Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ›› ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች ሊካሄድ ነው

  የ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ›› ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች ሊካሄድ ነው

  ቀን:

  የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት በኢትዮጵያ ‹‹እንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ›› ንቅናቄ በትምህርት ቤቶች እንደሚካሄድ የትምህርትና የጤና ሚኒስቴሮች አስታወቁ፡፡

  የእንድናገለግልዎ ማስክዎን ያድርጉ ንቅናቄ እንደሚካሄድ የገለጹት የትምህርት ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (/ር) እና የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (/ር) ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም.  በጋራ በሰጡት መግለጫ፣ ንቅናቄው የሚካሄደው ማክሰኞ ጥር 25 ቀን ነው፡፡

  በሁሉም የትምህርት ተቋሞች የሚገኙ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ሁሉም ማስክ በማድረግ በትምህርት ተቋሞቻቸው አካባቢ በመዘዋወር ኅብረተሰቡን ማስክ በማድረግ እንዳለበት ከፍተኛ ቅስቀሳ እንደሚያደርጉና እንደሚያስተምሩ ገልጸዋል፡፡

  ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደተገለጸው፣ በኢትዮጵያ የበሽታው ሥርጭት እየቀነሰ ባይመጣም ተማሪዎች ለረጅም ወራት ከትምህርት ገበታቸው ርቀው መቆየታቸውን ታሳቢ በማድረግ የኮቪድ-19 መከላከያ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ መማር ማስተማሩን  መቀጠል እንደሚቻል ታምኖበታል፡፡

   ተቀምጠው የነበሩ በርካታ መመሪያዎችና አሰራሮች ወደ መደበኛ ተግባሮቻቸው እንዲመለሱ የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው መሠረት፣ ከዘንድሮ ጀምሮ የመንግሥትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የገጽ ለገጽ መማር ማስተማር ሥራቸውን እንዲጀምሩ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ እንዲተገበሩ መመሪያ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡

  በተለይም የእጅ መታጠቢያዎችን አገልግሎት የማይሰጡትን በመጠገን እንዲሁም ቁጥራቸውን በመጨመር በሁሉም ትምህርት ቤቶች አገልግሎት እንዲሰጡ ማስቻል፤ የአፍንጫና ፊት መሸፈኛዎችን ሥርጭት ማሳደግ፣ ትምህርት ቤቶች ሙቀት ልየታ እንዲሠሩ የሙቀት መለኪያ መሣሪያውን እንዲያሟሉ ማድረግ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የተማሪዎችን መጨናነቅ ለማስቀረትም ተማሪዎችን በክፍል ውስጥ በግማሽ በመቀነስ እንዲሁም ቅዳሜን ጨምሮ በፈረቃዎች እንዲማሩ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።

  ‹‹ከኮሮና ተጠበቁ አትዘናጉ››

  የኮቪድ-19 ታማሚዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ ማድረግ የሚገቡ ጥንቃቄዎችን መተግበር እንደሚገባ በየጊዜው የጤና ሚኒስቴርም ሆነ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥብቅ ማሳሰቢያ መስጠታቸውን ለአፍታም ቸል አላሉም፡፡

  ኢትዮ ቴሌኮም የሁለቱ ዓበይት ተቋማት ዱካን በመከተል የቴሌፎን የድምፅ ጥሪን ‹‹ከኮሮና ተጠበቁ አትዘናጉ›› የሚል አንድምታ ያለውን የደወል ድምፅ እንዲህ አስተጋብቷል፡፡

  ‹‹ጤና ይስጥልኝ፡፡ የኮቪድ ፅኑ ሕሙማን ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ መዘናጋት ብዙዎችን አሳጥቶናል፡፡ ጥንቃቄ ብዙዎችን ዛሬን ያሻግራል፡፡ እባክዎትን ማስክዎን ያደርጉ፣ ሕይወትዎን ያትርፉ!››

  ይህም ሲፍታታ ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መስተጋብር ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተፅዕኖ ሳያንስ፣ እርስዎ በመዘናጋትም ሕይወትዎን እንዳያጡ አሊያም እንዳይታመሙና እንዳይሠቃዩ ልብ በሉ የሚል ሴማ አለው፡፡

  የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አሁናዊ መረጃ እንደሚያሳየው፣ እስከ ጥር 18 ቀን 2013 .. ድረስ 1,930,478 ሰዎች በተደረገው የላቦራቶሪ ምርመራ 134,569 ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ 120,748 ሰዎች አገግመዋል፡፡ 2,075 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ 11,744 ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው ታውቋል፡፡  

  ጥብቁ መመርያ

  መሰንበቻውን የጤና ሚኒስቴር ባወጣው ጥብቅ መመርያ መሠረት ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግሥታዊና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግና ተገልጋዮችም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውንና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት በተቋሙ ላይ ተጥሏል፡፡

   የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ አሽከርካሪ፣ አገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርትን በተመለከተ በሕግ ከተወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት መስጠት እንደሌለበት መግለጫው አመልክቶ፣ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሠሪዎች በተመለከተ በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውኃ፣ ሳሙና፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሣሪያ እንዲሁም የፀረ ተህዋሲያን ግብዓት የማሟላት ግዴታ እንዳለባቸው አስታውቋል፡፡

  በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የዘርፉ መሥርያ ቤቶች በየመስካቸው የሚያወጧቸው መመርያዎችና አሠራሮች የኮቪድ-19 በሽታን ለመግታት ወይም ለመቀነስ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባወጣው መመርያ ውስጥ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች የማይቃረኑና ተጣጥመው የወጡ መሆን እንዳለባቸው፣ በዚሁ መመርያ የተደነገጉ ክልከላዎችንና ግዴታዎችን የተላለፈ ማንኛውም ሰው አግባብነት ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ተጠያቂ እንደሚሆን፣ ማንኛውም ሰው 25/01/2013 ጀምሮ መመርያው የፀና መሆኑን አውቆ ተግባራዊና ተፈጻሚ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ ማሳሰቡ ይታወሳል፡፡    

  የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መጨመርን ከግንዛቤ በማስገባት ኅብረተሰቡ ጥንቃቄዎችን አዘውትሮ እንዲተገብር ያሳሰበው የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ዕለት ዕለት በሚደረገው እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በበሽታው መያዝን የሚወሰን መሆኑን በማስታወስ፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ አራቱን ‹‹›› ሕጎች በመተግበር የበሽታውን ሥርጭት ሁሉም እንዲከላከልም በጥብቅ አሳስበዋል፡፡

  አራቱ ‹‹›› ሕጎች

  • መራራቅ አካላዊ ርቀት መጠበቅ፣
  • መታጠብ እጅን በተደጋጋሚ በውኃና በሳሙና መታጠብ፣
  • መቆየት አስገዳጅ ካልሆነ ቤት ውስጥ መቆየት፣
  • መሸፈን ከቤታችን ወጥተን ስንንቀሳቀስ የአፍንና የአፍንጫ መሸፈኛ (የፊት ማስክ) መጠቀም፡፡
  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...