Friday, July 12, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የስኳርና የምግብ ዘይት ዋጋ ጭማሪ የጥር ወር ግሽበቱን አባብሶታል

ተዛማጅ ፅሁፎች

የምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጥ የሆኑት ስኳር፣ ዘይትና ቡና በጥር ወር ዋጋቸው በማሻቀቡ ምክንያት የወሩ ግሽበት ምጣኔ ጭማሪ ማሳየቱን የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ኤጀንሲው በየወሩ የሚያወጣው የዋጋ ግሸበት መረጃ እንደሚያሳው፣ የምግብ ዋጋ ግሽበት በታኅሳስ ወር ከነበረበት የ21.3 በመቶ ወደ 23.1 በመቶ ከፍ ያለ የቁጥር ብልጫ አሳይቷል፡፡

በጥር ወር አብዛኞቹ የእህል ዓይነቶች ጭማሪ እንደታየባቸው ያመለከተው ሪፖርቱ፣ በተለይም በስኳር፣ በምግብ ዘይት፣ በቅመማ ቅመም፣ በድንችና በቡና ላይ በተከታታይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ በመቀጠሉ የጥር ወር የዋጋ ግሽበት ምጣኔ እንዲጨምር አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቁሟል፡፡

በታኅሳስ ወር ዘይትና ቅባት 32.0 በመቶ፣ ድንችና ሌሎች ሥራ ሥሮች 16.7 በመቶ፣ እንዲሁም ቡና በኢንዴክሶቻቸው ጭማሪ ማሳየታቸውን ያመለከተው ሪፖርቱ፣ እነዚህ የምግብ ሽቀጣ ሸቀጦች ለተከታታይ ወራት ምንም ዓይነት የዋጋ ቅናሽ ሳታይባቸው በጥር ወርም እንደቀጠለ አመላክቷል፡፡

እንደ ምግብ ነክ ሸቀጣ ሸቀጦች ሁሉ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦችም በጥር ወር ከፍተኛ ግሽበት አስመዝግበዋል፡፡ በተለይም በአልኮል፣ በጫት፣ በነዳጅና በወርቅ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ምግብ ነክ ያልሆኑ ክፍሎች የዋጋ ግሽበትን በወሩ እንዲጨምር እንዳደረገው ኤጀንሲው የላከው መግለጫ ያሳያል፡፡

አጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር በ1.6 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን፣ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወር ጋር ሲነፃፀር ደግሞ በ19.2 በመቶ ከፍ ብሎ ታይቷል፡፡ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች በተደጋጋሚ እንደሚያስጠነቅቁት የዋጋ ግሽበት ጉዳይ እየተንከባለለ የመጣ ውጤት በመሆኑ፣ በሁሉም ዘርፍ ሰፊ የስትራቴጂና ተቋማዊ ሥራዎች መከናወን እንዳለባቸው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች