Thursday, June 13, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ብሔራዊ ባንክ የእናት ባንክ ፕሬዚዳንት ሹመትን አፀደቀ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የእናት ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ያጫቸውን የአቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ ሹመት አፀደቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ ሹመት ማፅደቁን ለእናት ባንክ በደብዳቤ ያስታወቀው፣ ዓርብ ታኅሳስ 23 ቀን 2013 ዓ.ም. መሆኑ ታውቋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ የባንኩ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲያገለግሉ የተሰየሙት ባንኩን በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ወንድወሰን ተሾመ ኃላፊነታቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አቶ ኤርሚያስ የእናት ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ከመሰየማቸው ቀደም ብሎ በምክትል ፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡ የእናት ባንክ ቆይታቸውን ጨምሮ በባንክ ኢንዱስትሪው ውስጥ የ 20 ዓመታት የአገልግሎት ልምድ አላቸው፡፡

እናት ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ውስጥ ሦስት ፕሬዚዳንቶችን ሰይሟል፡፡ የባንኩ የመጀመርያ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ፋሲካ ከበደ ሲሆኑ፣ እሳቸውን ተክተው ደግሞ አቶ ወንድወሰን በፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ አቶ ኤርሚያስ ሦስተኛው ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡፡     

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች