የቀድሞው የኢትዮጵያና አዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ክቡር ገና፣ ሰሞኑን ከ‹ዘ ሪፖርተር ጋዜጣ› ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የተናገሩት፣ ለከንቲባነት የሚደረገው ፉክክር ቀላል እንደማይሆንና ብቃት ያላቸው ተወዳዳሪዎች ከኢዜማም ሆነ ከሌሎች ፓርቲዎች ሊቀርቡ እንደሚችሉም ሳይገልጹ አላለፉም፡፡ አቶ ክቡር፣ በመጪው ግንቦት ወር በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲን ወክለው በሚኖሩበት ወረዳ 21 እና 22 ምርጫ ክልል ለአዲስ አበባ ምክር ቤት እንደሚወዳደሩ ባለፈው ወር አጋማሽ መገለጹ ይታወቃል፡፡