Sunday, September 25, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው የቀረበውን ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ሪፖርት ከተመለከቱ በኋላ ተጨማሪ ውይይት እያደረጉ ነው] 

  • የአሜሪካ መግለጫ በዚህን ያህል ጠንካራ መሆኑ ትንሽ አሳስቦኛል፡፡
  • ቀጥሎ ሊወስዱት የሚችሉት እንጂ መግለጫው እንኳን አያሳስብም።
  • እኔም እሱን ነው የምለው፡፡
  • ዕርምጃ ከመውሰዳቸው በፊት እንዲወጡ ቢደረግ. . .
  • ልክ ነው ዕገዳ ሳይጥሉ መሄድ አለባቸው፡፡ 
  • መውጣት ነው ወይስ መሄድ ያለባቸው? 
  • ዕገዳ ሰይጥሉ መሄድ ነው ያለባቸው፡፡
  • እነ ማንን ነው የሚሉት ክቡር ሚኒስትር?
  •  ልጆቹን ማለቴ ነው፡፡
  • ልጆቹ?
  • አዎ። ሁለቱ ልጆቼ በውጭ አገር እንደሚማሩ ታውቅ የለ?
  •  አዎ። 
  • ነገሩ ፀጥታው ምክር ቤት ከደረሰ ባለሥልጣናት የጉዞም የምንም ዕገዳ ሊጥሉ ይችላሉ?
  • ስለዚህ?
  • በፍጥነት መውጣት አለባቸው። 
  • ለልጆቹ ከሆነ መውጣት ከሚሉት ቅድም ያሉት ይሻላል።
  • ምን ያልኩት? 
  • መሄድ! 

  [ ክቡር ሚኒስትሩ ከአማካሪያቸው ጋር የጀመሩትን ሳይጨርሱ ስልካቸው ጠራ። የውጭ ጉዳይ ባልደረባቸው ነበር] 

  • ይገርማል እያስከብኩህ ነው የደወልከው፡፡ 
  • ምነው በሰላም ክቡር ሚኒስትር?
  •  በሰላም ነው። እንደው የአሜሪካ መግለጫ ብግን አድርጎኝ ላወራህ ነበር።
  • ምን ይደረጋል ብለው ነው?
  • እንዴት?
  • ያው አሜሪካ አሜሪካ ነች ብዬ ነው።
  • አሜሪካ ብትሆንስ! አላየህም እንዴ የማኅበረሰቡን ምላሽ?
  • እርግጥ ነው ማኅበረሰቡ. . .
  • ከእርግጥ በላይ ነው እንጂ፡፡ በዚያ ላይ መገጣጠሙ አይገርምም?
  • የምኑ?
  • ከዓድዋ በዓል ጋር መገጣጠሙ እኮ ነው ሕዝቡን ያስቆጣው።
  • እሱስ ልክ ነው፡፡ ነገር ግን. . .
  •  የምን ነገር ግን ነው. . . ሕዝቡ በነፃነቱ ሲመጡበት ቀፎው እንደተነካ ንብ እንደሚሆን እያሳየን፡፡
  • ወደ ደወልኩበት ጉዳይ ለመግባት ነበር እንደዚያ ያልኩት፡፡
  • ምን ነበር?
  • ዕርምጃ ከወሰዱ ምን ሊስተጓጎል እንደሚችል ለመለየት ጥናት እያደረግን ነው።
  • ጥሩ ነው። በዋናነት የጉዞ ዕገዳ ሊጥሉ ስለሚችሉ ልጆች ቢወጡ ጥሩ አይመስልህም። 
  • የጉዞ ዕገዳ ማን ላይ ይጥላሉ. . . የምን ልጆች?
  • ባለሥልጣናት ላይ የጉዞ ዕገዳ ሊጥሉ ይችላሉ ብየ አስባለሁ፡፡ 
  • ስለዚህ ምን መደረግ አለበት?
  • ልጆቻቸውን ውጭ አገር የሚያስተምሩ ቀድመው ቢያስወጡ አይሻልም. . . ጥናቱ ላይ ብታካትተው፡፡
  •  ጥናቱ ላይ?
  • አዎ።
  • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር ጥናቱ ስለ አገር እንጂ ስለ ቤተሰብ አይደለም። 

  [ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ የኢኮኖሚ ጉዳይ ላይ መግለጫ እንዲሰጡ በታዘዙት መሠረት ከአማካሪያቸው ጋር ሆነው ዝግጅት እያደረጉ ነው] 

  • የዳቦ ዋጋ ለምን ተወደደ የሚል ጥያቄ ቢነሳ ምን ይመልሳሉ? 
  • የገበያ ሰንሰለቱን የተቆጣጠሩት ሙሉ በሙሉ መበጣጠስ ባለመቻሉ ነው በቅርቡ መፍትሔ ያገኛል እላለሁ።
  • በጣም ጥሩ።
  • ግን መንግሥት ዳቦ ፋብሪካ ገንብቶ ራሱ እያከፋፈለ የምን ሰንሰለት ነው ብለው ቢጠይቁስ?
  • አይጠይቁም፡፡
  • እንዴት እርግጠኛ መሆን ይቻላል?
  •  አይጠይቁም ስልዎት፡፡ ይልቅ ወደ ቀጣዩ እንግባ፡፡ 
  • እሺ ቀጥል፡፡ 
  • የሰሞኑ የዋጋ መናር መነሻው ምንድን ነው? መንግሥትስ ምን እያደረገ ነው የሚል ጥያቄ ቢጠይቁ ምን ይላሉ?
  • ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ ምርት ወደ ከተማ እንዳይገባ ዘመቻ በመከፈቱ ነው፡፡ መንግሥት በቅርቡ ዕርምጃ በመውሰድ ለሕዝብ ያሳውቃል እላለሁ። 
  • በጣም ጥሩ ትክክል።
  • ግን ግን. . . ምርት እንዳይገባ ተቃዋሚዎች ዘመቻ ከፍተው ሊሆን ይችላል የመኖሪያ ቤት የኪራይ ዋጋ እንዴት ሊጨምር ቻለ ብለው ቢጠይቁስ?
  • በጭራሽ አይጠቁም። 
  • እንዴት እርግጠኛ ልትሆን ቻልክ?
  • ተቃዋሚዎች በከፈቱት ዘመቻ ምክንያት ነው ዋጋ የጨመረው የምንለው በምክንያት ነው። 
  • ማለት . . . የምን ምክንያት?
  • እንደዚያ ዓይነት ጥያቄ እንዳይነሳ። 
  •  እንዴት?
  • ጥያቄ የሚያነሳ የዛቻው አካል ተብዬ እፈረጃለሁ ብሎ ስለሚሠጋ። 
  • የቱ ዘመቻ?
  • የዋጋ ንረቱ እንዲፈጠር የተቀነባበረው ዘመቻ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  የአውሮፓ ኅብረት ተወካይ በተመድ ጉባዔ ‹‹የትግራይ መንግሥት›› በማለት ላደረጉት ንግግር ማስተካከያ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች

  በስዊዘርላንድ ጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 51ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ)...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  ብሔራዊ ባንክ ለፋይናንስ ተቋማት ለሚሰጠው ፈቃድና አገልግሎት እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ሊያስከፍል ነው

  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለአገሪቱ የፋይናንስ ተቋማት ለሚሰጠው የፈቃድ፣ የብቃት...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  በኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የምዕራባውያን ጣልቃ ገብነት

  ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ጠንካራ ጫና ማሳደራቸውን ቀጥለዋል፡፡ በዲፕሎማሲም...

  የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የድጎማ በጀት ለፖለቲካ ሥራ ማስፈጸሚያ እንደሚውል የሚያሳይ ሪፖርት ቀረበ

  ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚደረግ የበጀት ድጎማ ከመደበኛው ሥራ ይልቅ ከዋናው...

  መንግሥት የሥራ ግብር ምጣኔን እንዲቀንስ ተጠየቀ

  የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሠማኮ) መንግሥት የሠራተኛውን የኑሮ ጫና...

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የአመራሮች ምርጫና ቀጣይ ዕቅዶቹ

  የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሲጠበቅ የነበረውን...

  በ15 ቢሊዮን ብር የተመዘገበ ካፒታል የማይክሮ ፋይናንስ አገልግሎቱን ያሻገረው ስንቄ ባንክ ሥራ ጀመረ

  ከማክሮ ፋይናንስ ተቋምነት ወደ ባንክ አገልግሎት ከተሸጋገሩ አምስት የማክሮ...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [አብሮ የሚኖረው ወንድማቸው በተደጋጋሚ እየደወለ መሆኑን የተመለከቱት ክቡር ሚኒስትሩ በስተመጨረሻ የእጅ ስልካቸውን አንስተው ሃሎ አሉ]

  ሃሎ... ስብሰባ ላይ ሆኜ ነው ያላነሳሁት ...በሰላም ነው? ሰላም ነው። ልንገርህ ብዬ ነው... ምንድነው ምትነግረኝ?  ዛሬ አልመጣም፣ እንዳትጠብቀኝ ልነግርህ ነው። ምን ማለት ነው? ወደ አገር ቤት ልትመለስ ነው?  እንደዚያ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጋር ደውለው ልማታዊ ወጣቶች ያቀረቡት አቤቱታ በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጠው እያሳሰቡ ነው]

  እየደገፉን ያሉ አንዳንድ ልማታዊ ወጣቶች በከተማ አስተዳደሩ ላይ ቅሬታ አቅርበዋል። እኛ ላይ?  አዎ!  ቅሬታቸው ምንድነው? ለምን ለእኛ አላሳወቁንም? የሚሰማቸው ስላላገኙ ነው ቅሬታቸውን ወደ እኛ ይዘው የመጡት።  እስኪ ነገሩን አጣራለሁ...

  [ክቡር ሚኒስትሩ አዲሱ ዓመት ሰላም ይዞ ይመጣል የሚል ተስፋቸውን ለባለቤታቸው እየገለጹ ነው]

  መንግሥት አሁንም እጁን ለሰላም እንደዘረጋ ነው። ነገር ግን በዚያኛው ወገን ከጦርነት በቀር ሌላ ፍላጎት የለም። ከዚህ አዙሪት በቀላሉ መውጣት ይቻላል ብለህ ታምናለህ? አዲሱ ዓመት ሰላም ይዞ...