Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን ከማረጋጋት አንፃር እስከምን ድረስ ተጉዘዋል?

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ገበያን ከማረጋጋት አንፃር እስከምን ድረስ ተጉዘዋል?

ቀን:

በየጊዜው በኢትዮጵያ የሚከሰተውን የዋጋ ንረት፣ የኑሮ ውድነት ኅብረተሰቡ እንዲቋቋመው በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት ምርት በማቅረብ ለማረጋጋት ጥረት ይደረጋል፡፡

ለማረጋጋት የሚደረገው ጥረት ከሚከሰተው የዋጋ ንረት፣ የኑሮ ውድነት አንፃር ሲታይ እዚህ ግባ የማይባል መሆኑን ብዙዎች በምሬት ይናገራሉ፡፡

በዚህ ብቻ ሳይሆን፣ በኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ከሚቀርቡ ምርቶች አቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም፣ ዋጋ ጭማሪና ጥራት ጋር በተያያዘ ተገልጋይ ምሬት እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኅብረት ሥራ በአገር አቀፍ ደረጃ ከ90 ሺሕ በላይ ማኅበራት ከ391 በላይ ዩኒየኖች ይገኛሉ፡፡

በእነዚህ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአጠቃላይ 22.7 ሚሊዮን አባላት አሏቸው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ የሚገኙ 1.1 ሚሊዮን አባላት ያሏቸው፡፡ የማኅበራቱ ቁጥር 2,734 ሲሆኑ 12 ዩኒየኖች ደግሞ በመዲናዪቱ የሚገኙ ሲሆን ሁለት የገንዘብ ቁጠባ ተቋሞች፣ አሥር የሸማቾች ማኅበራት ናቸው፡፡ በዚህም ስድስት ቢሊዮን ብር ካፒታል በኅብረት ሥራ ማኅበራቱ እንደሚንቀሳቀስ የአዲስ አበባ ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ማኅበራቱ የግብርና ምርት፣ የኢንዱስትሪ ምርት እንዲሁም የድጎማ ምርቶች የሚቀርቡ ሲሆን፣ አሁንም ድረስ በዘርፍ የሚታዩ ብዙ ችግሮች እንዳሉ ተጠቁሟል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የዋጋ ንረቶች የሚከሰት ሲሆን፣ ገበያ ከማረጋጋት አንፃር ማኅበራቱ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ይታመናል፡፡

በኅብረት ሥራ ማኅበራቱ ዋጋ ከማረጋጋት በተጨማሪ ከ27 ሺሕ በላይ ዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ እንደሚገኙ ጥር 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ከፍተኛ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከክልል ከተሞች ጋር ስምምነት በማድረግ የሚቀርቡትን ምርቶች ከቦታው በማምጣት የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በመሥራት ላይ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

ከልደታ ክፍለ ከተማ የኦዲት ቡድን መሪ አቶ ሥራዬ ሎዬ ለሪፖርተር እንዳስረዱት፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት አንፃር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ናቸው፡፡

ነገር ግን በዘርፉ ከሚገኙ ችግሮች ውስጥ አንዱ ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት የማያቀርቡ ማኅበራት ጥቂት መሆናቸውን ይገልጻሉ፡፡ በዚህም ማኅበራቱ ያለባቸውን ክፍተቶች፣ ተጠያቂነትና ሌሎች በኦዲት ወቅት ሊታይ የሚችሉ ችግሮችን ለማየት አስቸጋሪ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

በክፍለ ከተማው የሚገኙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት የኦዲት ሪፖርት ማቅረብ ላይ ክፍተቶች መኖሩን ጠቁመው፣ በተመሳሳይ መልኩ ሌሎች ክፍለ ከተሞች ላይ ሊኖር እንደሚችል ይገምታሉ፡፡

የኅብረት ሥራ ማኅበራት ለኅብረተሰቡ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የጠቆሙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ አሥር ቦርድ አመራር፣ በተለይም ገበያን በማረጋጋት ረገድ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ አኳያ ሊቀረፍ የሚገቡ በርካታ ችግሮች በመኖራቸው ሱቆቹን በብዛት በመክፈት፣ የግብርና ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ምርት ከቦታው በማምጣት ችግሩን በቀላሉ መፍታት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡

ሱቆችን በብዛት ለመክፈት ትልቁ ችግር የሆነው የካርታ ጉዳይ ሲሆን፣ ካርታው በንግድና ኢንዱስትሪ ሥር በመሆኑ አንዳንዴም የኅብረት ሥራ ማኅበራት የተባሉ ቦታዎች ጭምር ባለማወቅ በመንግሥት እንደሚወሰድ ከመድረኩ ተነስቷል፡፡

በአዋጅ የተሰጡ ንብረቶችና የብድር አገልግሎቶች፣ የግብርና ምርት አቅርቦት፣ የድጎማ ምርት፣ አምራችና ሸማች የማገናኘት ሥራ ውጤታማ ያለመሆን ችግሮች መኖራቸውን ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ተወካዮች ከቀረቡት ችግሮች መካከል ይገኙበታል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኤጀንሲ፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራቱን በማጠናከር የኅብረተሰቡን ችግር ከመቅረፍ በተጨማሪ ማኅበራቱን በማብዛት የኑሮ ማረጋጋት ላይ ይሠራል ብለዋል፡፡

ማኅበራቱ ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት በተለይም ከአቅርቦት አንፃር ከክልሎች ጋር ስምምነት በማድረግ ችግሮቹን ለመቅረፍ እየተሠራ ይገኛል ተብሏል፡፡

ኤጀንሲው ማኅበራቱ ለኅብረተሰቡ ከሚሰጡ አገልግሎት በተጨማሪ አሁን ያለው የአሠራር ክፍተት ላይ በመሥራት በቀጣይ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለኅብረተሰቡ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር ዓባይ እንደተናገሩት፣ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አቅም ከማሳደግ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡

በዚህም ኅብረተሰቡን ችግር ከመቅረፍ በተጨማሪ የማኅበራቱን አቅም ለማሳደግ እየተሠራ ይገኛል ተብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...