Friday, May 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየአምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ፋውንዴሽን ተመሠረተ

የአምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ፋውንዴሽን ተመሠረተ

ቀን:

የቀድሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) መታሰቢያ የተቋቋመው ፋውንዴሽን ይፋ ተደረገ፡፡

ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና በአረንጓዴ ልማት ላይ እንደሚሰማራ ታውቋል፡፡

ፋውንዴሽኑ ጥር 26 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ ሲደረግ የዶ/ር አምባቸውን ቤተሰብ በመወከል ልጃቸው ወ/ሪት መዓዛ አምባቸው እንደተናገሩት፣ አገር አቀፉ ፋውንዴሽን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚታዩ ማኅበረሰባዊ ችግሮችን በማቃለል፣ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ችግሮችን በውይይትና በመቀራረብ እንዲፈታ ያደርጋል፡፡ በሕዝቦች መካከልም ያለውን የእርስ በርስ ጥርጣሬ በማስወገድ የአስተሳሰብ ለውጥ እንዲመጣ እንደሚያደርግም አውስተዋል፡፡

- Advertisement -

በአምባቸው መኮንን ስም የተቋቋመው ተቋም እርሱ በሕይወት እያለ የጀመራቸውንና ዕድሉን አግኝቶ በሕይወት ቢኖር ሊሠራቸው የሚችሉ ሥራዎችን ለማስቀጠል አልሞ የሚንቀሳቀስ እንደሆነም ወ/ሪት መዓዛ ገልጸዋል፡፡

‹‹ዶ/ር አምባቸው መኮንን አልሞተም በሕይወት አለ ወደፊትም ይኖራል ብለን እንድናስብና እንድንፅናና የሚያደርገን ደግሞ ሁሌም ቢሆን እናንተ ወገኖቻችን ከጎናችን መሆናችሁን ስናስብ ነው፤›› ያሉት ልጃቸው፣ የፋውንዴሽኑ ዋና ዓላማ በሕይወት እያለ የጀመራቸውን እና ዕድሉን አግኝቶ በሕይወት ቢኖ ሊሠራቸው የሚችሉት ሥራዎችን ማስቀጠል ነው፤›› የሚችሉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ለፋውንዴሽኑ አገልግሎት የሚውል መሬት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ አካባቢ መስጠቱም ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፣ አምባቸው (ዶ/ር)፣ በሕይወት ዘመኑ ለጎጥና ከፋፋይ አስተሳሰብ ቦታ የማይሰጥ ለእውነተኛ ዴሞክራሲና ለሕዝብ የታገለ ቁልፍ መሪ ነበር።

ራዕዩን ለማሳካት የተቋቋመው ፋውንዴሽን ግቡን እንዲመታ አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ፋውንዴሽኑ በትምህርት፣ በጤና፣ በአረንጓዴ ልማት ከሚሠራቸው በተጨማሪ እውነትንና ሀቀኝነትን ይዞ የአገርን ልማት የሚያግዝ ማኅበረሰብ ለመፍጠር የታለመ መሆኑንም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ሃቻምና ከጓዶቻቸው ጋር በስብሰባ ላይ ሳሉ የተገደሉት አምባቸው (ዶ/ር)፣ በ1962 ዓ.ም. በጎንደር ክፍለ ሀገር ጋይንት አውራጃ አቄቶ ኪዳነ ምሕረት የገጠር መንደር ላይ የተወለዱ ሲሆን፣ ላለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ ነበሩ፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...