Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየኤልያስ መልካ አዎንታዊ የሙዚቃ ግጥሞች ሲገለጡ

የኤልያስ መልካ አዎንታዊ የሙዚቃ ግጥሞች ሲገለጡ

ቀን:

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ካላቸው ውስጥ ስሙ ይወሳል፡፡ በተለይም የዘጠናዎቹ ሙዚቃ ሲነሳ ስሙ ለአፍታ አይዘነጋም፡፡ ስለአገሩ፣ ስለሃይማኖትና ከሥርዓተ ፆታ ጋር በተያያዘ ያለው ሚዛናዊ አመለካከቱ በሰዎች ዘንድ ቅቡልነትን እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡

የዚህ የሙዚቃ ባለሙያ አገር ‹‹ጠይም›› መሆኗንም በሙዚቃ ግጥሞቹ ለማንፀባረቅ ጥሯል፡፡ የጌቴ አንለይ የሙዚቃ ሥራ ውስጥ ጥቁር፣ ጠይምና ቀይ ድብልቅ ጠይምን አጉልቶ አሳይቷል፡፡

የቀይ ጥቁር ጠይም (አሸነፈች) የግጥምና ሙዚቃን ቅንብር በኤልያስ መልካ የተዘጋጀው ነጠላ ዜማ የምር አገሩን ገልጾበታል የሚሉ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከግጥሞቹ የተወሰኑ ስንኞችን ከዚህ በታች እንመልከት፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

‹‹የሚነጣው ሁሉ የሚጠቁረውን ሰው

የቀይ ዳማው ሰው በክፉ አይነሳም (አይታማም)

ከእሷ ፊት ማንም ሰው ከእሷ ፊት ማንም ሰው (2X)

ቢያሞቁ ቢያከቧት ቢያደንቁ ወይ ቢክቧት

አታልፍም ግን ሰምታ ያስከፋታል ሐሜት (2X)

በእናቴ በአባቴ በዘር ተዋልዷታል

ዘመድ ናት ይህቺ ልጅ ይመለከታታል

አለች ቆጣ ቆጣ ፊቷን ከፋው እሷ

የሩቅ አርገው ቢያሟት ጠይም ሰው ለራሷ

ጥቁርስ ቢታማ እንዴት አያማትም

ጠይም ናት ልጅቷ ባዕድ ሰው የላትም…

የሁሉም ቀለም ኅብር ‹‹ጠይም›› በአገሩ ያለው የቀለም ዓነት ድምር ‹‹ጠይም›› መሆኑን በሙዚቃ ግጥሞቹ ተስተውለዋል፡፡

በዚህ ሥራ ውስጥ ቀይ፣ ጥቁርና የቀይ ዳማ ሁሉ ሲነካ የሚያማት አንዲት ታዳጊ እንዳለች ያመላክታል፡፡ የሁሉም ቀለም ጥምር ውበት ያለው ‹‹ጠይም›› አገሩን ገልጾበታል፡፡ አንዱ ቀለም ሲነካ የሚታመመው ጠይም ታዳጊ ሁሉም የቀለም ዓይነት ሲነኩበት የማትወደው ‹‹ኢትዮጵያን›› የገለጸበትን መንገድ ብዙዎች ያደንቁለታል፡፡

የኤልያስ መልካ ‹‹ኢትዮጵያ›› ጠይም ናት፡፡ የቀይ፣ የጥቁርና የቀይ ዳማ ድብልቅ ክልስ ‹‹ጠይም›› ቀለም ለእርሱ ኢትዮጵያ ናት፡፡

በቀጥታ ባይሆንም በግጥሙ አንዱ ሲነካ አገር እንደሚከፋት በጥቅል ለማንሳት ጥሯል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋዎችና ባህሎች አካዴሚ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በመሆን ‹‹ዘፈንና ሥነ ቃል ከአገራዊ ፋይዳ አንፃር!›› በሚል መሪ ሐሳብ ጥር 27 እና 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ባሰናዳው መድረክ የተለያዩ ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

ከእነዚህ ጽሑፎች መካከል የኤልያስ መልካ የዘፈን ግጥሞች ከአዎንታዊነት (Positivism) ፍልስፍና አንፃር ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ ሕይወቱ እስኪያልፍ ድረስ በሠራው ሥራዎች ላይ የቀረበ ጽሑፍ ነው፡፡

ጽሑፉን ያቀረበው ጋዜጠኛ ይናገር ጌታቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በሙዚቃ ታሪክ በኤፍኤም 97.1 ላይ የሚሠራ፣ እንዲሁም በኤልያስ መልካ ሥራዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በቅርቡ የጻፈውን መጽሐፍ ለኅትመት ሊያቀርብ መሆኑን በመድረኩ ተነስቷል፡፡

የኤልያስ መልካ ግጥሞች ከተዜሙ ዜማዎች ውስጥ ብስራት ኃይለ ማርያም (ቤሪ)፣ ኢዮብ መኮንን (ነፍስ ኄር)፣ ኃይሌ ሩት፣ ዘሪቱ ከበደና ሌሎችም ያዜሙት ውስጥ ይጠቀሳል፡፡

በድምፃዊ ብሥራት ኃይለ ማርያም (ቤሪ) የተዜመው ‹‹ህሊና›› የሚለው ሙዚቃ ውስጥ ስለዘርና ሌሎች ኢትዮጵያን የሚያተራምሱ ጉዳዮችን በጥልቀት የታየበት ሙዚቃ ነው፡፡

የሰው ልጅ ወዶ ባልተወለደው ዘር እንዲያውም የሰው ልጅ ራሱን እንደማይፈጥር፣ ማንም ከማንም የሚበልጥ እንዳልሆነ የተንፀባረቀ ሲሆን፣ ይህን ማስተዋል ያቃተው እንዳለ የሚያመለክት ዜማ ነው፡፡

‹ህሊና›

‹‹ማን ቀድሞ ዓይቶ

መልኩን አውቆ ተወለደ

መርጦ መጣ ጠቁሮ ነጣ

ሁሉ አብሮት እንጂ

ሰው ተማክሮ መቼ ራሱን ፈጥሮ

እንዲህ አብሮት እንጂ

ህሊና ይህን ካላስተዋለ

ሰውን በዘር ኮናኝ ብዙ አለ›› …

የዚህ የሙዚቃ ግጥም ከአሁናዊ የፖለቲካ አመለካከት ጋር እጅጉን የሚያሳይ ነው፡፡ በዘር በሚኮነንበት፣ በዘር ሰው ወዶ ፈቅዶ ባልተፈጠረበት የሰውን በዘር መኮንን እጅጉን ከባድ መሆኑን የሚያስገነዝብ ግጥም ነው፡፡

ማን ቀድሞ በልጦ፣ ዘር ነገዱን መርጦ ‹‹ህሊና›› በሚል የተሰየመው ዜማ እጅጉን የተመሠገነ አስተዋይነትን እንዲበልጥ መካሪ ሙዚቃ መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡

ለኤልያስ መልካ ‹‹ሴት ልጅ››ን የሚገልጽበት መንገድ እጅጉን የሚወደድ መሆኑ ይናገር በጽሑፉ አሳይቷል፡፡ በእዮብ መኮንን የተዜመው ‹‹ወኪል›› የሚለው ሙዚቃ ሴት ልጅ ምን እንደሆነች በይበልጥ አሳይቷል፡፡

‹‹ወኪል ነሽ ከላይ

ደግነቱን እንይ››  

ከእኔ በላይ ነው ገባኝ ለእኔ ያወቀልኝ

ፍፁም ሰላም ነው ከእኔ ጋር ሳወዳድረው

የእርሱ ምርጫ ነሽ ለእኔ ወዶ የሸለመሽ

መቼ አገኝሽ ነበር ምርጫ ቢሰጠኝ

ነበር ልታመልጪኝ ለእኔ ከእኔ በላይ

ያሰበው ወዳጄ አደረሰኝ ደጄ…››    

የኤልያስ መልካ ፍልስፍና በሙዚቃ ግጥሞች ውስጥ ሲንፀባረቁ ይታያል፡፡ በብዙ ሙዚቃዎች የሚሰሙ የአገር አገላለጽ ቃላቶች አሉ፡፡ አፈር፣ ጋራ ሸንተረር፣ ወንዝና ተራራ እያሉ የሚገልጹ ዘፈኖች ብዙ ናቸው፡፡  

በኤልያስ መልካ የሙዚቃ ግጥሞች ውስጥ ሌሎች የሙዚቃ ግጥሞች ኢትዮጵያ ከአምሳለ መሬት ወደ አምሳለ ሰውነት የቀየረበት መንገድ ያሳያል፡፡ ለምሳሌ፣

ወሬ ከቢላ ታኒታና

መሸ ከበላ ታኒታሻ

መሬት አይደለም ማገር ጣሪያው

ነፍስሽ ነው ቤቱ የአገር ሥፍራው

አንቺ ነሽ አገሬ ሆያ..

ነፍስ አለሽ አካሌ ሆያ..

በዚህ ሙዚቃ ኤልያስ መሬት አይደለም አገሩ ሰው ነው አገሩ ብሎ የሚሞግትበት የሙዚቃ ግጥም ነው፡፡ በ1950ዎቹ የነበረው የሙዚቃ አረዳድ ስንመለከት የዓለማየሁ ፈንታ ሙዚቃ በምሳሌነት በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ጀግኖች በብርታት እየተተኮሱ

ተዋግተው የለም ወይ ጋራው ለንጉሡ

የኢትዮጵያ ጋራ ኮረብታው በነገር

አያልቅም የዋለው ውለታ .. እያለ ይቀጥላል፡፡ በዓለማየሁ ፈንታ በኢትዮጵያ የጀግንነት ተጋድሎ ውስጥ ከሰው ባልተናነሰ ጋራው፣ ኮረብታው የነበረውን አስተዋጽኦ ያስረዳል፡፡

በዚያን ጊዜ ብቻ ሳይሆን አሁንም ድረስ አገር በተራራ፣ በኮረብታና በወንዝ የመመሰል ነገር ይስተዋላል፡፡ በኤልያስ መልካ አረዳድ ግን አገር ሰው ሰው መሆኑን የሚያስረዳ የሙዚቃ ግጥሞች ውስጥ የራሱን ፍልስፍና ያንፀባርቃል፡፡

ከአንቺ አይብስ ሁልጊዜም

ዳሎልም ተከዜም

ለፍቅር ነው እንጂ ማዜም

በፍቅር እንጂ ማዜም.. እያለ ይቀጥላል፡፡ የኤልያስ መልካ የሙዚቃ ግጥሞች እጅጉን የተለዩ እንደሆኑ ብዙዎች ይሞግታሉ፡፡ ከአዎንታዊ የሙዚቃ ግጥሞቹ በተጨማሪ የእያንዳንዱ ክንውኖች፣ ፖለቲካ ማኅበራዊ፣ ሃይማኖታዊና ሌሎች ነገሮች ያለውን ፍልስፍና በብዙዎች አድናቆት ተችሮታል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...