Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየመሬት ወረራን ጨምሮ በኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ላይ ሕገወጥ ተግባር የፈጸሙ በሕግ ሊጠየቁ...

የመሬት ወረራን ጨምሮ በኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ላይ ሕገወጥ ተግባር የፈጸሙ በሕግ ሊጠየቁ ነው

ቀን:

  • ከ1,300 ሔክታር በላይ መሬት ተወሯል
  • 322 ባለቤት አልባ ሕንፃዎች ተገኝተዋል
  • ያለ ዕጣ የተላለፉ 51,064 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ተገኝተዋል
  • 10,565 የቀበሌ ቤቶች በሕገወጥ መንገድ ተይዘዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ከ1,300 ሔክታር በላይ የመሬት ሲወረር፣ ከ50 ሺሕ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ያለዕጣ ሲሰጡና ከ10,000 በላይ የቀበሌ ቤቶች በሕገወጥ መንገድ ሲያዙ፣ በሕገወጥ ተግባሩ የተሳተፉና የተጣለባቸውን ኃላፊነት ሳይወጡ በቀሩ በየደረጃው የሉ አመራሮችን፣ በሕግ ለመጠየቅ ጉዳዩ ለፌዴራል ፖሊስና ለጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ መላኩ ተገለጸ፡፡

አስተዳደሩ ከተባባሪ ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ጥናት፣ ሕገወጥ የመሬት ወረራ፣ ቤት አልባ ሕንፃዎች፣ በሕገወጥ መንገድ የተላለፉ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በሕገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ ቤቶች መገኘታቸውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ በዝርዝር እንዳስረዱት በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ 121 ወረዳዎች ውስጥ 88 ላይ 1,338 ሔክታር መሬት ወረራ ተካሂዷል፡፡  

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የመሬት ወረራው ከ1997 ዓ.ም. ጀምሮ የቆየ ታሪክ ያለውና በየጊዜው እየተደራረበ የመጣ ሕገወጥ ድርጊት እንደሆነ ምክትል ከንቲባዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በ2010 ዓ.ም. አገራዊ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት ሰፋ ባለ መልኩ የመሬት ወረራው የነበረና ከለውጡ በኋላም አጠቃላይ አመራሩ ሕገወጥነትን በተገቢው ባለመከላከሉ ችግሩ እንዲደራረብ እንዳደረገው ተናግረዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ባለቤት አልባ ቤቶችና ሕንፃዎችን በተመለከተ ሲናገሩ፣ በድምሩ 322 ሕንጻዎች እንደተገኙ የገለጹ ሲሆን፣ የቦታ ስፋታቸው ደግሞ 229,556 ካሬ ነው፡፡

ከተገኙት ባለቤት አልባ ሕንፃዎች መካከል ግንባታቸው የተጠናቀቁት 58 ሲሆኑ 125,409 ካሬ ቦታ የተገነቡና ተከራይተው ያሉ፣ ነገር ግን ባለቤት ነኝ የሚል አካል መረጃውን እንዲያቀርብ ቢጠየቅም የሚቀርብ ባመኖሩ ባለቤት አልባ እንደተባሉ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ግንባታቸው ያልተጠናቀቁና ባለቤት አልባ ሕንፃዎች ብዛት 264 ሲሆን ስፋታቸው ደግሞ 104,147 ካሬ ላይ ያረፉ ቤቶችናንፃዎች ናቸው፡፡

የሕገወጥ የመሬት ወረራው በግለሰብ ደረጃና በሃይማኖት ተቋማት፣ በቡድን በመሄድና መንደር በመመሥረት በሕገወጥ መልኩ ይዞታን በማስፋፋት የመንግሥትን መሬት በመውረር በግለሰቦችና በሪል ስቴት አልሚዎች የተፈጸመ እንደሆነ ወ/ሮ አዳነች ተናረዋል፡፡

በዚህም በአጠቃላይ የመሬት ማኔጅመንት አመራሮችን በመጣስ፣ በባለሀብቱና የመንግሥት አመራሩ መካከል በነበረ የጥቅም ትስስርናገወጥ ደላሎች ከመንግሥት አመራሮች ጋር ትስስር በመፍጠር እንደተፈጸመ ተገልጿል፡፡

የኮንደሚኒየም ቤቶችን ሁኔታ በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ላለፉት ሁለት ወራት ጥናት ሲደረግ እንደቆየ የገለጹት ወ/ሮ አዳነች ጥናቱን ተከትሎ በአራት መንገዶች መረጃዎቹን የማጥራትራው ተሠርቷል ብለዋል፡፡

በዚህም ቤቶች ኮርፖሬሽን ላይ ያለን መረጃ፣ በዕጣ የተላለፉ ቤቶች ዝርዝር፣ ከባንክ ጋር ውለታ የተፈጸመበት መረጃና በመስክ የተገኘን መረጃ ማዕከል በማድረግ ዝርዝር መረጃውን የመተንተን መሠራቱን ተነግሯል፡፡

በዚህም በሕገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶች 21,695 ሲሆኑ 15,891 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መረጃ ያልቀረበባቸው፣ 4,530 ለረዥም ጊዜ ዝግ የሆኑ፣ 850 ከመጀመሪያውም ዝግ የሆኑ የተቀመጡ ቤቶች አንደተገኙ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም 424 በሕገወጥ መልኩ በግለሰቦች ተይዘው የሚገኙበዕጣ ሳይሆን ያለአግባብ ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51,064 ቤቶች እንደተገኙ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በቤቶች ኮርፖሬሽን ተመዝግቦ የሚገኘው 132,678 የባለዕጣዎች ዝርዝር ውስጥ 18,423 ቤቶች የቤት ባለቤት ስም የሌላቸው መሆኑን በጥናቱ እንደተለየ ተገልጿል፡፡

በእነዚህ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦች መረጃቸውን እንዲያቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም መረጃ ማቅረብ ያልቻሉ ወይም ያልፈለጉ በመሆናቸው ቤቶቹ በሕገወጥ መንገድ እንደተያዙ ተመዝግቧል ተብሏል፡፡

መገንባት የነበረባቸው ነገር ግን ያልተገነቡ 28 የጋራ መኖሪያ ብሎኮችንና 83 የጋራ መጠቀሚያንፃዎች/ኮሚናል ሳይገነቡ እንደቀሩና ለምን እንደልተገነቡ መረጃም አለመገኘቱን ወ/ሮ አዳነች አክለው ገልጸዋል፡፡

የቀበሌ ቤቶችን በተመለከተ በከተማ አስተዳደሩ ሥር የሚተዳደሩ 150,737 የቀበሌ መኖሪያና ንግድ ቤቶች አሉ፡፡ በዚህ ጥናት ተደራሽ መሆን የቻሉት 138,652 የመኖሪያና የንግድ ቤቶች ናቸው፡፡

ጥናቱ እንደሚያሳው 10,565 የቀበሌ ቤቶች በቁልፍ ግዥ፣ ሰብሮ በመግባትና በሌሎች ከሚፈቅደው ውጪ በሕገወጥ መንገድ ተይዘዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ 7,723 ቤቶች ውል በሌላቸው ሰዎች፣ 2,207 ቤቶች ወደ ግል የዞሩ 265 ቤቶች በሦስተኛ ወገን የተያዙ 164 ቤቶች ኮንደምንየም ደርሷቸው ወይም የራሳቸው ቤት እያለቸው ከሕጉ ወጪ የቀበሌ  ቤቶችን የያዙ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል 137 በሽያጭ ወደ ግል የተላለፉ 1,243 ታሽገው ተዘግተው የተቀመጡ 5043 የፈረሱ 180 አድራሻቸው የማይታወቁ ወይም የጠፉ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች መገኘታቸውን ምክትል ከንቲባዋ አክለው ገልጸዋል፡፡

በከተማዋ 25,096 የንግድ ቤቶች እንደሚገኙ የገለጹት ወ/ሮ አዳነች ከእነዚህ ውስጥ 4,076 በሕገወጥ ተይዘው እንደሚገኙና 1,070 ቤቶች ውል የሌላቸው ነጋዴዎች እንደያዟቸዉ ተገልጿል፡፡

2,451 ቤቶች ከአንድ በላይ የንግድ ቤት በያዙ 1,086 ነጋዴዎች 376 ቤቶች ደግሞ በተከራይ አከራይ በሦስተኛ ወገን እንደተያዙና 179 የታሸጉ የንግድ ቤቶች መገኘታቸውን ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡

ምትል ከንቲባዋ በሕገወጥ የተወረረውን መሬት ወደ መሬት ባንክ፣ ባለቤት አልባ ሆነው የተገኙትን ቤቶች ደግሞ በዕጣ እንደሚተላለፉም አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...