በየዓመቱ የካቲት 23 ቀን እየተመላለሰ የሚመጣው የዓድዋ ጦርነት ድል መታሰቢያ በተከሰተ ቁጥር፣ ከሚደመጡት ዘፈኖች አንዱ የድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ‹‹ትናገር ዓድዋ ትናገር ትመስክር›› ተጠቃሽ ነው፡፡ ዘንድሮም ክብረ በዓሉ በአዲስ አበባ ሲከበር በየሚዲያው ሞገድ አሳብሮ ተሰምቷል፡፡ ማክሰኞ የካቲት 23 ቀን 2013 ዓ.ም.፣ በአራዳ ጊዮርጊስ በሚገኘው የዳግማዊ ምኒልክ አደባባይ ዕለቱ ሲታሰብ፣ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ተገኝተው የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡ ፎቶዎቹ የአከባበሩን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡
ፎቶ መስፍን ሰሎሞን