Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ሚኒስትሩ የውኃ ሀብት የግጭት መነሻ መሆኑ እስካልቀረ ድረስ ጥቅም ላይ ሳይውል...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውኃ ሀብት የግጭት መነሻ መሆኑ እስካልቀረ ድረስ ጥቅም ላይ ሳይውል መፍሰስ የለበትም አሉ

ቀን:

ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና ውስጥ ውኃ የጭቅጭቅ መነሻ መሆኑ አይቀሬ እንደሆነና ይህንን ማስቀረት እስካልተቻለ ድረስ ኢትዮጵያ ሀብቷን ጥቅም ላይ ሳታውል ማፍሰስ እንደማይገባት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) አሳሰቡ። 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሰሞኑን ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር ባደረጉት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ በሰጡት አስተያየት ‹‹ውኃ በዚህ በእኛ ቀጣና ውስጥ የጭቅጭቅ፣ የዲፕሎማሲ፣ የግጭትና የውጊያ መነሻ ማዕከል መሆኑ አይቀርም፡፡ ነዳጅን መተካቱ አይቀርም›› የሚል አስተያየት ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ያሏት የውኃ ሀብቶች በሙሉ ወደ ሌላ አገር የሚፈሱ እንጂ ከሌላ አገር ወደ ኢትዮጵያ የሚፈስ አንድም የውኃ ሀብት እንደሌለ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያን የተፈጥሮ የውኃ ሀብት በመጠቀም ረገድ በመንግሥት በኩል ያለው ዕይታ የተሟላ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢትዮጵያ የውኃ ሀብት ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያና ሱዳን እንደሚፈስ ለዓብነት ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ግን ከአንድም አገር ውኃ የምትቀበል እንዳልሆነች ተናግረዋል።

‹‹ኢትዮጵያ ከአንድም አገር ውኃ አትቀበልም ግን ሰጪ ናት፡፡ ይህንን የምትሰጠውን ውኃ ቢያንስ ተጠቅማበት የምትሰጥ አገር መሆን አለባት እንጂ ዝም ብሎ በተፈጥሮ በተቀደደለት ቦይ የሚፈስ ከሆነ ዋጋ የለውም። በተፈጥሮ ሸለቆው ዝም ብሎ እየፈሰሰ የሚያጣላን መሆን የለበትም፤›› ብለዋል። 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩትበት ወቅት ኢትዮጵያ በዓባይ ውኃ ላይ በጀመረችው ታላቁ የህዳሴ ግድብ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ከሱዳንና ከግብፅ ጋር የተካረረ ጭቅጭቅ ውስጥ በገባችበት ወቅት መሆኑ በበርካቶች ላይ ግርምትን ጭሯል። 

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የግብፅና የሱዳን መንግሥታት ኢትዮጵያ ወደፊት ከህዳሴ ግድቡ በላይ ባለው የዓባይ ተፋሰስ ላይ ተጨማሪ የውኃ ልማት ፕሮጀክቶችን እንዳታለማ የሚገድብ የሕግ ስምምነት ለማስፈረም ግብፅና ሱዳን ማሴራቸው ሦስቱ አገሮች ታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ስምምነት ላይ እንዳይደርሱ መሠረታዊ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። 

የወቅቱ የአፍራካ ኅብረት ሊቀመንበር የሆነችው ዴሞክራቲክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ከፍተኛ የመንግሥት ልዑካን ቡድን በተጠናቀቀው ሳምንት በሱዳን ከተማ ተገኝቶ ከአገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር የህዳሴ ግድቡን ድርድር ለማስቀጠል ውይይት አድርጓል። 

በወቅቱም የሱዳን መንግሥት የተቋረጠው ድርድር ሊቀጥል የሚችለው ከሦስቱ ባለጉዳይ አገሮች በተጨማሪ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ አሜሪካና የአፍሪካ ኅብረት በጋራ የሚሳተፉበት አሠራር ከተዘረጋ ብቻ ነው የሚል አቋማቸውን ግልጽ አድርገዋል። 

ከዚህ በተጨማሪም ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ዙር ሁለተኛ ዓመት የውኃ ሙሌትመጪው ሐምሌ ወር ማካሄድ የለባትም ይህ ከሆነ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሱዳናውያንና ከህዳሴ ግድቡ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኘው የሱዳን ግድብን አደጋ ላይ እንደሚጥል አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ የውኃ ሀብት በተቻለ አቅም ሁሉ ጥቅም ላይ ሳይውል ወደ ታችኞቹ አገሮች ሊፈስ አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለካቢኔ አባሎቻቸው ሰሞኑን ማሳሰቢያ መስጠታቸው ኢትዮጵያ በዓባይ ውኃና በህዳሴ ግድቡ ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የውኃ ሀብቶቿንም ማልማቷን እንደምትቀጥል ለማሳወቅ ያደረጉት ንግግር እንደሆነና አቅም እስካላት ድረስም የሚከለክላት እንደሌለ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...