Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምበአሜሪካ የታጠቁ ቡድኖችም ያደርጉታል የተባለው ተቃውሞ

በአሜሪካ የታጠቁ ቡድኖችም ያደርጉታል የተባለው ተቃውሞ

ቀን:

አሜሪካ በ2020 እንዳከናወነችው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፈተና የሆነባትን  ምርጫ ከዚህ ቀደም አላስተናገደችም፡፡ ከአራት ዓመት በፊት በተደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሒላሪ ክሊንተን ጋር ተፎካክረው የአሜሪካ 45ኛ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶናልድ ትራምፕ፣ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ብቻ ሳይሆን በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ጭምርም ነበር አወዛጋቢ ንግግሮችን ሲያደርጉ የከረሙት፡፡

በሥልጣን ዘመናቸው ተሿሚዎቻቸውን ቶሎ ቶሎ በመቀያየር፣ በስደተኞች ጉዳይ፣ በቻይና፣ በዓለም ጤና ድርጅቶች፣ በሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት፣ በፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነትና በሌሎች በርካታ የአገር ውስጥና የውጭ ጉዳዮች ዓለምን አጀብ ያሰኙ ፕሬዚዳንትት ናቸው፡፡ እንዳሻቸው በመናገር የሚታወቁት ትራምፕ ተቃውሞ ያሰነዘሩ ውሳኔዎችን በማሳለፍም ይታወቃሉ፡፡

አሜሪካ ከሰሜን ኮሪያ ጋር የነበራትን እጅግ የሻከረ ግንኙነት ለመቀልበስ ባደረጉት ጥረት የተመሠገኑት ትራምፕ፣ በፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ካሳለፏቸው ውሳኔዎችና እንዳሻቸው ከመናገራቸው አንፃር ለሚዲያውና ለየዘርፉ ባለሙያዎች የሠላ ትችት የተጋለጡም ናቸው፡፡

የዓለምን ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ላንቀጠቀጠው የኮቨድ-19 ወረርሽኝ ባላቸው የተቃለለ ምልከታ፣ አሜሪካውያንን መከራ ውስጥ ከተዋል የሚባሉት ትራምፕ፣ በ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ መሸንፋቸው ደግሞ በአሜሪካ ታሪክ እንዳሁኑ ተሰምቶና ተደርጎ የማያውቅ ድርጊት ውስጥ መሳተፋቸው የዴሞክራሲ ቁንጮ የምትባለውን አሜሪካ ትዝብት ላይ ጥሏል፡፡

በአሜሪካ የታጠቁ

 

ትራምፕ የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊከናወን ቀናት ሲቀሩት ነበር ምርጫው ተጭበርብሯል ማለት የጀመሩት፡፡ ምርጫው ተጠናቆ የ84 ዓመቱ ጆ ባይደን ተመራጭ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ ደግሞ፣ የትራምፕ አካሄድ እሳቸው፣ ‹‹ዴሞክራሲያዊ መብቴን እየተጠቀምኩ ነው፤›› ብለው ባመኑበት መንገድ 60 የምርጫ ተጭበርብሯል ክሶችን ለፍርድ ቤት አቅርበው ውድቅ ተደርጎባቸዋል፡፡

በጆርጂያ ግዛት በነበረው ምርጫ ትራምፕ ምርጫ እንዲጭበረበር በስልክ የተለማመጡበት መረጃ መውጣቱም የሰሞኑ ወሬ ነበር፡፡ ብዙ ፈተናዎች የገጠሙት ምርጫ ግን ዛሬም ተግዳሮቶቹ አላባሩም፡፡ የጆ ባይደንን ምርጫ ለማፅደቅ ባለፈው ሳምንት በካፒቶል ሂል የተሰበሰቡ የሴኔት አባላት ድንገት በትራምፕ ደጋፊዎች ተወረዋል፡፡ ዕቃ ተሰባብሯል፡፡ ንብረት ተዘርፏል፡፡ የአራት ሰዎች ሕይወት ስለማለፉም ሲኤንኤን አሥፍሯል፡፡

ትራምፕን ደግፈውና ጆ ባይደንን አውግዘው ተቃውሞ የወጡ ሠልፈኞች ካለፈው ሳምንት በባሰ ሁኔታ በ50 የአሜሪካ ግዛቶች የተመራጭ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በዓለ ሲመት በቀጣዩ ሳምንት ረቡዕ ጥር 12 ቀን 2013 ዓ.ም. ከመካሄዱ አስቀድሞ ተቃውሞ እንደሚወጡ የአሜሪካ የደኅንነት ቢሮ (ኤፍቢአይ) አስታውቋል፡፡

የታጠቁ ቡድኖች ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በ50 የአሜሪካ ግዛቶች ለተቃውሞ እንዲወጡ መረጃ ማግኘቱን የጠቆመው ኤፍቢአይ የደኅንነት ክፍሉ የባይደንን በዓለ ሲመት ደኅንነት ለማስጠበቅ ቁጥጥሩን አጠናክሯል ብሏል፡፡ ሆኖም የታጠቁ የትራምፕ ደጋፊዎች ለታቃውሞ ይወጣሉ መባሉ ሥጋት ፈጥሯልም ተብሏል፡፡  

ጆ ባይደንና ምክትል ተመራጭ ፕሬዚዳንቷ ካማላ ሐሪስ በካፒቶል ሒል በሚያደርጉት በዓለ ሲመትና የመጀመርያ ንግግር፣ ከሕንፃው ውጪ ቢሆንም ሥጋት እንደሌላቸው አስታወቀዋል፡፡

የደኅንነት አካላትም፣ ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የኮንግረስ አባላት የባይደንን የምርጫ ውጤት ለማፅደቅ በካፒቶል ሒል በተሰበሰቡበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች የሕንፃውን የታችኛው ክፍል ከፍተው እንደገቡትና ጥፋት እንደፈጸሙት ዓይነት ሁከት ዳግም እንደማይከሰት ገልጿል፡፡

በአሜሪካ ሊደረግ የታሰበው ተቃውሞ

የጆ ባይደን በዓለ ሲመት ከመደረጉ አስቀድሞ ተቃውሞ ሊደረግና ጥቃቶች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ የአሜሪካ የደኅንነት አካላት አሳስበዋል፡፡

የትራምፕ ደጋፊዎች በበይነ መረብ ኔትወርክ የፊታችን እሑድ ተቃውሞ ጠርተዋል፡፡ በጥሪያቸው በአሜሪካ በሚገኙ ግዛቶች የታጠቁ ደጋፊዎች ጭምር እንዲሳተፉ መወትወታቸው ማቅረባቸው ሥጋት ፈጥሯል፡፡ በባደን ባዕለ ሲመት ዕለትም በዋሽንግተን ተቃውሞ እንዳደረገም ተነግሯል፡፡

ኤቢሲ ኒውስና ሌሎች መገናኛ ብዙኃን ዘግበውታል ብሎ ቢቢሲ እንዳሠፈረው፣ አንድ ቡድን የባይደን በዓለ ሲመት ከመከናወኑ በፊትም ሆነ በዕለቱ ትራምፕ ከሥልጣን ከተሰናባቱ ተቃዋሚዎች የመንግሥት ተቋማትንና የአካባቢያዊና ፌዴራል ፍርድ ቤቶችን በተቃውሞ እንዲያጥለቀልቁ ጥሪ ቀርቧል፡፡

ትራምፕ በበኩላቸው እስከ ጥር 16 ድረስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፅድቀዋል፡፡ ይህም ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቀልበስ ታቅዶ ነው ተብሏል፡፡ በመጪው ሰንበትም ከአሥር ሺሕ በላይ ብሔራዊ የክብር ዘብ አባላት ወደ ዋሽንግተን የሚገቡ ሲሆን፣ ተጨማሪ አምስት ሺሕ መዘጋጀቱም ተዘግቧል፡፡

የዋሽንግተን ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር፣ ባለፈው ሳምንት በካፒቶል ሒል ‹‹ያልተጠበቀ የሽብር ጥቃት›› ከተከሰተ በኋላ የተጠናከረ የደኅንነት አካል እንዲሰማራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አሜሪካውያን ለበዓለ ሲመቱ ዋሽንግተን ከመምጣት እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...