Sunday, March 3, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለብዙኃን ቀረቤታ ባላቸው የተዘነጋው ኮቪድ-19

ለብዙኃን ቀረቤታ ባላቸው የተዘነጋው ኮቪድ-19

ቀን:

‹‹ጤና ይስጥልኝ፡፡ የኮቪድ ፅኑ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ መዘናጋት ብዙዎችን አሳጥቶናል፡፡ ጥንቃቄ ብዙዎችን ዛሬን ያሻግራል፡፡ እባክዎትን ማስክዎን ያደርጉ፣ ሕይወትዎን ያትርፉ!››

ይህ ስልክዎትን ለወዳጅ ዘመድዎ ሲመቱ ወደ ጆሮዎ የሚንቆረቆረው የኢትዮ ቴሌኮም የጥሪ ድምፅ ያለ ምክንያት አይደለም የተለቀቀው፡፡ ይልቁንም ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ሳያንስ እርስዎ በመዘናጋትም ሕይወትዎን እንዳያጡ አሊያም እንዳይታመሙና እንዳይሠቃዩ ለማስገንዘብ ነው፡፡

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ተከሰተ በተባለበት መጋቢት 2012 ዓ.ም. የመጀመርያዎቹ ስድስት ወራት እንዳሁኑ ግንዛቤው የተሻለ ባይሆንም፣ ፍርኃት በወለደው ጥንቃቄ ብዙዎች የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ሲተገብሩ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በተለይ በአዲስ አበባ ተቋማትን በከፊል ከመዝጋት፣ የትራንስፖርት የመጫን አቅምን በግማሽ ከመቀነስ አንስቶ የተሠሩ ሥራዎች መልካም የጥንቃቄ ትግበራዎች እንዲደረጉ አስችሎም ነበር፡፡

አሁን ላይ ህ ተዘንግቷል፡፡ በወቅቱ በየመገናኛ ብዙኃን በስፋት ይተላለፉ የነበሩ መልዕክቶች ዛሬ ደብዝዘዋል፡፡ የኅብረተሰቡን ሥነ ልቦና የሚሰልቡ በርካታ አገራዊ አጀንዳዎች ቢኖሩም፣ ችላ ሊባል የማይገባቸው የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶች ተዘንግተዋል፡፡

ክልሎች ደግሞ ይበልጥ ትተውታል ማለት ይቻላል፡፡ በየብሮድካስት ሚዲያው የክልሉ በሚያስተላልፋቸው ፕሮግራሞች የኮቪድ-19 መከላከያ አንዱ የሆነውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ አለማድረግ ማሳያ ናቸው፡፡

በመቐለ፣ በባህር ዳር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብና በሌሎችም የሚከወኑ በዓላትም ይሁን ዝግጅቶች ላይ ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክ ያደርጉ›› የሚለው በብዛት ሲተገበር አይስተዋልም፡፡    

በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ ፕሮግራሞች፣ ማስታወቂያዎች፣ ታዋቂ ሰዎችና ባለሥልጣናት የሚገኙባቸው መድረኮች ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን ለኅብረተሰቡ ለማድረስ ዓይነተኛ ሚና አላቸው፡፡

ሆኖም ታዋቂና በሕዝቡ በብዛት የመታየት ዕድል አላቸው ከምንላቸው ሰዎች ማስክ ያለመጠቀም፣ ርቀት ያለመጠበቅና አንዳንዴም ተቃቅፎ ሰላምታ እስከመለዋወጥ የሚደርሱ መኖራቸውም ታይቷል፡፡

የጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጥር 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ያስጀመሩት የስድስት ወራት ንቅናቄም ይህንኑ መዘናጋት ለማስቀልበስ ነው፡፡

የንቅናቄው ዓላማ በኅብረተሰቡ፣ በታዋቂ ሰዎችና በመገናኛ ብዙኃን እየተዘነጋ የመጣው ኮሮና ቫይረስ ላይ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለማስቻል መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የመዘናጋት ውጤቱ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ዜጎች ቁጥር በየቀኑ እንዲጨምር ማድረጉ ብቻ ሳይሆን፣ ፅኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡ ሰዎች ቁጥርም ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡    

የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) የኮሮና ቫይረስ፣ በድጋሚ መባባሱን ተከትሎ ለኅብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያደርጉ›› የሚል ንቅናቄ በአዲስ መልክ ማስጀመር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አፅንኦት ሰጥተውታል፡፡

የጤና ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያስጀመሩት ኮሮና ቫይረስን የመከላከል ንቅናቄ በሌሎች ክልሎችም በስፋት እንደሚጀመር ተገልጿል፡፡

ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ኅብረተሰቡ ግንዛቤ በይበልጥ እንዲዳብር በዚህ የማይመለስ ከሆነ በሕግ አግባብ የተቀመጡ ዕርምጃዎች ተግባራዊ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያዎች አተገባበር በመንግሥት ባለሥልጣን ጭምር በከፍተኛ ሁናቴ መዘናጋትና ችላ ባይነት መስተዋሉም ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዮሐንስ ጫላ (ዶ/ር) እንደተናገሩት፣ በቫይረሱ ሕይወታቸው ካለፉ ሰዎች ውስጥ 70 በመቶዎቹ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡  ይህም ምክንያት የነበረው የኮሮና ቫይረስ ጥንቃቄ አሁን ላይ በእጅጉ መቀነሱን ያሳያል ተብሏል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙት ሰዎች ውስጥ 57 በመቶዎቹም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አቶ ዣንጥራር ዓባይ፣ የተጀመረውን ንቅናቄ ሁሉም በትጋት መተግበር እንዳለበት ገልጸው፣ አሁን ያለውን ችላ ባይነት ማቆም ካልተቻለ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል ብለዋል፡፡ በዓለም ወረርሽኙ በስፋት እየተሠራጨ ከሚገኝባቸው አገሮች ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ ናት ያሉት የጤና ሚኒስትሯ መከላከልና ጥንቃቄውን ማጠናከር ቀዳሚ ዕርምጃ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በኮሮና ቫይረስ ከሚመረመሩ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙ ጥቂት እንደነበሩ፣ አሁን ላይ ከሚመረመሩ ሰዎች በቫይረሱ የሚያዙት ቁጥር ከፍ ማለቱን ዶ/ር ሊያ ጠቁመዋል፡፡

ለዚህም ማስክ የሚጠቀሙ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየቀነስ በመምጣቱና ሌሎች ቫይረሱ እንዳይሠራጭ የሚያደርጉ ጥንቃቄዎች መቅረታቸው እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡

በኢትዮጵያ እስከ ጥር 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ [መረጃው እስከ ጥር 7 ቀን ምሽት 1፡00 ሰዓት ድረስ ያልተቀየረ] ከተመረመሩ 1,870,415 ሰዎች ውስጥ 129,922 በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

የሟቾች ቁጥር 2,008 ሲደርስ ከበሽታው ያገገሙት 114,749 ናቸው፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸው 13,163 ሲሆኑ፣ በፅኑ የታመሙት 229 መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...