Tuesday, February 27, 2024

በፀጥታ ሥጋቶችና በግጭቶች ዓውድ ውስጥ የተጀመረው የምረጡኝ ቅሰቀሳ ፈተናዎች

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

ዘንድሮ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው አጠቃላይ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ወይም የምርጫ ዘመቻዎቻቸውን በይፋ የሚጀምሩበት ዕለት ሰኞ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም. እንደሆነ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው የምርጫ ሒደቶች መርሐ ግብርን የጊዜ ሰሌዳ ያመለክታል።

ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ ቀን ለተቆረጠለትዚህ አጠቃላይ ምርጫ ለመወዳደር ዝግጁ የሆኑ ፓርቲዎችም ዝግጅቶቻቸውን አጠናቀው፣ የምርጫ ዘመቻው የሚጀመርበትን የካቲት 8 ቀን እየተጠባበቁ ነበሩ። 

ከእነዚህ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የምርጫ ዘመቻው የሚጀመርበትን ቀን በጉጉት ከሚጠብቁት መካከል አንዱ ስለመሆኑ፣ በተለያዩ ዘርፎች ያዘጋጃቸውን ፖሊሲዎች ለማስተቸት ሲያደርጋቸው የነበሩ ውይይቶች ይጠቁማሉ። 

ነገር ግን የምርጫ ዘመቻው በሚጀመርበት ዕለት ዋዜማ አመሻሽ ላይ፣ በኢዜማ አመራሮች መካከል ቀዝቃዛ ድንጋጤ የፈጠረ አሳዛኝ ዜና ተሰማ። 

የኢዜማ በቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 የኢዜማ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ግርማ ሞገስ፣ የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ገደማ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመተው ተገደሉ።

የአባሉን መገደል አስመልክቶ ኢዜማ በሰጠው መግለጫ አቶ ግርማ ከመገደላቸው አስቀድሞ ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርሳቸው እንደነበር፣ ኢዜማም እንደ ፓርቲ በቢሾፍቱ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ ከፍተኛ ጫና ይደርስበት እንደነበር ገልጿል።

ኢዜማ በቢሾፍቱ ከተማ የፖለቲካ እንቅስቃሴዎችን እንዳያደርግ ከፍተኛ ጫናና ማዋከብ ይገጥመው እንደነበረ፣ በከተማው ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ለማድረግ በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ በከተማው አስተዳደር እንቢተኝነት ምክንያት አለመሳካቱን ይገልጻል። 

በቢሾፍቱ ከተማ የኢዜማ ምርጫ ወረዳ መዋቅር የሚጠቀምበትን ጽሕፈት ቤት ለመክፈት እንዳልተቻለ የሚገልጸው ፓርቲው፣ ‹‹በከተማው ኢዜማ ከነዋሪዎች ጋር ሊያደርግ የነበረውን ስብሰባም ሆነ ጽሕፈት ቤት ለመክፈት ይደረግ የነበረውን እንቅስቃሴ በግንባር ቀደምትነት ለማስተባበር ሲሠሩ የነበሩት አቶ ግርማ ነበሩ፤›› ብሏል። 

ከዚህም የጎላ እንቅስቃሴያቸው ጋር በተያያዘ በየጊዜው እየጨመረ የመጣ ዛቻና ማስፈራሪያ ይደርስባቸው እንደነበር ፓርቲው ገልጿል። 

ይህንንን ተደጋጋሚ ዛቻና ማስፈራሪያ በተመለከተም ኢዜማ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ለምርጫ ቦርድ፣ እንዲሁም ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና ለሌሎች ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት አስቀድሞ አስታውቆ እንደነበር ገልጿል። 

በመሆኑም የመንግሥትና ምርጫው የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላት ለቀረበው አቤቱታ ፈጣን ምላሽ ባለመስጠታቸው፣ መምህር ግርማ በጥይት ተገድለው መሞታቸውን ይገልጻል።

የሁለት ልጆች አባትና የቤተሰብ አስተዳዳሪ የነበሩት የኢዜማ ፓርቲ የቢሾፍቱ ቅርንጫፍ የነበሩት አቶ ግርማ ሞገስ መገደላቸውን ተከትሎ፣ የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ በሰጡት መግለጫ ግለሰቡ ከመገደላቸው በፊት የተለያዩ ዛቻና ማስፈራሪያዎች ይደርሷቸው እንደነበር አረጋግጠዋል።

‹‹ከአቶ ግርማ ጋር ግጭት የነበራቸው ግለሰቦች ያስፈራሯቸውና ይዝቱባቸው እንደነበር መረጃ ተገኝቷል፣ ማስፈራሪያና ዛቻ ያደርሱ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱም በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው፤›› ሲሉ የቢሾፍቱ ፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ተናግረዋል።

ነገር ግን ግለሰቡ የኢዜማ አባል ስለመሆናቸው እንደማያውቁ ኮማንደሩ በይፋ የተናገሩ ሲሆን፣ ግለሰቡ የፖለቲካ ፓርቲ አባል መሆናቸውና ግድያው ከዛ ጋር ግንኙነት የሚኖረው ከሆነ በምርመራ እንደሚጣራ ለሚዲያዎች ተናግረዋል።

የፖሊስ መምርያ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ በሰጡት መግለጫ ክህደት ተፈጽሞብኛል ያለው ኢዜማ በበኩሉ፣ ግድያው የተቀነባበረ በመሆኑ በጥልቀት እንዲመረመርለት ጠይቋል።

‹‹የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ ጉዳዩን ተከታትሎ በሕግ የተጣለበትን ፍትሕን የማስከበር ሥራውን ከመወጣት ይልቅ፣ የአባላችን መገደልን አስመልክቶ የከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ፣ ሟች አቶ ግርማ የኢዜማ አባል እንደነበሩ እንደማያውቁ በመካድ የግድያውን አቅጣጫ ለማስቀየር የሄዱበት ርቀትና ከዚህ በፊት በከተማው የፓርቲያችን እንቅስቃሴ ላይና አባሎቻችን ላይ ይደርስ ከነበረው መዋከብና እንግልት ጋር ተደምሮ፣ ግድያው የተቀነባበረ እንደሆነ ያመላክታል፤›› ብሏል።

ይህንን መሠረት አድርጎም የአቶ ግርማን ግድያ በተመለከተ የሚደረገው ምርመራ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚገኙ አካላትንም እንዲካተቱ ጥሪ አቅርቧል።

ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ በሚጀመርበት ዕለት ዋዜማ አመሻሽ ላይ አባሉ በጥይት የተገደሉበት ቢሆንምበማግሥቱ የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም. የምርጫ ቅስቀሳውን በአዲስ አበባ ጎዳናዎች በይፋ ጀምሯል።

ይሁን እንጂ ይህ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ጅማሮም እንከን አልባ አልነበረም። ፓርቲው ትራንስፖርት የሚፈልጉ የከተማዋ ነዋሪዎች ትራንስፖርት ለማግኘት ተሠልፈው በሚጠባበቁባቸው አካባቢዎች የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አውቶቡሶችን በነፃ በማቅረብ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ነዋሪዎችን በማጓጓዝ፣ የፖለቲካ ፕሮግራሞቹን በአመራሮቹ አማካይነት በማስተዋወቅ የምርጫ ዘመቻውን በተለየ መንገድ ጀምሯል። 

ይሁን እንጂ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የምርጫ ዘመቻውን በተጠቀሰው መንገድ ለማካሄድ ያደረገው ሙከራ በፖሊሶች ተስተጓጉሏል። 

‹‹ቅስቀሳው ሊደረግባቸው ከታሰቡ ቦታዎች አንደኛው በሆነው ሽሮሜዳ አካባቢየምርጫ ቅስቃሳ ስለመጀመሩ አናውቅም› ባሉ የፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት ቅስቀሳው ሳይደረግ ተስተጓጉሏል፤›› ሲል ፓርቲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። 

የምርጫ አዋጁ ቁጥር 1162 የምርጫ ቅስቀሳ ስለማካሄድ በሚልዕስ በአንቀጽ 43 ሥ ባሰፈረው ድንጋጌ በዕጩነት ተመዘግቦ ዕውቅና የተሰጠው ተወዳዳሪ፣ ለድምፅ መስጫው አራት ቀን እስከሚቀረው ድረስ ከከተማ አስተዳደርም ሆነ ከክልል መንግሥታት ፈቃድ መጠየቅ ሳያስፈልገው በማሳወቅ ብቻ የምርጫ ቅስቀሳ የማካሄድ መብት እንዳለው ይደነግጋል። 

ኢዜማ የምርጫ ቅስቀሳ በይፋ በሚጀመርበት ዕለት ዋዜማና በዕለቱ የገጠሙትን ተግዳሮቶች ከላይ በተቀመጠው መንገድ ለማሳያነት ይቅረቡ እንጂ፣ ተመሳሳይ ብቻ ሳይሆን ከዚህ የከፉ ተግዳሮቶች የገጠሟቸው ፓርቲዎች አቤቱታቸውን ለምርጫ ቦርድ እያሳወቁ ይገኛሉ። 

ከእነዚህም መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንጎረንስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች አባሎቻቸው እየታሰሩና እየተገደሉ እንደሆነ፣ ቅርንጫፍ ሕፈት ቤቶቻቸውም እንደተዘጉባቸው የሚገልጽ አቤቱታ በማሰማት ላይ ናቸው። 

በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ ይካሄዳል ብለው እንደማያስቡ በመግለጽ፣ ሁኔታው ካልተስተካከለ ከምርጫ ውድድሩ ራሳቸውን ለማግለል እንደሚችሉም በማሳወቅ ላይ ናቸው። 

ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንድ የፖለቲካና የግጭት ጉዳዮች ተንታኝ መጪው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ሁሉ በእጅጉ የተሻለ እንዲሆን መንግሥት የምርጫጎችን በማሻሻልና የምርጫ አስፈጻሚውን ተቋማዊ ጥንካሬ በማጎልበት፣ እንዲሁም ከቀድመው የተሻለ ገለልተኛ የሆኑ የቦርድ ከባላት እንዲመራ መደረጉ ትልቅርምጃ ቢሆንም ይህ ብቻውን ወደሚፈለገው ግብ እንደማያደርስ ይገልጻሉ።

ቀጣዩ ምርጫ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሆን መሟላት ከሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አንዱ የምርጫ ሒደቱ የሚካሄድበት ዓውድ፣ ሰላማዊና ምቹ ወይም የተረጋጋ መሆኑ ነው ብለዋል። 

ይህ ድባብ ሲኖርፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ በሚደረግባቸው አካባቢዎች በነፃነት መንቀሳቀስ ያስችላቸዋል የሚሉት ባለሙያው፣ በሰላምና በነፃነት መንቀሳቀስ ሲቻል ደግሞ ፓርቲዎች አማራጮቻቸውን በቀላሉ ለማኅበረሰቡ ማቅረብና ማስረዳት እንደሚያስችላቸው ይገልጻሉ። 

በሰከነ የፖለቲካ ዓውድ ውሰጥ የሚያልፍ የምርጫ ሒደት ለፖለቲካ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆን መራጮች ደኅንነታቸው ተጠብቆ ያለ ሥጋትና ፍርኃት ድምፃቸውን በምክንያት ላይ ተመሥርተው በመስጠት የፈለጉትን ፓርቲ መንግሥት አድርገው እንዲመርጡ ያስችላቸዋል የሚሉት ባለሙያው፣ ይህ ሲወራ ቀላልና የተለመደ አገላለጽ ቢሆንም የአንድን ምርጫና ከምርጫው በኋላ የሚኖረውን አገራዊ የፖለቲካ ሁኔታ የሚወስን እንደሆኑ ያስረዳሉ።

ከዚህ አኳያ በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ሲገመገም ከፍተኛ ጉድለት እንዳለበት የሚገልጹት ባለሙያው፣ ምርጫው በዚህ ድባብ ውስጥ ባይካሄድ ይመርጣሉ። 

ነገር ግን ይህንን አሁን ማድረግ የሚቻል አይመስልም፣ ቢቻልም ያንን ማድረግ በራሱ የሚያስከትለው ቀውስ ሊኖር እንደሚችል በመገመት ምርጫ ቦርድ በአፋጣኝ ማድረግ አለበት ያሉትን ያሳስባሉ፡፡ 

‹‹የምርጫ ቦርድ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ አጠቃላይ የግጭት ሁኔታ ትንተና (ኮንፍሊክት አሰስመንት) ሠርቶምርጫ ቅሰቀሳም ሆነ ምርጫ ለማድረግ አስቸጋሪ የሆኑ ቦታዎችን በፍጥነት ማሳወቅ አለበት፤›› ሲሉ ሐሳባቸውን አቅርበዋል። 

ይህ ሳይደረግ የሚካሄድ የምርጫ ቅስቀሳ በተለይልጣን ላይ ያለውን ፓርቲ ለሚቃወሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስቸጋሪ የደኅንነትጋት ሲፈጥር፣ ለገዥው ፓርቲ ግን የተመቻቸ የውድድር ሜዳ ይፈጥራል ብለዋል። 

ምክንያታቸውንም ሲያብራሩ፣ ‹‹ገዥው ፓርቲ የመንግሥት ሥልጣን ላይ መሆኑ የሚሰጠውንድል ተፎካካሪ ፓርቲዎች አያገኙም። ከወረዳ እስከ ቀበሌ ያሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚገኙ የገዥው ፓርቲ አባላት በእንደዚህ ዓይነት የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ለመንቀሳቀስ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይቸገሩም፡፡ በመሆኑም በዚያውድ መንቀሳቀስ የሚችል በምርጫውም የተሻለድል ይኖረዋል፤›› ብለዋል።

የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ማድረግ ያልቻለ ፓርቲ በአካባቢዎቹ የመራጮችን ድምፅ የማግኘት ዕድሉ የመነመነ ሲሆን፣ ገዥው ፓርቲ ግንልጣን ላይ የሚገኝ በመሆኑ የተሻለድል ይኖረዋል ሲሉ ሐሳባቸውን ያጠናክራሉ።

በመሆኑም ያለው ሁኔታ ምክንያታዊ ተቀባይነት ባለው ደረጃ ለሁሉም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተሳትፎ ምቹ መሆንና አለመሆን በግጭት ጥናት በመለየት ማሳወቅ፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁኔታውን እንዲያስተካክሉ ጊዜ መስጠትና ሌሎች ጥረቶችን ማድረግ ይገባል ብለዋል። ሁኔታው ባልተሻሻለባቸው አካባቢዎች ደግሞ ምርጫው በሌላ ጊዜ እንዲከናወን መወሰን ያስፈልጋል ሲሉ አክለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላት ከሁለት ሳምንት በፊት ምርጫውን በተመለከተ ያላቸውንጋትና ተስፋ በሰጡት የቪዲዮ መልዕክት፣ የፀጥታ ሥጋት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳን ጨምሮ የሚያሳስባቸው እንደሆነ ገልጸዋል። 

ከአምስቱ የምርጫ ቦርድ አመራር አባላት አንዷ የሆኑት ወ/ሮ ብዙወርቅ ከተተ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹ምርጫው የሚካሄድበት ምህዳር ውስብስብ ነው፣ አንዱ ትልቁ ሥጋት የፀጥታው ሁኔታው ነው። ይህንን ሥጋት ለመቅረፍ የመንግሥትም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሌሎች ባለድርሻ አካላት የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ የተጀመሩ ሥራዎች አሉ፣ ይህንን አጠናክሮ መቀጠል ያስፈልጋል፤›› ብለዋል። ከፀጥታጋት በተጨማሪ የጊዜ እጥረት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል።

የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በበኩላቸው፣ ‹‹ወደ ምርጫ አፈጻጸም ስንሄድላማዊነቱን መጠበቅ አንዱ ችግር ይሆናል ብዬ እገምታለው ነገር ግን እየተዘጋጀንበት ነው። በየቦታው ላይ ችግር ሊፈጥሩ የሚችሉ ሁኔታዎች ምንድንናቸው? ወደ ግጭት ሊያመሩ የሚችሉ ምንድንናቸው? ቦርዱ፣ ፓርቲዎችና ሲቪል ማኅበራት ይህ ችግር እንዳይፈጠር እንዴት መከላከል ይችላሉ? የሚለውን እያጠናን የተለያዩ የመከላከያ አሠራሮችን ለመዘርጋት እየሞከርን ነው፤›› ብለዋል። 

በአፍሪካ ሥልጣን ላይ ያሉ ገዥ ፓርቲዎች ከላይ የተገለጹትን ዓይነት ተግዳሮቶች በሌሎች ላይ ሲፈጥሩ ይስተዋላል እንጂ፣ እንደ እነዚህ ዓይነት ተግዳሮቶች እነርሱን እምብዛም አይገጥማቸውም ወይም ጨርሶም አያውቋቸውም። 

የወቅቱ የኢትዮጵያ ገዥ የፖለቲካ ድርጅት የሆነው ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ዘመቻ እንቅስቃሴ በይፋ በተጀመረበት የካቲት 8 ቀን ለምርጫ ውድድር ያዘጋጀውን ማኑፌስቶ በይፋ ያስተዋወቀ ሲሆን፣ በተለያዩ የመንግሥት ሚዲያዎችም ሰፊ ሽፋን ተስጥቶታል። 

በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ፕሬዚዳንትና ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) ባደረጉት ንግግር፣ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አቃፊና ቃሉን መተግበር እንጂ ብዙም መናገር የማይሆንለት የተለየ ፓርቲ እንደሆነ ገልጸዋል። 

እሳቸው በወቅቱ ባደረጉት ንግግር ፓርቲያቸው መጪውን ምርጫ እንደሚያሸንፍእርግጠኝነት ያስታወቁ ሲሆን፣ ይህ እንዳለ ሆኖ ከሁሉ በላይ የሚፈልጉት መጪው ምርጫ ሁሉም በእኩልነት የሚሳተፍበትናዝብ በነፃነት በድምፁ የሚወስንበት እንዲሆን እንደሚሠሩና ይህ እንዲሳካም ሁሉም ባለድርሻ አካል ትብብር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። 

በዚሁ ንግግራቸው ወቅት ስለብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ማኒፌስቶ ይዘቶች ገልጸው፣ ‹‹ተፎካካሪ ፓርቲዎች እኔም የትምህርት ፖሊሲ አለኝ፣ እኔም የጤና ፖሊሲ አለኝ ብለው በዚህ በአንድ ወር ውስጥ ይቀርባሉ። ነገር ግን ድርሰት እንጂ ፖሊሲ ሊሆን አይችልም፤›› ብለዋል። 

የምርጫ አዋጁ አንቀጽ 143(6) ላይ የሰፈረው ድንጋጌ ማንኛውም ተወዳዳሪ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ አመራርና ወኪል የሌሎች ፓርቲዎች ወይም ተወዳዳሪዎች የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ እንዲስተጓጎል ወይም እንዲቋረጥ፣ ወይም እንዲበላሽ ወይም እንዲዳከም ማድረግ እንደማይችልና ይህንን ማድረግ የሥነ ምግባር ጥሰት እንደሆነ ይደነግጋል። 

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -