Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለሠራተኞች ሥጋት የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመዋቅር ጥናት

ለሠራተኞች ሥጋት የሆነው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመዋቅር ጥናት

ቀን:

ፌዴሬሽኑ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ መጻፉም ተሰምቷል

የአትሌቲክስ ውድድሮች በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ እየተሰረዙና እየተራዘሙ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ አዲስ አደረጃጀት ለመዘርጋት ያለመ የሚመስለው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመዋቅር ጥናት እያስጠና ይገኛል፡፡ የዚህ ጥናት ቡድን ሰብሳቢ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ቢልልኝ መቆያ ናቸው፡፡ የአደረጃጀት ጥናቱ በገለልተኛ ባለሙያ ቡድን ወይም ድርጅት እየተሠራ አለመሆኑ ደግሞ በሠራተኞች ላይ ጥርጣሬና ሥጋት መፍጠሩ እንዳልቀረ የሚናገሩ አሉ፡፡

በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ሰብሳቢነት የሚመራው ይህ የጥናት ቡድን፣ በኢትዮጵያ ሆቴል በመሆን የአደረጃጀት ጥናቱን ከጀመረ ከሳምንት በላይ እንደሆነው ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የፌዴሬሽኑ ሠራተኞች ይናገራሉ፡፡ እንደ ሠራተኞቹ፣ ‹‹ብሔራዊ ተቋሙ የመዋቅር ጥናት ማድረጉ ተገቢና ትክክለኛ ውሳኔ ቢሆንም በየትኛውም መመዘኛ ተቋሙን በኃላፊነት የሚመራ ኃላፊ የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ ከሆነ ግን የጥናቱን ገለልተኝነትና ተዓማኒነት የተሟላ አያደርገውም፤›› በማለት የአሠራር ሒደቱ ሠራተኞች ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይሠሩ አድርጓል ሲሉ ይወቅሳሉ፡፡

ሠራተኞቹ የጥናት ቡድኑን ስብስብ በተመለከተ ሲናገሩ፣ ከፌደሬሽኑ ሰብሳቢውን ጨምሮ አያሌው ጥላሁን (ዶ/ር)፣ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝና የሠራተኞች ተወካይ በሚል አቶ ጎሳ ግርማ ሲካተቱ፣ ከደቡብ፣ ከኦሮሚያ፣ ከትግራይና ከአማራ ክልሎች አንዳንድ ተወካዮች በዚሁ የጥናት ቡድን ውስጥ ተካተው እንደሚገኙ ይናገራሉ፡፡

‹‹ሁሉም እንሚያውቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአገሪቱ ከሚገኙ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በውጤት የተሻለ ደረጃ ላይ የሚገኝ ነው፡፡ በራሱ አቅምና በጀት የሚንቀሳቀስ ትልቅ አገራዊ ተቋምም ነው፡፡ ዘመኑንና ጊዜውን የሚመጥን የመዋቅር ጥናት ያስፈልገዋል፣ ይሁንና ጥናቱ በዚህ ደረጃ ያስፈልጋል ከተባለ፣ የሙያ ደረጃውን በጠበቀ ገለልተኛ አካል መጠናት ይኖርበታል ብለን እናምናለን፤›› የሚሉት እነዚሁ ሠራተኞች፣ አሁን ባለው ሁኔታ ግን ጥናቱ የፌዴሬሽኑን ሙያተኞች በትክክለኛው ቦታና አቅም መዝኖና ገምግሞ ተዓማኒነት ያለው የመዋቅር ጥናት ለመሆኑ ይሠጋሉ፡፡ በዚህ ጉዳይ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑን ኃላፊዎች ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በሌላ በኩል ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅትና ከአትሌቶች ምርጫ ጋር ተያይዞ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ማስገባቱ ተሰምቷል፡፡ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ከስምንት ወራት በፊት ዝግጅት መጀመሩ የሚታወቅ ነው፡፡

በዚሁ መሠረት ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲየም ከ800 ሜትር እስከ 10 ሺሕ ሜትር የመጀመርያ ዙር ማጣሪያ አድርጎ፣ ለእያንዳንዱ የውድድር ዓይነቱ አምስት አምስት ባጠቃላይ ከ123 በላይ አትሌቶችን መርጦ፣ ሆቴል አስገብቶ እያዘጋጃቸው መሆኑ ይታወሳል፡፡

እንደ ሪፖርተር ምንጮች ከሆነ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽን ከሰሞኑ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ ለመጻፍ ያነሳሳው ዋናው ምክንያትም፣ አሠልጣኞችን ጨምሮ ከአትሌቶች ምርጫ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ አለመግባባት ነው፡፡ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለዚህ ዝግጅት የሚውለው ሙሉ ወጪ የሚሸፈነው በኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደመሆኑ መጠን፣ ፌዴሬሽኑ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ የሚይዛቸውን አትሌቶችና አሠልጣኞች መርጦ ተገቢውን ዝግጅት እንዲጀምር ሲጠይቅ፣ በፌዴሬሽኑ በኩል ደግሞ የወጪ ጥያቄ ሊቀርብ አይገባም የሚል መከራከሪያ እንደሚያነሳ ነው የሚነገረው፡፡

ከአሠራር ጋር ተያይዞ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ቅሬታ እንኳ ቢኖረው ቅሬታውን ማቅረብ የሚገባው የአካሄድ ቅደም ተከተሉን በጠበቀ መልኩ ለስፖርት ኮሚሽን አሊያም ለኮሚሽኑ ተጠሪ ለሆነው ለባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር መሆን ነበረበት የሚሉ አልጠፉም፡፡ ይሁንና ኮሚሽኑ ባለፈው ሰኞ የሁለቱን ተቋማት አመራሮች ጠርቶ ያነጋገራቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...