Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየኦሊምፒክ ሥራ አስፈጻሚ እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት ይቀጥላል

የኦሊምፒክ ሥራ አስፈጻሚ እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት ይቀጥላል

ቀን:

ተቋሙ የውኃ ፋብሪካ ባለቤት ሊሆን ነው

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ 45ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ባለፈው እሑድ በሐዋሳ አከናውኖ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል፡፡ ጉባዔው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ምክንያት መራዘሙን ተከትሎ አሁን በሥራ ላይ የሚገኘው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ማግስት በኃላፊነት እንዲቀጥል ወስኗል፡፡

የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) ዓምና ሊያካሂደው የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል፡፡ አይኦሲ የቶኪዮ ኦሊምፒክ ስያሜውን እንደያዘ በመጪው ክረምት በ2021 የውድድር ዓመት (ከስድስት ወራት በኋላ) እንደሚያካሂድም ይጠበቃል፡፡

ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ከቀደሙት ዓመታት በተለየ መልኩ የተለያዩ ዝግጅቶችን  ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የሥራ አመራር ቦርድ፣ ምንም እንኳ የአገልግሎት ጊዜው አሁን ላይ ቢጠናቀቅም፣ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚው ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የጀመራቸውን ዝግጅቶች ማስቀጠልና ለውጤት ማብቃት ስላለበት፣ ጉባዔውም ይህንኑ በመረዳት እስከ ውድድሩ ማግስት ድረስ አመራሩ በያዘው ኃላፊነት እንዲቀጥል ወሳኔ አሳልፏል፡፡

የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ፕሬዚዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር)፣የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) ጉባዔ ባስተናገደችበት ማግስት አዲስ በተዋቀረው የሲዳማ ክልል በሐዋሳ ከተማ ጉባዔውን ማካሄዱ ልዩ እንደሚያደርገው ተናግረው፣ አኖካ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ የወሰነውን የ2022 የአፍሪካ ወጣቶች ኦሊምፒክን የሲዳማ ክልል እንዲያዘጋጅ መደረጉ የውሳኔውን ትክክለኛነት ማሳያ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ከ120 በላይ ብሔራዊ አትሌቶችን በሆቴል አሰባስቦ ዝግጅት የጀመረው ከስምንት ወር በፊት መሆኑን ለጉባዔው ያስረዱት ዶ/ር አሸብር፣ ከዝግጅቱ ጎን ለጎን የገቢ ማሰባሰብ ሥራዎችን ኅብረተሰቡን ባማከለና ዘመኑን የሚመጥን ሥርዓት (ሲስተም) በመዘርጋት ተሻጋሪ የሆነ ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝም ለጉባዔው አስተረድተዋል፡፡

ኮሚቴው ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ጎን ለጎን ብሔራዊ ተቋሙ የራሱ የገቢ ምንጭ ይኖረው ዘንድ በሰሜን ሸዋ ደብረ ብርሃን አካባቢ በማስገንባት ላይ የሚገኘው የውኃ ፋብሪካ የቅድመ ዝግጅት ሥራው ተጠናቆ ምርት መጀመር በሚያስችል ሒደት ላይ እንደሚገኝ  አሸብር (ዶ/ር) ለጉባዔው አስረድተዋል፡፡

ለጉባዔው ሌላው የቀረበው ጉዳይ የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) በቅርቡ በአዲስ አበባ ባካሄደው ጉባዔ መደሰቱን በመግለጽ፣ ቀጣይ መደበኛ ጉባዔውን እንደገና በአዲስ አበባ ለማካሄድ ለኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ጥያቄ ማቅረቡ ይገኝበታል፡፡ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ጥያቄውን መነሻ አድርጎ ውሳኔውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር አጠቃላይ ሁኔታዎቹን የሚያሳውቅ እንደሚሆን አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ለጉባዔው አብራርተዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...