በየዓመቱ ጥር 23 ቀን የሚከበረው የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች በዓል ዘንድሮም ለ81ኛው ጊዜ በእንጅባራ ከተማ ተከብሯል፡፡ በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲዘልቅና መስህብ እንዲሆን የክልሉ መስተዳድር እንደሚደግፍ ቃል ገብቷል፡፡ በዓሉ የተከበረው በጉግስ፣ በሸርጥ፣ በግልቢያና በሌሎች ትርዒቶች ነው። በ1933 ዓ.ም. የተመሠረተው የአዊ ዞን የሰባት ቤት አገው የፈረሰኞች ማኅበር፣ በአሁኑ ወቅት ከ53 ሺሕ በላይ አባላት እንዳሉት ተገልጿል፡፡ ፎቶዎቹ የመሰናዶውን ከፊል ገጽታ ያምናውን ጨምሮ ያሳያሉ፡፡
ፎቶ፡ አብመድ