Monday, January 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊእጅግ ዝቅተኛ ተከፋይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞችን ባለድርሻ የሚያደርግ ማኅበር ለማደራጀት ስምምነት ተፈረመ

እጅግ ዝቅተኛ ተከፋይ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞችን ባለድርሻ የሚያደርግ ማኅበር ለማደራጀት ስምምነት ተፈረመ

ቀን:

እንኳን ቤተሰቦቻቸውን ሊደግፉ ቀርቶ ለራሳቸው የዕለት ቀለብ ሊበቃቸው የማይችል እጅግ ዝቅተኛ (ከ1,000 ብር እስከ 2,000 ብር ድረስ) የወር ደመወዝ የሚከፈላቸውን ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞችን ባለድርሻ የሚያደርግ የኅብረት ሥራ ማኅበር ለማደራጀት፣ ሦስት ተቋማት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

የመግባቢያ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ የፌዴራል የኅብረት ሥራ ኤጀንሲና ፕሮጀክቱን ‹‹ይደግፋል›› የተባለው መሠረቱ ኔዘርላንድ እንደሆነ የተነገረው ‹‹አይዲኤች›› የተባለ ተቋም ነው፡፡ ኮርፖሬሽኑን በመወከል ምክትል ሥራ አስፈጻሚው አቶ ሽፈራው ሰለሞን፣ ኤጀንሲውን በመወከል ምክትል ዳይሬክተሩ አቶ አብዲ ሙመድና አይዲኤችን በመወከል ደግሞ አቶ ቴዎድሮስ ይልማ የመግባቢያ ሰነዱን ፈርመዋል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን በተፈራረሙበት ወቅት እንደተነገረው፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ውስጥ የሚሠሩ ዜጎች ደመወዛቸው ለወር ስለማያደርሳቸው ሥራቸውን ተረጋግተው መሥራት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም በፓርቹ ውስጥ ያለው ሠራተኞች ፍልሰት በዓመት ውስጥ 90 በመቶ እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

ምንም እንኳን ኢንዱስትሪ ፓርኮች እጅግ በጣም የሚስደስቱና እንደ አገር የሚያኮሩ ቢሆኑም (በተለይ የሐዋሳው ኢንዱስትሪ ፓርክ)፣ በኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ እጀግ በጣም ርካሽ የሆነ የሰው ጉልበት ያለበት አገር መሆኑ ጎልቶ ስለሚነገር፣ ከውጭ የሚመጣው ባለሀብት (ኢንቨስተር) እንኳ፣ በዓለም አቀፍ የተቀመጠውን ደረጃ (Stanedared) የሠራተኛ ክፍያ እንደማይከፍል ተገልጿል፡፡

በአገሪቱ የተገነቡት ከ13 በላይ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ከመቶ ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል የፈጠሩ ቢሆንም፣ ከሚከፈላቸው ደመወዝ አንፃር ኑሯቸውን ተረጋግተው መምራት እንደማይችሉም ተጠቁሟል፡፡

በአገሪቱ 390 ሺሕ መሠረታዊ የሠራተኛ ማኅበራትና 389 የኅብረት ሥራ ማኅበራት ከመኖራቸውና የተሻለ ሥራ እየሠሩ ከመሆናቸው አንፃር፣ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሠራተኞችንም በኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት፣ የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞችን በኅብረት ሥራ ማኅበር ለማደራጀትና በሞዴልነት ለመውሰድ በመታቀዱ የመግባቢያ ሰነዱ መፈረሙንም ተናግረዋል፡፡

ሁሉንም ሠራተኞች ያቀፉ ሆኖ፣ የድርሻ መዋጯቸውን በረዥም ጊዜ ክፍያ እንዲያጠናቅቁ በማድረግና ‹‹የእኔነት›› ስሜት እንዲያድርባቸው በማድረግ ማኅበሩ በድጋፍ ሰጪ ድርጅቶች (እንደ አይኤልኦ) እና ሌሎችም ድርጅቶች እንዲጠናከር በማድረግ፣ ራሳቸውን እንዲችሉና የራሳቸውን ሥራ በመሥራት እንዲለወጡ የማድረግ ራዕይ ይዞ የተነሳ መሆኑም ተነግሯል፡፡

የሚቋቋመው ማኅበር ለሠራተኛው ሁለገብ አገልግሎት የሚሰጥ ሆኖ፣ የሠራተኛውን ኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ሌሎችም የጋራ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት፣ በተናጠል ሊፈቷቸው ያልቻሏቸውን ችግሮች በጋራ ለማቃለል መቋቋሙንና በጋራ ባለቤትነት የሚያስተዳድሩት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

ማኅበሩ የግብዓት አቅርቦት ሰንሰለቱን በማሳጠር ከአርሶ አደሮችና አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶችን በቀጥታ ማግኘት ስለሚችል፣ ሠራተኛው ከመደበኛ ዋጋው ባነሰ ከማግኘቱም በተጨማሪ፣ የትርፍ ተካፋይ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡ እስከዚያው ድረስ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ክበቦችን በማቋቋም ሠራኛው በዝቅተኛ ክፍያ የሚመገብበትን አሠራር በማዘጋጀት፣ ምርታማ ሠራተኛን በአንድ ቦታ ማቆየት እንደሚቻል ተነግሯል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የገጠር መሬት ማሻሻያና የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ከቅርብ ወራት ወዲህ መሬትን በተመለከተ ጠንከር ያሉ የለውጥ...

በፖለቲከኞች እጅ ያለው ቁልፍ

ኢትዮጵያ በተለይ ካለፉት አምስት ዓመታት ወዲህ ሰላሟ መረጋጋት አቅቶታል፡፡...

የኤክሳይስ ታክስ ረቂቅ አዋጅ ፓርላማው ያፀደቀውን አዋጅ የሚጥሱ ድንጋጌዎችን በማካተቱ እንዳይፀድቅ ተጠየቀ

ሰሞኑን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የኤክሳይስ ታክስ ማሻሻያ...

በፀጥታ ችግር ሳቢያ ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው አማራ ክልል የገቡ ዜጎች ቁጥር 800 ሺሕ መድረሱ ተነገረ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 112 ሺሕ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ...