Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊበትግራይና በመተከል ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

  በትግራይና በመተከል ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ ተጀመረ

  ቀን:

  በትግራይ ክልል ከድኅረ ሕግ ማስከበር ዘመቻ በኋላ፣ እንዲሁም ከመተከል ዞን ተፈናቅለው ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን ለመርዳት፣ የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ በሥሩ ባሉት ማኅበራት አማካይነት፣ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ የሚጠናቀቅ 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የማሰባሰብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

  የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አያልሰው ወርቅነህ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በትግራይና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል አካባቢዎች የተፈጠረውን ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውሶችን ለመከላከል፣ ለመቀነስና ለመቋቋም የኅብረት ሥራ ማኅበራት መረባረብ እንዳለባቸው ማክሰኞ ጥር 25 ቀን 2013 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በተደረገ ድንገተኛ ስብሰባ በሁሉም የክልል የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኃላፊዎች ከስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል፡፡

  የሚደረጉት ድጋፎች የዓይነትና የገንዘብ እንደሆኑ ወ/ሮ አያልሰው ገልጸው፣ ይህም የሚከናወነው በገንዘብ ቁጠባ የኅብረት ሥራ ማኅበራትና ምርት ባላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

  ሁሉም የኅብረት ሥራ ማኅበራት እንደየአቅማቸው ድጋፉን ለማድረግ ተስማምተዋል ያሉት ኃላፊዋ፣ ‹‹በዚህም ማኅበራቱ በጠቅላላ ጉባዔያቸው በኩል እያስወሰኑ የመጀመሪያ ዙር ድጋፉን እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. ድረስ ሰብስቦ በማጠናቀቅ ለተረጂዎቹ ለማድረስ እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፤›› ብለዋል፡፡

  በአንድ ወር ውስጥ በሚሰባሰበው ድጋፍ ከኅብረት ሥራ ማኅበራት ለተጎጂው ኅብረተሰብ ተደራሽ የሚሆን 50 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ፣ 30,452 ሜትሪክ ቶን የግብርና ምርት በኅብረት ሥራ ማኅበራት አማካይነት እንዲቀርብ፣ ጠንካራ የግብይት ትስስር መፍጠርና አንድ ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የተለያዩ የኢንዱስትሪ ውጤቶችና መሠረታዊ የፍጆታ ሸቀጦች በማኅበራቱ አማካይነት ለተጎጂ ወገኖች ግብይት ለማቅረብ ከወዲሁ በዝርዝር ተቀምጦ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

  በትግራይና በመተከል አካባቢዎች ያለው ሕዝብ አቅርቦቱን በማጣትና ለመሸመት የተቸገረ እንደ መሆኑ መጠን ከሚደረገው ዕርዳታ ባሻገር ለነዋሪዎቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርትን ማቅረብ፣ ከዚሁ ጎን ለጎን በቋሚነት የሚከናወን ተግባር መሆኑን የሚገልጹት ወ/ሮ አያልሰው፣ በተለይም የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶችን የግብይት ትስስር መሠረት በማድረግ የአቅርቦቱ ሥራ እንዲቀጥል ይደረጋል ብለዋል፡፡ በዋናነት በትግራይ ክልል የሚገኙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት በነበረው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ለጉዳት ተዳርገው ስለነበር፣ እነሱን በማቴሪያልና በሰው ኃይል የማጠናከር ሥራ የመጀመሪያ ተግባር ሆኖ ክልሉ ላይ በተቋቋሙ ኮሚቴዎች አማካይነት እየተሠራበት እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

  የሁሉም ክልሎች የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ በተካሄደው ውይይት ላይ የተገኙ ሲሆን፣ በከፍተኛ መነሳሳት ድጋፍ የማድረጉን ሐሳብ በደስታ ተቀብለውታል ብለዋል፡፡ በውይይቱም በቅርቡ የትግራይ ክልል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ማዕረግ ግርማይ መገኘታቸውን፣ ዜጎችን ለመታደግ የዘርፉ ኃላፊዎች ያሳዩትን አዎንታዊና ያልተገደበ ድጋፍ አመሥግነው፣ በክልሉ ያለውን ሁኔታ በተጨባጭ እንዳስረዱ የገለጹት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ፣ ይህንንም የተረዱት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኃላፊዎች የታቀደውን ድጋፍ በፍጥነት በማስተባበር በትግራይና በመተከል አካባቢዎች ባሉ የኅብረት ሥራ ማኅበራትም ሆነ ድጋፍ ለማሰባሰብ በተቋቋመ ግብረ ኃይል በኩል ድጋፉ እንዲዳረስ ለማድረግ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ብለዋል ፡፡

  የፌዴራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዘርፉን በሚፈለገው ደረጃ ወደፊት ለማሻገር የተለያዩ የአሠራር፣ የአደረጃጀትና የሰውይል ማሻሻያ ሪፎርም በመንደፍ በተግባር ለማዋል በየደረጃው የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝና ይህን የሚያግዙ ጥናቶችና ውይይቶች እየተደረጉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ 

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...