Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ የክልሎችን ትብብር ጠይቆ ምላሽ አለማግኘቱን አስታወቀ

ምርጫ ቦርድ የክልሎችን ትብብር ጠይቆ ምላሽ አለማግኘቱን አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከስምንት ክልሎችና ከሁለት የከተማ አስተዳደሮች የሚያስፈልጉትን ድጋፎች በዝርዝር የጠየቀ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ከክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የተሰጠው ምላሽ እንደሌለ አስታወቀ፡፡

ቦርዱ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ምንም እንኳን ክልሎቹ ለጥያቄዎቹ ምላሽ እንዲሰጡ የተጠየቁት እስከ ጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ቢሆንም፣ ከክልሎቹና ከተማ አስተዳደሮቹ ምንም ምላሽ ማግኘት አልተቻለም ብሏል፡፡

‹‹በክልሎች ቢሮ ለመክፈት የሚያስፈልግ ዝግጅት በደብዳቤ በመጠየቅ ለጥር 10 ቀን 2013 ዓ.ም. እንዲያሳውቁ ጥያቄ የቀረበ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ ይህንን ዝግጅት አስመልክቶ ምላሽ ያቀረበ የክልል አስተዳደር የለም። በመሆኑም በደብዳቤ የተገለጹት አስፈላጊ የምርጫ የክልል ቢሮዎችን ለመክፈት የሚያስፈልጉ ትብብሮች ለምርጫው ሒደት አስፈላጊነታቸውን በመገንዘብ ክልሎች ትብብራቸውን እንዲያፋጥኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 161 የተቀመጠውን የመተባበር ግዴታቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን፤›› ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ፣ ‹‹ማንኛውም ሰው ይህን አዋጅ በሥራ ላይ ለማዋል የመተባበር ግዴታ አለበት፤›› ሲል ይደነግጋል፡፡

ቦርዱ በመግለጫው ክልሎች እንዲያዘጋጁለት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 33 የምርጫ ክልል ቢሮዎችና ሦስት የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 47 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ አንድ የዞን ማስተባበሪያ ቢሮና የሥልጠና ቦታ፣ የሶማሌ ክልል 72 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 11 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ የጋምቤላ ክልል 14 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ ሦስት የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ የደቡብ ክልል 113 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 16 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ የሐረሪ ክልል ሦስት የምርጫ ክልል ቢሮዎች አንድ የዞን ማስተባበሪያ ቢሮና የሥልጠና ቦታ፣ አፋር ክልል 32 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ አምስት የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ አማራ ክልል 138 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 12 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች፣ የሲዳማ ክልል 19 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ አንድ ዞን ማስተባበሪያ ቢሮና የሥልጠና ቦታ፣ የኦሮሚያ ክልል 179 የምርጫ ክልል ቢሮዎች፣ 20 የዞን ማስተባበሪያ ቢሮዎችና የሥልጠና ቦታዎች ናቸው፡፡

ክልሎቹ ምላሽ ያልሰጡ ቢሆንም ቦርዱም በጥያቄው ለክልሎች ለዕቅድና ለአፈጻጸም ያመቻቸው ዘንድ፣ የምርጫ ክልሎች ዝርዝርና ቢሮአቸው የሚቋቋምባቸው ከተሞች ዝርዝር፣ የዞን ማስተባበሪዎች ዝርዝርና ቢሯቸው የሚቋቋሙባቸው ከተሞችን ዝርዝር፣ እንዲሁም ቦርዱ ያወጣውን ረቂቅ የምርጫ ሰሌዳ ኮፒ አብሮ አቅርቧል ሲል ቦርዱ ገልጻል፡፡

ይሁንና ይኼ መዘግየት በምርጫ ሰሌዳው ላይም ሆነ በምርጫው ሒደት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ምን ሊሆን እንደሚችል ቦርዱ አላስታወቀም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...