Tuesday, November 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የኢንዱስትሪዎች ትስስር ምክክር

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና የኢንዱስትሪዎች ትስስር ምክክር

ቀን:

በሳይንስ፣ በፈጠራና በምርምር የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ያሟላ ምቹና በቂ፣ በሚፈለገው ደረጃም የሠለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራትና ግብዓት ለማቅረብ እንዲቻል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል፡፡

ይሁን እንጂ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) አነጋገር፣ የሠለጠነ የሰው ኃይል በሚያቀርቡትና በሚጠቀሙት አካላት መካከል ሰፊ ክፍተት አለ፡፡ የሚቀርበውም የትምህርት አገልግሎት የአግባብነትና የጥራት ችግር ይታይበታል፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነት ክፍተቶችን ለመሙላት ተቀራርቦ፣ ተደማምጦና ተመካክሮ መሥራት ያስፈልጋል፡፡

‹‹ትስስር ለአገራዊ የልማት ግቦች ስኬት›› በሚል መሪ ቃል የካቲት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በሒልተን አዲስ አበባ የተካሄደውን የከፍተኛ ትምህርትና ሥልጠና፣ የምርምር ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ምክክር መድረክን አስመልክተው ሚኒስትሩ እንደገለጹት፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያሠለጠኑ የሚያወጧቸው ምሩቃን ለኢንዱስትሪው የሚመጥኑ፣ የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎችም ፈጠራና ቴክኖሎጂን ለማምረት የሚያግዙ እንዲሁም ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ  የሚያስችሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

በአሥር ዓመት መሪ ዕቅድ ለኢንዱስትሪው ዘርፍ በጣም ምቹና ብቁ የሆነ የኢንዱስትሪውን ፍላጎት የሚያሟላ የሰው ኃይል  ከማቅረብ አንፃር፣ እንዲሁም ጉዳዩ በይበልጥ ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት በመናበብ ለመሥራት የሚያስችል በቂ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በበኩላቸው የአሁኑ ዘመን አጠቃላይ ሁኔታ በኢንዱስትሪዎች መካከል በጣም ከፍተኛ ውድድር ያለበት፣ እንዲሁም አራተኛው የኢንዱስትሪ አብዮት ወይም ኢንተለጀንስ ኢንዱስትሪ ያደገበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡

ይኼም ቀጣይነት ባለው የጥናትና ምርምር እንዲሁም ቴክኖሎጂ ዕድገት ላይ የተደረሰበት መሆኑን ገልጸው፣ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች ግን ውድድራቸው በአካባቢያቸው ከሚገኙ ወይም አኅጉሩ ውስጥ ካለው ኢንዱስትሪ ብቻ ሳይሆን በሁሉም አኅጉሮችና በዓለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር መሆን እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡

ይህ ዓይነቱ የኢንዱስትሪዎች ተወዳዳሪነት አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው ቀጣይነት ባለው የምርምርና ጥናት እየተደገፈ ሲሄድ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለምርምር ተቋማትና ለኢንዱስትሪዎች ዕድገት የዩኒቨርሲቲዎች ድርሻና ኃላፊነት ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ድህነት በዕውቀት፣ በቴክኖሎጂና በሳይንስ ካልሆነ በስተቀር በሌላ በምንም ዓይነት ሁኔታም ቢሆን ሊፈታ አይችልም፡፡ በአገሮችም መካከል የለው ልዩነት የቴክኖሎጂ ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በተፈጥሮ ሀብትና ፀጋ ረገድ ኢትዮጵያ በዓለም የተሻሻለ ተወዳዳሪ ልትሆን እንደምትችል ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

ነገር ግን ልዩነታችን የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ልዩነት ስለሆነ ይህንን ልዩነት ለማጥበብ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋሞች መጠንከር አለባቸው ሲሉ አክለዋል፡፡

በትስስር ዙሪያ ከሚታዩ በርካታ ጉድለቶች መካከል ዋናዎቹ የሕግ ማዕቀፎችን ያለማወቅ፣ ወደ ተግባር ለማስገባት የሚታዩ እንቅፋቶች የቅንጅት መላላት ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ካለው ነባራዊ ይዞታ ጋር የሚዛመድ የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ ሥራዎች በእጅጉ አለመከናወናቸውን ተጠቃሾች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ ልምዳቸውን ያካፈሉት የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ በላይነህ ክንዴ፣ የኢትዮጵያን ድህነት መፍታት የሚቻለው በትምህርት፣ በዕውቀትና በሥራ መሆኑን ጠቁመው፣ ከዚህ አንፃር የትምህርት ተቋማት ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ካመረቱ ዕድገት ሊመጣና ድህነትም ሊቀረፍ ይችላል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተቋማት ትስስር በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በኢኖቬሽን ፖሊስ ውስጥ ቁልፍ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ መሆኑንና በ1986 ዓ.ም. ሥራ ላይ የዋለውና በ2004 ዓ.ም. የተሻሻለው ፖሊሲው በአሁኑ ጊዜ በመከለስ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ

ለሲኒመር ትሬዲንግ አ/ማ አባላት በሙሉ የጠቅላላ ጉባኤ የስብሰባ ጥሪ ሲኒመር ትሬዲንግ...

የባህር በር በቀጣናዊ ተዛምዶ ውስጥ

በበቀለ ሹሜ መግቢያ በ2010 ዓ.ም. መጋቢት ማለቂያን ይዞ ዓብይ አህመድ በጠቅላይ...

ሥጋት ያስቀራል ተብሎ የሚታሰበው የጫኝና አውራጅ መመርያ

በአዲስ አበባ ከተማ በሕገወጥ መልኩ በመደራጀት ማኅበረሰቡ ላይ እንግልትና...

ማወቅ ወይስ አለማወቅ – ድፍረት ወይስ ፍርኃት?

በአሰፋ አደፍርስ ወገኖቼ ፈርተንም ደፍረንም የትም አንደርስምና ለአገራችን ሰላምና ክብር...