Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የ‹‹ሸገሮቹ›› ጥንካሬና ብርታት ቀጣይነት ይኖረው ይሆን?

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር የ‹‹ሸገሮቹ›› ጥንካሬና ብርታት ቀጣይነት ይኖረው ይሆን?

ቀን:

በባህር ዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም የተጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 13ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዋንጫ ፉክክሩ ተገማች ሲያደርጋቸው፣ የአሠልጣኝ ለውጥ ያደረጉ ክለቦችን ደግሞ ወደ ተባባሰ ችግር ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ ለአዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ሁለተኛ አሠልጣኝ ስንብትም ምክንያት ሆኗል፡፡

ላለፉት ሁለት አሠርታት በተዟዙሮ የጨዋታ ሥርዓት ቀጥሎ የቆየው ፕሪሚየር ሊጉ፣ በአዲስ አበባና በጅማ ከተሞች እንዲሁም አሁን ላይ ባህር ዳር ከተማ ላይ የ13ኛ ሳምንት የጨዋታ መርሐ ግብሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ፕሪሚየር ሊጉን በቀጥታ የማስተላለፉ መብት ሽያጩን የገዛው የዲኤስቲቪና የሊጉ አስተዳደዳሪ ሼር ካምፓኒ ከኅዳር 2013 ዓ.ም. ጀምሮ ስምምነት ማድረጋቸውን ተከትሎ ሁሉም ጨዋታዎቹ ለተመልካች ተደራሽ ሆነዋል፡፡

ቀደም ሲል በሼር ካምፓኒውና በዲኤስቲቪ ስምምነት መሠረት በሊጉ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል 60 ጨዋታዎች የቀጥታ ሽፋን እንደሚያገኙ ተነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ እስካሁን ባለው ግን በቀጥታ ሥርጭት ለተመልካች ካልደረሱት ሁለት ጨዋታዎች በስተቀር ሌሎቹ እንዲተላለፉ ተደርጓል፡፡ ቀሪዎቹ ጨዋታዎችም በተመሳሳይ ሽፋን የሚያገኙ ስለመሆናቸው ጭምር ከካምፓኒው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በፕሪሚየር ሊጉ የ13ኛ ሳምንት ጨዋታ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ኢትዮጵያ ቡናና ቅዱስ ጊዮርጊስ በእኩል 24 ነጥብ በጎል ተበላልጠው ከመሪው ፋሲል ከተማ በአራት ነጥብ ዝቅ ብለው እንዲገኙ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሁለቱ የሸገር ደርቢዎች በዚሁ ሳምንት ለዋንጫ ፉክክሩ ተገማች ከመሆናቸው ባሻገር በጨዋታ ላይ ተጋጣሚዋቻቸውን እኩል አራት ጎል በማስቆጠር 4 ለ1 እና 4 ለ2 ማሸነፍ መቻላቸው አጋጣሚውን ለየት እንዲል አድርጎታል፡፡

ሌላው ሁለቱ ቡድኖች ተጋጣሚዎቻቸው በሆኑት አዳማ ከተማና ወልቂጤ ከተማ ላይ ካሳዩት የጨዋታ ብልጫ በመነሳት ብቃታቸው ቀጣይነት ይኖረው ይሆን? የሚል ጥያቄ ማስነሳቱም አልቀረም፡፡

የሊጉ መሪ ፋሲል ከተማ አሁን ላይ በእያዳንዱ ጨዋታ ላይ እያሳየው ካለው እንቅስቃሴ አንፃር በብዙዎች የአሸናፊነት ግምት ያገኘ ብቸኛው ቡድን ሆኖ ነበር፡፡ ሁለቱ የሸገር ደርቢዎች ጅማ ከተማ ላይ ባደረጉት ጨዋታ ውጤት የጣሉበት ሒደትና እንቅስቃሴ ግምቶች ወደ ፋሲል እንዲያዘነብሉ በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ከሁለቱ ቡድኖች በተቃራኒ ሳምንቱ ብዙዎቹ ባጋጠማቸው የውጤት ቀውስ ምክንያት አሠልጣኞችንና መሰል ኃላፊዎችን ላሰናበቱ ክለቦች ለበለጠ ሥጋት የዳረጋቸው ሆኗል፡፡ የውጤት ቀውሱ ሥጋት ካለባቸው መካከል የአዳማ ከተማ እግር ኳስ ቡድን አንዱ ሲሆን፣ ቡድኑ ባለፈው ሳምንት ከውጤት ጋር በተያያዘ የቡድኑን ዋና አሠልጣኝ ካሰናበተ በኋላ በተመሳሳይ በውጤት ምክንያት ከሲዳማ ቡና የተሰናበተውን አሠልጣኝ መቅጠሩ መዘጋባችን ይታወሳል፡፡

ይሁንና ክለቡ አሁንም ውጤት ሊቀናው ባለመቻሉ የቡድኑ ሁለተኛ አሠልጣኝ የነበሩትን አሠልጣኝ አስቻለው ኃይለ ሚካኤል ሁለተኛው ተሰናባች እንዲሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡ ለአሠልጣኙ ቅርብ የሆኑ ሰዎች እንደሚናገሩት ከሆነ፣ አሠልጣኝ አስቻለው ኃላፊነታቸውን የለቀቁት በራሳቸው ፍላጎት እንደሆነ ነው፡፡ ክለቡ እስካሁን በጉዳዩ የሰጠው ማስተባበያም የለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...