Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትያለ ቅንጅታዊ አሠራር ብቃታቸው የተረጋገጠ ስፖርተኞችን ማፍራት እንደማይቻል ተገለጸ

ያለ ቅንጅታዊ አሠራር ብቃታቸው የተረጋገጠ ስፖርተኞችን ማፍራት እንደማይቻል ተገለጸ

ቀን:

የስፖርት አካዴሚው የአሥር ዓመት ዕቅዱን አቅርቦ አስገምግሟል

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ በአሥር የስፖርት ዓይነት ሠልጣኞችን ተቀብሎ በማብቃት ለክለቦች በማሸጋገር ታላላቅና ስመ ጥር አትሌቶችን እያፈራ ቢገኝም፣ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሠራር የላላ በመሆኑ፣ ተቋሙ ሙሉ አቅሙን መጠቀም እንዳልቻለ ተገለጸ፡፡ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ከስፖርቱ ባለድርሻ ጋር ጠንካራ ሙያዊ ውይይት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ አካዴሚው ጥር 7 እና 8 ቀን 2013 ዓ.ም. በሐዋሳ ባዘጋጀው መድረክ፣ ተቋሙ ሥልጠና መስጠት ከጀመረበት ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በርካታ ተተኪና ወጣት አትሌቶችን በማፍራት በአኅጉራዊና በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ውጤት ማስመዝገብ የቻለ መሆኑ ቢታመንም፣ ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል ትልቅ ድርሻ ያላቸው የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራርና ሚና ዝቅተኛ መሆኑ ተነግሯል፡፡

- Advertisement -

አካዴሚው የአሥር ዓመታት የስፖርት ስትራቴጂካዊ ዕቅድና የ2013 በጀት ዓመት በማዘጋጀት፣ በተለይ ከኮቪድ-19 በፊትና በወረርሽኙ ውስጥ ሆኖ ሲሰጥ የቆየውን ሥልጠና የክልሎች፣ የከተማ አስተዳደሮች፣ የብሔራዊ ፌዴሬሽኖችና አሶሴሽኖች እንዲሁም የክለቦች አመራሮችና ኃላፊዎች በተገኙበት ሙሉ ዕቅዱን አቅርቦ ውይይትና ምክክር እንዲደረግበት አድርጓል፡፡

መንግሥት ለስፖርትና ለመሠረተ ልማቱ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በጀት በመመደብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ለዚህም የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚና የጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከልን በአብነት የጠቀሱት የስፖርት ኮሚሽነሩና ምትላቸው አቶ ኤልያስ ሽኩርና አቶ ዱቤ ጅሎ ናቸው፡፡

ስፖርቱን ለማዘመንና ለማስፋፋት ብሎም ውጤታማ ተወዳዳሪ አትሌቶችን ማፍራት ይቻል ዘንድ፣ ሁሉን አቀፍ የሆነ የስፖርት ሪፎርም መዘጋጀቱ፣ ይህን መነሻ ያደረጉ በርካታ ሥራዎች በማከናወን ላይ መሆናቸውን ያስረዱት ኮሚሽነሮቹ በአሁኑ ወቅት በስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት እየተፈጠረ ይገኛል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የድርጊት መርሐ ግብርና የአሠራር ዕቅዶችን ወደ ታች ለማውረድና ለመሥራት ደግሞ አንዱና ዋነኛው የባለ ድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ በዋናነትም ብሔራዊ አካዴሚው በስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ልዩ ችሎታ ያላቸውን ታዳጊዎች በመመልመልና በማሠልጠን ሁለንተናዊ ብቃታቸው የተረጋገጠ ስፖርተኞችን ማፍራት ዓላማውና ተግባሩ እንደሆነም በዕቅዱ አካቷል፡፡

አካዴሚው በተለይ የአሥር ዓመቱን ዕቅድ ለማሳካት ስምንት ዋና ዋና ግቦችን ያስቀመጠ ሲሆን፣ ዝርዝር አተገባበሩን በሚመለከት ተተንትኖ በድርጊት መርሐ ግብር እንዲሁም ለሚያጋጥሙ ችግሮች የሚወሰዱ የመፍትሔ አቅጣጫዎችና የፋይናንስ ምንጮችን ጭምር አስደግፎ አቅርቧል፡፡ መድረኩ በእያንዳንዱ ዝርዝር ጉዳይ በመምከር መካተት ያለባቸው እንዲካተቱ ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አምበሳው እንየው በበኩላቸው፣ በመድረኩ የቀረቡ አስተያየቶችና ትችቶች ለአካዴሚው ውጤታማነት የሚጠቅሙ በመሆናቸው እንደሚወስዷቸው፣ ሆኖም አካዴሚው ምንም እንኳን በሕግ የተሰጠው ኃላፊነት እንደተጠበቀ፣ በየደረጃው የሚገኙ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነትና ትጋት ለስፖርቱ ዕድገት ወሳኝ እንደሆነ ግን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ እስካሁን ባለው ለአካዴሚው የሚቀርብለት ጥያቄ በአብዛኛው ሜዳና የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሆነ ተናግረው፣ እንደ አገር ለስፖርቱ የሚጠቅሙ በተለይም ከምርምርና መሰል ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ‹‹አግዙን እንተጋገዝ›› የሚሉ የስፖርት ማኅበራት ዕቅድ ቀርቦላቸው እንደማያውቅ ለባለድርሻ አካላቱ አብራርተዋል፡፡

አካዴሚው የአገር ሀብት እንደመሆኑ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ለመሥራት ‹‹ሙሉ ፈቃደኛ ነው›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ከአንዳንድ አመራሮች ከሥልጠና ስታንዳርድ ጋር በተገናኘ በቀረበው አስተያየት፣ ‹‹ችግሩ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚስተዋል ነው፣ የሥልጠና ስታንዳርድ መዘጋጀት ካለበትም በእያንዳንዱ ስፖርት እንደሆነ፣ ለዚህ ደግሞ ቅንጅታዊ ትስስር መፈጠር ይኖርበታል፤›› ብለዋል፡፡    

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...