Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየትግራይን ስፖርት የመታደግ ዘመቻ

የትግራይን ስፖርት የመታደግ ዘመቻ

ቀን:

በትግራይ ክልል ከሦስት ወራት በፊት በተከስተው ጦርነት ምክንያት የችግሩ ገፈት ቀማሽ ከሆኑት ዘርፎች  ስፖርትና መሠረተ ልማቱ ይጠቀሳሉ፡፡

በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት ሊከናወኑ የታቀዱ ስፖርታዊ ክንውኖች ሁሉ ተቋርጠዋል፡፡ ትግራይ በአትሌቲክሱ በዓለም አቀፍ የውድድር መድረኮች ‹‹Yifter The Shifiter›› ማርሽ ቀያሪው በሚል የሚታወቀውን ምሩፅ ይፍጠርን ጨምሮ እንደነ ገብረ እግዚአብሄር ገብረ ማርያም፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ሐጎስ ገብረ ሕይወት፣ ለተሰንበት ግደይ፣ ጉዳፍ ፀጋይና ሌሎችንም ያፈራ እያፈራም የሚገኝ ነው፡፡

በእግር ኳሱ በፕሪሚየር ሊግ ደረጃ ሲወዳደሩ የምናውቃቸው ያለፈው ዓመት የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታን ጨምሮ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲና ስሑል ሽረ ሲጠቀሱ በከፍተኛና በብሔራዊ ሊጉ እንዲሁም በየደረጃው የሚወዳደሩ በርካታ የእግር ኳስ ቡድኖችን አቅፎ እያስተዳደረ የሚገኝ ክልል ነው፡፡
በብስክሌት አሁን ላይ በዓለም አቀፉ የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስያሜውን እንደያዘ ወደ 2021 የተሸጋገረው ቶኪዮ ኦሊምፒክ ላይ ኢትዮጵያን በመወከል ለመሳተፍ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ የምትገኘው እንስት ሰላም አመሓ እንዲሁም 2016 በብራዚል ሪዮ ኦሊምፒክ ላይ የተወከለው ፅጋቡ ገብረ ማርያምና ሌሎችንም ከዋክብትን ለአገሪቱ ያበረከተ ክልል ነው፡፡ በርካታ የአትሌቲክስ ክለቦችን ጨምሮ በክልሉ የሚታወቁ የተለያዩ ስፖርቶች የሚዘወተሩበት ስለመሆኑም ይታወቃል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በጦርነቱ ሳቢያ የክልሉን ስፖርት በበላይነት የሚያስተዳድረው የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ንብረቶችና መሰል መሠረተ ልማቶች መውደማቸው ይነገራል፡፡ ስለሆነም በችግሩ ምክንያት የተዳከመውንና የተቀዛቀዘውን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሁም መሠረተ ልማቱ እንዲያንሰራራ ለማድረግ በስፖርት  ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ የሚመራ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል ተቋቁሟል፡፡

በምክትል ኮሚሽነሩ የሚመራው ይህ ግብረ ኃይል፣ በትግራይ ክልል በተከሰተው የሰላም ዕጦት ምክንያት ከተጎዱት ተቋማት መካከል የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ለበርካታ ዓመታት ያፈራቸው ሀብቶች ማለትም የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች፣ የስፖርት ትጥቆችና ሌሎች መሠረተ ልማቶች ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ ይቻል ዘንድ ያለመ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ኮሚሽኑ የጀመራቸው እንቅስቃሴዎች በዚህ ሳምንት በስፖርቱ መንደር ከተከናወኑ ክስተቶች አንዱ መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ዜጎች በትልቁ ሊደግፉትና ሊከተሉት የሚገባ እንደሆነ የብዙዎች እምነት ነው፡፡

በመሆኑም በስፖርት ኮሚሽን አማካይነት የተቋቋመው ይህ የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረ ኃይል፣ ከየካቲት 11 ቀን 2013 .. ጀምሮ እንቅስቃሴ መጀመሩ ኮሚሽኑ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባሠራጨው መግለጫ አሳውቋል፡፡  ግብረ ኃይሉ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጨምሮ የአገር አቀፍ ስፖርት ማኅበራት፣ ተጠሪ ተቋማትና የክልልና ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽኖችን ማካተቱን መግለጫው ያስረዳል፡፡ ግብረ ኃይሉ የደረሰበትን ደረጃና የሚያደርገውን ድጋፍ በሒደት ለኅብረተሰቡ አስታውቃለሁ ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...