Saturday, May 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልየሀገር ፍቅር ቴአትር ዳግማዊ ዕድሳት

የሀገር ፍቅር ቴአትር ዳግማዊ ዕድሳት

ቀን:

በኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ከሚባሉ ቴአትር ቤቶች አንዱ መሆኑ የማይዘጋ ነው፡፡ ከአመሠራረቱ ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ ዓመታት አገልግሎት የሰጠ ሲሆን ከውስጡም በርካታ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መውጣት ችለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅትም እየወጡ ይገኛል፡፡

86 ዓመታትን ያስቆጠረው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ‹‹ሀገር በሀገር ፍቅር ይታደስ›› በሚል መሪ ቃል ጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም. ላይ የተለያዩ የመንግሥት ባለሥልጣናት በተገኙበት የሕንፃ ዕድሳት መርሐ ግብሩን በይፋ ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቁ መንገሻ የዕድሳት መርሐ ግብሩን አስመልክቶ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ በመደበው 20 ሚሊዮን ብር አማካይነት ዕድሳቱ ይከናወናል፡፡

- Advertisement -

ቴአትር ቤቱ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆንና ከዚህ በፊት የነበሩትን ታሪካዊ ቅርሶች ተጠብቀው እንዲቀጥሉ በማድረግ ዕድሳቱ ይደረጋል፡፡ የተለያየ መጓተቶች ካልተፈጠረ በስተቀር ዕድሳቱ ለሰባት ወር ያህል የሚቆይ ሲሆን ዕድሳቱም እንደተጠናቀቀ በውስጡ የራሱ የሆነ ሙዚየም እንደሚደራጅለት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊትም መሠረታዊ የሆነ ዕድሳት ያልተደረገለት መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት በተፈለገው መጠን በመገንባት ያሉትን ታሪካዊ ቅርሶች ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ቴአትር ቤቱ በርካታ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሲጠቀሙባቸው የነበሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች፣ አልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶችን የያዘ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም የተለያዩ ፕሮግራሞችን ለማካሄድ ሲፈለግ ሌሎች አዳራሾችን መከራየት የግድ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የነበሩት ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) አማካይነት የተሰጠ 900 ካሬ ሜትር መሬት ርክክብ ሲደረግ ደረጃውን የጠበቀ ቴአትር ቤት እንደሚገነባ ገልጸዋል፡፡

በዕድሳቱ ማስጀመርያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ አቶ ዣንጥራር ዓባይ እንደተናገሩት፣ ቴአትር ቤቱ አንጋፋ አርቲስቶችን ያፈራ፣ ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረና እንደ አገር ቅርስ የሚታይ ቦታ በመሆኑ ታሪካዊ ዳራውን ሳይለቅ በሚደረገው ዕድሳት የከተማ አስተዳደሩ ባለው አቅም ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ዕድሳቱም በታሰበለት ወቅት እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አመራሮች ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባቸውም ሳያሳስቡ አላለፉም፡፡

ቴአትር ቤቱ ፋሺስት ጣሊያን ኢትዮጵያ በ1928 ዓ.ም. ለመውረር በተዘጋጀበት ዋዜማ በሐምሌ 1927 ዓ.ም. የተቋቋመው ‹‹የኢትዮጵያ ሀገር ፍቅር ማኅበር›› በሚል ስያሜ ነበር፡፡

ከአፍሪካ ሀገር በቀል ቴአትር ቤቶች አንጋፋ የሆነው ሀገር ፍቅር ቴአትር ከአሥራ አምስት ዓመት በፊት በአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ ነባሩን ሕንፃ በጠበቀ መልኩ መታደሉ ይታወሳል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...