Tuesday, March 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናረቂቅ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕጉ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር እንዲሻሻል ጥሪ ቀረበ

ረቂቅ የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕጉ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር እንዲሻሻል ጥሪ ቀረበ

ቀን:

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሸን (ኢሰመኮ) ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የወንጀል ሥነ ሥርዓትና የማስረጃ ሕግ (Criminal Procedure Code and Evidence Law) በርካታ ድንጋጌዎች ከሰብዓዊ መብቶች ሕግና መርሆች አንፃር ሊሻሻሉ እንደሚገባ፣ ማክሰኞ ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ጥሪ አቀረበ፡፡

 ኮሚሽኑ ይፋ ባደረገው ባለ 33 ገጽ ሪፖርት ማሻሻያ እንዲደረግባቸው ካሳሰበው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል   መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪን ለመያዝ፣ ለብርበራና በልዩ የወንጀል ምርመራ ዘዴ ኃይል ሊጠቀም የሚችለው ጥንቃቄ የማድረግ የሕጋዊነት የጥብቅ አስፈላጊነት፣ የተመጣጣኝነትንና አድልዎ ያለ ማድረግ መርሆችን ባከበረ መንገድና ሌላ አማራጭ መንገድ የሌለ መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነና በዚህ ረገድ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ሥነ ሥርዓትም በግልጽ ሊደነገግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

በወንጀል የተጠረጠረ ወይም የተያዘ ሰው የቃል አቀባበል ሒደትን ጨምሮ በማቆያ ቤት ወይም በእስር ወቅት ኢሰብዓዊ አያያዝ እንዳይፈምበትና ተፈሞም ሲገኝ ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ሊካተቱ የሚገባ መሆኑን አሳስቧል፡፡  

ለጥቃት ተጋላጭ የሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች እስር መያዝ፣ በምርመራ፣ በክስ እንዲሁም ምስክርነት በመስጠት ደት ሰብ መብቶቻቸውን፣ ክብራቸው ልዩ ፍላጎቶቻቸውን የበለጠ ሊያስከበሩ የሚያስችሉ ማሻሻያዎች ሊካተቱ እንደሚገባ አስገንዝቧል፡፡

ሕፃናት ከእናታቸው ጋር የሚታሰሩበትን ሁኔታ ለማስቀረት  ነፍሰ  ጡር  ለሆነች  ሴት  ወይም  ከዘጠኝ  ዓመት  በታች  የሆነ  ሕፃን፣  ወይም  የምንትንከባከበው  የአካል  ጉዳተኛ  ልጅ  ላላት  እናት  የዋስትና  መብት  ወዲያውኑ  እንዲፈቀድና  በጥፋተኝነት  ፍርድ  ጊዜም  ከእስር  ውጪ  ያለ  ቅጣት (Non-Custodial Measures)  በአማራጭነት  እንዲወሰድ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ማንኛውም  የታሰረ  ሰው  በተጠረጠረበት  ወይም  በተከሰሰበት  ወንጀል  ጥፋተኛ  ሆኖ  ቢገኝ  ሊጣልበት የሚችለውን የመጨረሻውን  የእስር  ቅጣት  እርከን  ያህል በእስር የቆየ እንደሆነ ወዲያውኑ ሊለቀቅ የሚገባ መሆኑን፣ እንዲሁም  ለሕገ ወጥ መያዝ ወይም እስር የተዳረገ ሰው ካሳ  የሚያገኝበት ሥነ ሥርዓት ሊደነገግ የሚገባ መሆኑን ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ካቀረባቸው ነጥቦች መካከል  ናቸው፡፡

ኮሚሽኑሪፖርቱ በአጠቃላይ 30 በላይ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ የማሻሻያ ምክረ ሐሳብ ከእነ ማብራሪያዎቹ ያቀረበ መሆኑን፣ ለምክር ቤቱ ሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ /ቤት ቀርቧል

 በሌላ በኩል ረቂቅ ሕጉ ከሰብዓዊ መብቶች አንፃር በርካታ ጠንካራኖች እንዳሉትና ነዚህም የወንጀል ምርመራ ዓላማ እውነትን ማውጣት መሆኑን፣  መካሄድና መጠናቀቅ ያለበትም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር ተጠርጣሪው ሳይያዝ መሆኑን በግልጽ መደንገጉን፣ በስህተት የተሰጠ ፍርድ እንደገና የሚመረመርበት ሥነ ሥርዓት መደንገ የሚሉትን ይጨምራሉ

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሸነር ዳንኤል በቀለ (/ር)፣ ‹‹ረቂቅ ሕጉ በርካታ ጠንካራ ጎኖች ቢኖሩትም፣ በኮሚሽኑ ሪፖርት የተመለከቱትን የማሻሻያ ምክረ ሐሳቦች በማካተት ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ግዴታዎች ጋር የተጣጣመ ሕግ ማውጣት የግድ አስፈላጊ ነው፤›› ማለታቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

‹‹ከኦነግ ሸኔ ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት አለን›› ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ

መንግሥት ከ‹‹ኦነግ ሸኔ››ጋር ያለውን ግጭት በሰላም ለመፍታት ከፍተኛ ፍላጎት...

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...