Friday, December 8, 2023

የኢትዮ ሱዳን ድንበር ውጥረትን አስመልክቶ በሁለቱ አገሮች የተሰጡ ይፋዊ መረጃዎች የፈጠሩት ብዥታ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

ኢትዮጵያና ሱዳን የሚዋሰኑት የጋራ ድንበር ሰፊ ቢሆንም፣ በተለይ በሱዳን በኩል አልሻፋቅ በሚል ስያሜ በኢትዮጵያ በኩል በመተማና በሁመራ ድንበር አካባቢ የሚገኘው ለም መሬት ሁለቱን አገሮች በተደጋጋሚ የሚያወዛግብ ነው።

1990ዎቹ መጨረሻ ገደማም ይኸው አካባቢ የውዝግብ መነሻ የነበረና በሁለቱ አገሮች የፀጥታ አካላት መካከልም መሣሪያ ያማዘዘ ነበር።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ 1990ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ተከተስቶ በነበረው ተመሳሳይ የድንበር ውጥረት ማብራራያ እንዲሰጡ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

በፓርላማ መቀመጫ የነበራቸው በተለይም የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት በወቅቱ የተከሰተው የድንበር ግጭት የመወረርና የመደፈር ስሜትጭሮባቸው የነበረ በመሆኑ፣ ማብራሪያውን የሰጡት የወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ይህንን ስሜት ለማስከን የሚችል ሥረ መሠረቱን የዳሰሰ ምላሽ ሰጥተውበት ነበር።

አቶ መለስ በወቅቱ በሱዳን በኩል ለተነሳው የድንበር ጥያቄና ከዚሁ ጋር ተያይዞ ለተፈጠረው መካረር መነሻ ምክንያቱ፣ ሁለቱ አገሮችን የሚያዋስነው ረዥም ኪሎ ሜትር የድንበር ወሰን በሕጋዊ መንገድ ባለመከለሉ ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን ጠቁዋል፡፡

መሠረታዊ ምክንያቱ በወቅቱ የግብፅ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ሆስኒ ሙባረክ በአዲስ አበባ ከተማ ለመግደል የተደረገው ሙከራን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ከወሰደው ወታደራዊርምጃ ውጤት ጋር በማስተሳሰር ምላሽ ሰጥተውበት ነበር።

የግብፁን ፕሬዚዳንት ለመግደል ሙከራ ካደረጉት የውጭ ታጣቂዎች መካከል የሱዳን ዜግነት ያላቸው መሳተፋቸውና የግድያ ሙከራው ሴራ የተጠነሰሰውም ሱዳን ውስጥ መሆኑ የኢትዮጵያን መንግሥት በወቅቱ አስቆጥቶ እንደነበር የገለጹት አቶ መለስ፣ ከሁሉም ነገር በላይ ደግሞ የግድያ ሙከራውን ያደረጉት የውጭ ታጣቂዎች ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የዘለቁት በአወዛጋቢው ድንበር በኩል በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ በግድያ ሙከራው ላይ የሱዳን መንግሥትን እንድትጠረጥር እንዳደረጋት አስረድተዋል።

የግድያ ሙከራውን ካደረጉት ታጣቂዎች መካከል የተወሰኑት ሲገደሉ፣ ያልተያዙት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ በዘለቁበት ድንበር በኩል አድርገው ወደ ሱዳን ማምለጣቸውን ገልጸዋል።

በዚህ ወቅትም ድንበር የሚጠብቀው የሱዳን ጦር የግድያ ሙከራ አድርገው ያመለጡትን ግለሰቦች ለመያዝ አልያም ወደ ሱዳን እንዳይገቡ ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ፣ የኢትዮጵያ የፀጥታ አካላትን ጥረት እንዳስተጓጎለ ተናግረው ነበር።

ድንበር ላይ የነበረው የሱዳን ጦር ያመለጡትን ገዳዮች ለመያዝ ተልዕኮ ላይ የነበረውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኃይል ከድንበር እንዳያልፍ እንደከለከለ ያስታወሱት አቶ መለስበዚህም ምክንያት የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ላይ የነበረውን የሱዳን ሠራዊት አጥቅቶ እንዲያልፍ መታዘዙን ገልጸው ነበር።

በታዘዘው መሠረት ዕርምጃ መውሰድ የጀመረውን የኢትዮጵያ የጦር ኃይል መቋቋም ያልቻለው የሱዳን ሠራዊት እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደኋላ እንደሸሸና ጉልበት ሰብስቦም ዳግም ለመዋጋት እንዳልመጣ የተናገሩት አቶ መለስ፣ የኢትዮጵያ ጦርም በወቅቱ ከሚታወቀው የሁለቱ አገሮች ድንበር ሰፊ ርቀት ሱዳን ውስጥ ዘልቆ በተቆጣጠረው መሬት ላይ እንዲቆይ መደረጉን አስታውሰዋል።

ይህ ውሳኔ የሱዳን ጦር ተደራጅቶ ለማጥቃት ይመለሳል በሚል እሳቤ የተወሰነ ቢሆንም፣ የሱዳን ጦር ግን በዚያው የውኃ ሽታ ሆኖ መቅረቱን፣ የኢትዮጵያ ጦርም ካምፑን በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች መመሥረቱን ገልጸዋል።

ይህ ሁኔታ ሳይቀየር ዓመታት በማለፋቸው በኢትዮጵያ ጦር ቁጥጥር ሥር የወደቁትን ይዞታዎች አጎራባች የኢትዮጵያ ግዛት አስተዳዳሪዎች ይዞታውን የእነርሱ የአስተዳደር ወሰን አካል አድርገው በመቁጠር፣ የግብርና መሬቶችን ለአርሶ አደሮችና ሰፋፊ እርሻዎችንም ለኢንቨስተሮች እንደሰጡ በወቅቱ አቶ መለስ አስረድተው ነበር።

ሱዳኖቹ እየጠየቁ የነበሩት ይህ ሁኔታ ተስተካክሎ ቀድሞ የነበረው ሁኔታ እንዲመለስ መሆኑን ያመለከቱት አቶ መለስ፣ በኢትዮጵያ በኩልም ይህንን ከግንዛቤ በማስገባት የማስተካከያራዎች መተግበር መጀመራቸውን ለአብነትም ሰፋፊ እርሻ የወሰዱ የውጭ ኢንቨስተሮች እንዲለቁ መደረጉን ገልጸው ነበር።

የኢትዮጵያ አርሶ አደሮች ለጊዜው እያረሱ እንዲቀጥሉና አጠቃላይ የሁለቱ አገሮች የድንበር ማካለል በፍጥነት ተከናውኖ፣ በዚህ አካባቢ ያለው ጉዳይም መፍትሔ እንዲያገኝ በኢትዮጵያ በኩል ሐሳብ ቀርቦ ተቀባይነት ማግኘቱን አስረድተው ነበር።

በወቅቱ የተፈጠረው የድንበር ውጥረት በተገለጸው መንገድ በስምምነት ከተቋጨ በኋላ በአካባቢው አልፎ አልፎ የአርሶ አደሮችና የሚሊሻ ግጭቶች ሲከሰቱ ቢቆይም፣ በመንግሥታት ደረጃ የተደገፈ ይህ ነው የሚባል የገዘፈ ችግር ሳይከሰት በርካታ ዓመታት ተቆጥረዋል።

ከጥቅምት ወር 2013 ዓ.ም. መጨረሻ ወዲህ በሁለቱገሮች መካከል ዳግም ያገረሸው የድንበር ውጥረት በዚሁ አልሻፋቅ በሚባለው ለም መሬት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን፣ የድንበር መካረሩ ደረጃም ከዚህ ቀደም ከነበሩት ክስተቶች የገዘፈ ይመስላል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ከሳምንት በፊት በሰጠው መግለጫ የሱዳን መንግሥትን ተጠያቂ ከማድረጉ በዘለለ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና አጠቃላይ የመከላከያ ሠራዊቱ በትግራይ ክልል የሕግ ማስከበር ዘመቻ በጀመሩ በማግሥቱ የሱዳን ጦር አወዛጋቢዎቹን የድንበር አካባቢዎች በኃይል መቆጣጠሩን እንደ ክህደት ቆጥሮታል።

የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌተና ጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ባደረጉት ንግግር ደግሞየሱዳን ጦር አወዛጋቢዎቹን የድንበር አካባቢዎች የተቆጣጠረው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በተደረገ ስምምነት ነው ብለዋል፡፡

ይህ ንግግራቸው ቀደም ብሎ በሱዳን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ሲሰጡ ከነበሩ መግለጫዎች የሚጣረስ ሆኗል።

ሌተና ጄኔራል አል ቡርሃን ራሳቸው የሱዳን ጦር አወዛጋቢዎቹን አካባቢዎች በኃይል ከተቆጣጠረ በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ የሱዳን ጦር የአገሪቱን ሉዓላዊ የግዛት አንድነት እንደሚያስከበርና ‹‹አንድ ስንዝር የሱዳን መሬት አልፎ አይሄድምአይነካም፤›› ማለታቸውን፣ የአገሪቱ የዜና አውታር ሱና ዘግቦ ነበር።

ባለፈው ቅዳሜ በሰጡት አስተያየት ደግሞ የሱዳን ጦር የተጠቀሱትን የድንበር አካባቢዎች የተቆጣጠረው ኃይል ተጠቅሞ ሳይሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) ጋር በተደረገ ስምምነት እንደሆነ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ያካሄደውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) ጋር በሁለቱ አገሮች ግንኙነቶች ዙሪያ መምከራቸውን የገለጹት ሌተና ጄኔራል ቡርሃን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የሱዳን ጦር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እንዲሰማራ እንደሚፈልጉ እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትግራይ ክልል በሚጀመረው የሕግ ማስከበር ዘመቻን በመሸሽ ወደ ሱዳን ድንበር ሊያመልጡ የሚችሉ በሕግ የሚፈለጉ ግለሰቦችን ለመግታት እንዲቻል በማሰብ፣ የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ እንዲሰማራ በጠየቁት መሠረት የሱዳን ሠራዊት በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኙ የሱዳን ይዞታዎች ላይ መሰማራቱን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ መንግሥትና በሱዳን የእንግሊዝ የቅኝ ገዥ አስተዳደር መካከል የኢትዮሱዳን ድንበርን በሚመለከት የድንበር ስምምነት ... 1902 መፈረሙን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰሞኑን የሰጠው መግለጫ ያሰገነዝባል። ይህ ስምምነትም የሁለቱ አገሮችን የጋራ ድንበር ለማካለልና ለዚህም ይረዳ ዘንድ የጋራ የድንበር ኮሚሽን ማቋቋምን የሚመለከት እንደነበር ይጠቅሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሱዳንን የሚወክለው የሱዳን ቅኝ ገዥ የነበረችው እንግሊዝ ተወካይ (ሜጀር ግዌን) ምንም ዓይነት የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ ባልተገኘበት ወይም የኢትዮጵያ መንግሥት ፈቃድ ባልሰጠበት ሁኔታ፣ በተናጠል የድንበር ማካለልራውን ... 1903 ማካሄዱን ይገልጻል፡፡ በዚህ ምክንያት በተለይም በዳግላይሽ ተራራ በስተሰሜን ያለው የግዌን ድንበር ማካለል አከራካሪ ሆኖ እስካሁን ድረስ መቆየቱን ይገልጻል።

በሁለቱ አገሮች መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት የኢትዮጵያና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ... 1972 በተለዋወጡት ማስታወሻ ከዳግላይሽ ተራራ በስተደቡብ ያለውን ድንበር ለማካለል መስማማታቸውን የሚገልጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ፣ ድንበሩን ለማካለል በርካታደቶች ቢከናወኑም የማካለልራው እስካሁን እንዳልተከናወነ አስገንዝቧል።

የሱዳን መንግሥት በበኩሉ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል የሚያወዛግብ የድንበር ወሰን እንደሌለ፣ ሁለቱ አገሮች የጋራ ድንበራቸውን 1902 በፈጸሙት ስምምነት መካለሉን፣ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ስምምነቱ መሬት ላይ ወርዶ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ አለመደረጉን ይገልጻል።

በቅርቡ የሆነውም በሁለቱ አገሮች ስምምነት መሠረት ሱዳን በተከለለው ድንበሯ ላይ ጦር ሠራዊቷን የማስፈር ተግባር ብቻ እንደፈጸመች ያስረዳል፡፡ ሁለቱ አገሮች በተለያዩ ጊዜያት የሚሰጧቸው መረጃዎች እርስ በርስ የሚጣረሱ በመሆናቸው ብዥታ የተፈጠረ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት በድንበር አካባቢ የጦር ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ይገኛሉ።

ይህ ሁኔታ ወደ ለየለት ግጭት ከማምራቱ አስቀድሞ ልዩነቶችን በውይይትና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት በኢትዮጵያ በኩል ሰፊ ጥረት እየተደረገ ሲሆንጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔ ፍለጋ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ልዩ መልዕክተኛቸው አድርገው ባለፈው ሳምንት ወደ ደቡብ ሱዳን ልከዋል።

በዚህም መሠረት የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኢትዮጵያና በሱዳን መንግሥታት መካከል እየተካረረ ያለው የድንበር ጠብ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በውይይት እንዲፈታ ደቡብ ሱዳን እንድታሸማግል፣ ለሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላምዶክ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል። እዚህ ላይ አስገራሚ ነጥብ የሚሆነው የኢትዮጵያና የሱዳን የድንበር ውዝግብ በውይይት እንዲፈታ አስታራቂ ሆና የቀረበችው ደቡብ ሱዳን ራሷ፣ ከሱዳን ጋር የምትወዛገብበት ያልተካለለ ሰፊ የድንበር ጥያቄ ያላት መሆኑ ነው።

ከዚህ በተጨማሪም የሱዳን መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ የተነሳውን የድንበር ውዝግብ በተመለከተ ሚስጥራዊ ውይይት ከግብፅ መንግሥት ጋር እያደረገ ቢሆንም፣ ሱዳን ራሷ ከግብፅ መንግሥት ጋር ያልፈታቸው የሃለያብ ድንበር ውዝግብ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በእንጥልጥል የሚገኝ መሆኑ ሌላው እንቆቅልሽ ነው።

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -