Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለተሰንበት ግደይ ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቀለች

ለተሰንበት ግደይ ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቀለች

ቀን:

ወርልድ አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ውድድሮች እንዲመለሱ ውሳኔ አሳለፈ

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ዝግጅት ያልጀመሩ የትግራይ ክልል አትሌቶች ብሔራዊ ቡድኑን መቀላቀላቸውን አስታወቀ፡፡ በመስከረም ወር በስፔን ቫሌንሲያ በተደረገው የ5,000 ሜትር ውድድር አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበችው ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ ሌሎች የትግራይ አትሌቶች በማዕከላዊ መንግሥትና በክልሉ መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ግንኙነት በመቋረጡ ከብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅት ውጪ ሆነው ቆይተው ነበር፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ፣ በኦሊምፒክና በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዋ ጥሩነሽ ዲባባ ከ12 ዓመት በላይ ተይዞ የነበረውን የአምስት ሺሕ ሜትር የዓለም ክብረወሰን የሰበረችው ለተሰንበት ግደይ፣ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ተቀላቅላ ዝግጅት ለመጀመር የኮቪድ የምርመራ ውጤት እየጠበቀች ነው፡፡ ሐጎስ ገብረ ሕይወትን ጨምሮ ለብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች አትሌቶች ለዝግጅት ሆቴል ከገቡ ከሳምንት በላይ ሆኗቸዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ትግራይ ካፈራቻቸው ምርጥ አትሌቶች መካከል 22 ዓመቷ ለተሰንበት ትጠቀሳለች፡፡ አትሌቷ ወርልድ አትሌቲክስ በቅርቡ በትዊተር ገጹ ባደረገው ምርጫ የዓመቱ ምርጥ አትሌት አድርጎ መርጧታል፡፡

​​ለተሰንበት ግደይ ብሔራዊ ቡድኑን ተቀላቀለች

ሩጫን በትምህርት ቤት የስፖርት ክፍለ ጊዜ እንደጀመረች የሚነገርላት የሰሜኗ ኮከብ ለተሰንበት ግደይ፣ የዓለም ምርጥ አትሌትነትን ክብር ማግኘት የቻለችው፣ ወርልድ አትሌቲክስ መስከረም ወር በስፔን ቫሌንሲያ ባካሄደው 5,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ርቀቱን 1406.65 በመግባት አዲስ የዓለም ክብረወሰን ማስመዝገቧን ተከትሎ ነው፡፡

በረዥም ርቀት በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአይበገሬነቷ በምትታወቀው ጥሩነሽ ዲባባ 2008 ኦስሎ ላይ ተመዝግቦና ተይዞ የቆየው 1411.05 የርቀቱ ክብረ ወሰን ነበር፡፡ 12 ዓመት በኋላ ከአራት ደቂቃ በላይ በማሻሻል ክብረ ወሰኑን በእጇ ያስገባቸው ለተሰንበት ግደይ፣ ይህን ክብርና ድል ለማስመዝገብ የቻለችው፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ዓለም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥጋት ውስጥ በነበረበት ወቅት መሆኑ አይዘነጋም፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወትሮው በተለየ ከስምንት ወር በፊት ዝግጅት የጀመረ ሲሆን፣ በአሠልጣኞች ዕቅድ መሠረት የመጀመሪያው ዙር ሥልጠና ካጠናቀቀ በኋላ ጥር 8 እና 9 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲየም የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ከ800 እስከ 10,000 ሜትር በየውድድር ዓይነቱ አምስት አምስት አትሌቶችን ማስመረጡ ይታወሳል፡፡ ይሁንና የትግራይ ክልል አትሌቶች በዚህ የዝግጅት መርሐ ግበር አልተካተቱም ነበር፡፡

በሌላ በኩል ወርልድ አትሌቲክስ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የጎዳና ላይ ውድድር ከኮቪድ በፊት በነበረው ይዘት እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ዓለም አቀፉ ተቋም እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ከዚህ ቀደም በወርቅ፣ በብርና በነሐስ ደረጃ በመለየት በተለያዩ ወቅቶችና በተለያዩ ከተሞች ሲካሄዱ የነበሩ የጎዳና ላይ ውድድሮች ከዚህ ወር ጀምሮ በሚወጣላቸው ፕሮግራም መሠረት ይከናወናሉ፡፡

የመጀመሪያው የጎዳና ላይ ውድድር የሚካሔደው በመጪው ክረምት የ2020 ኦሊምፒክን በምታስተናግደው ጃፓን ሲሆን፣ ውድድሩም የኦሳካ ማራቶን ይሆናል፡፡ ከኦሳካ በኋላ በተለይም በውድድር ዓመቱ እንዲካሔዱ ፕሮግራም የተያዘላቸው የማድሪድና የሳኦ ፖሎ ማራቶኖች ስለመሆናቸውም ወርልድ አትሌቲክስ በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል፡፡

ዓለም አቀፉ ተቋም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘው አትሌቲክስ የገቢ ምንጩን ጨምሮ እንደገና ወደ ነበረበት ለመመለስ የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጭምር አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...