አውሮፕላኖች የሴትና የወንድ የቆላ ዝንቦች በቤተ ሙከራ በማራባትና ወንዶችን በመለየት በጨረራ አማካይነት በማምከን፣ የመከነውን ዝርያ ወደ ጫካ ወስዶመልቀቅ እንዳይራቡ ለማድረግ ጥቅም ይሰጣሉ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...