Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊከ1.4 ሚሊዮን በላይ የመሬት ይዞታዎችን በአምስት ዓመታት ለመመዝገብ ቢሠራም ክንውኑ 435 ሺሕ...

ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የመሬት ይዞታዎችን በአምስት ዓመታት ለመመዝገብ ቢሠራም ክንውኑ 435 ሺሕ ብቻ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

ላለፉት አምስት ዓመታት ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የመሬት ይዞታዎችን በዘመናዊ መንገድ ለመመዝገብና ለማረጋገጥ ታቅዶ ሥራ ቢጀመርም፣ 435 ሺሕ ይዞታዎች ብቻ በሥርዓቱ መካተታቸውን፣ የፌዴራል የከተማ መሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው ይኼንን የገለጸው የአምስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ፣ ከክልሎችና ከሁለቱ የከተማ አስተዳዳሮች ተወካዮች ጋር ሐሙስ ታኅሳስ 22 ቀን 2013 ዓ.ም. በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተደረገ የፓናል ውይይት ነው፡፡

ሐዋሳ፣ መቀሌ፣ ባህር ዳር፣ ድሬዳዋና ሐረርን ጨምሮ በ18 ከተሞች የመሬት ይዞታ የመመዝገብና የማረጋገጥ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ፣ የፌዴራል የመሬትና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ሴታ ተናግረዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመሬት መረጃ አያያዝ ዘመናዊ ባለመሆኑ ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ሕገወጥ አሠራሮች ባለፉት ዓመታት ጎልተው እንደታዩ ጠቁመዋል፡፡ በዘላቂነት ችግሮቹን ለመፍታት የካዳስተር ሥርዓት ተግባራዊ ሲደረግ መቆየቱን የጠቆሙት ዋና ዳይሬክተሩ፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታትም ዕቅዱ ተግባራዊ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡  

የካዳስተር ምዝገባ በዋናነት በአራት ከተሞች ማለትም በሐዋሳ፣ በአዳማ፣ በባህር ዳርና በመቀሌ መካሄዱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ በካዳስተር አገልግሎት የመሬት ይዞታ ለመመዝገብና ለማረጋገጥ በአምስት ዓመታት ውስጥ ከታቀደው በታች መሥራቱን ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመው፣ ከታቀደው ውስጥ 30 በመቶ ያህሉ ብቻ ተፈጻሚ ሆኗል ብለዋል፡፡

በዋነኛነት እንደ ችግር የተጠቀሱትም በዘርፉ ያሉ አመራሮች ያላቸው የክህሎት ክፍተት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ለዘርፉ ያለው የትኩረት አናሳነትና በቴክኖሎጂ የታገዘ አለመሆኑ ናቸው፡፡ በዚህም ሳቢያ የተሠራው ሥራ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል ሲሉ አክለዋል፡፡

ኤጀንሲው ችግሮቹን በመቅረፍ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በ60 ከተሞች ከሦስት ሚሊዮን በላይ የከተማ መሬት ይዞታዎች ለመመዝገብ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ የመሬት ይዞታ የማረጋገጥና የመመዝገብ ሥራ በዋናነት ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ፣ ዘመናዊ የመሬት አስተዳደር ሥርዓት ለመዘርጋትና የዜጎችን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ የመጀመርያው አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ570,000 የመሬት ይዞታዎች ውስጥ 412,056 መመዝገቡን ጠቁመው፣ ከሌሎች ክልሎች የተሻለ አፈጻጸም እንዳለው አስታውቀዋል፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀጥሎም የደቡብ፣ የኦሮሚያ፣ የአማራ፣ የትግራይ ክልሎች በመሬት ይዞታ ምዝገባ አፈጻጸም፣ በየደረጃ መቀመጣቸውን የአምስት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርቱ ያሳያል፡፡   

ያደጉ አገሮች የመሬት ይዞታ ምዝገባና ማረጋገጥ ከ100 ዓመታት በፊት መጀመራቸውን ያስረዱት አቶ ወንድሙ፣ ዘመናዊ አሠራር መኖሩ ቀልጣፋና ፍትሐዊ አገልግሎት እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ ለመሬት ይዞታ ማነቆ ምክንያቱ ዘመናዊ የሆነ አሠራር፣ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የዕውቀትና የሕግ ማዕቀፎች አለመኖር መሆኑን ገልጸው፣ ዘርፉ እንዳይዘምንና አንድ ዕርምጃ ወደፊት እንዳይሄድ እንዳደረገውም ጠቁመዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...